ዛሬ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ በኦሮሚያና ሶማሌ አዋሳኝ ድንበር አካባቢ በተለይም በሐረርጌ በተከሰተው ግጭት ”ተረብሸናል” ብሏል።
በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግሥት ግጭቱን ግልጽ በሆነ አካሄድ እንዲያጣራና ተጠያቂዎቹን ለህግ እንዲያቀርብ ጠይቋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በአካባቢው እየተፈጠረ ስላለው ሁኔታ ”ግልጽ መረጃ የለም’ ይላል የአሜሪካ ኤምባሲ መግለጫ፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ ግጭቱ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለችግሩ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲሹ መበረታታት ይኖርባቸዋል ብሏል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በሃገሪቱ ውስጥ በሁለቱም ዘሮች ላይ የተነሳው የእርስ በእርስ ግጭት ብዙ ማህበረሰብ ከመኖሪያ ቦታቸው እንዲፈናቀሉ ከማድረጉም በላይ ቁጥራቸው እስከ አሁን በውል ያልታወቁ ማህበረቦችን ለሞት መዳረጉም ተገልጦአል።
መንግስት የእርስ በእርስ ግጭቱን አስመልክቶ የተለያዩ በሃሳብ የተጣረሱ መረጃዎችንም ቢያቀርብም በኦሮሚያ እና በሶማሊያ ክልል ያሉ የመንግስቱ አገልጋይ የተባሉት አመራሮች እርስ በእራሳቸው መካሰሳቸውንም መረጃዎች ጠቁመዋል።
ባለፈው አርብ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሃላፊ ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ከቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ጋር ባደረጉት ቆይታ የኦሮሚያንና የሶማሌ ክልሎች ሃላፊዎችን ማስጠንቀቃቸውንና አስፈላጊውን ማጣራት ተደርጎ ጥፍተኞቹን ለህግ እንደሚቀርቡ መግለጻቸው ይታወሳል።
”ኢትዮጵያ ጠንካራ፣ የበለጸገችና ዴሞክራሲያዊት ሀገር መሆን የምትችለው፤ ግልጽና ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ውይይትና ግልጽ የመንግሥት አሰራር ሲኖራት፣ እንዲሁም የዴሞክራሲና የፍትህ ተቋማትን ማጠናከር ስትችል እንደሆነ እናምናለን፡፡ የሰሞኑ ሁነቶች በተጠቀሱት ዘርፎች ላይ ይበልጥ ፈጣንና ተጨባጭ ለውጥ አስፈላጊ እንደሆነ አመላካች ናቸው” ይላል የአሜሪካ ኤምባሲ መግልጫ እንደሚያመለክተው ።
በሌላም በኩል መንግስት በአማራው ክልል ያደረገው የዜጎችን የእርስ በእርስ መለያየት እና ማንነታቸሁን በእራሳችሁ መንገድ መለየት አለባችሁ በሚል ስሜት አልባ ምርጫ ህዝቡን ማስቆጣቱን መገናኛ ብዙሃኑ ገልጸዋል ። በተለይም ላለፉት ፲፰ አመታት ኢትዮጵያ በከፍተኛ ዘር እንድትታመስ የተደረገበት ዋነኛ አላማው ቀዳማይት ትግራይ የሚለውን አላማቸውን ለማሳካት እንደሆነ እና በተሳካ ሁኔታ ኦሮሞውን እና አማራ ብሄረሰቡን ከለያዩ በኋላ በመቀጠልም አማራው ጉልበት እንዳይኖረው በሰሜን ጎንደር እርስ በእራሱ እንዲጋጭ እና ስምምነት እንዲኖረው አላደረጉም ይህም የእራሳቸው ፖለቲካ እንዲጠናከር አድርገዋል ሲሉ መገናኛ ብዙሃኖቹ ገልጸዋል። ኢትዮጵያኖችን አንድ ነን እያሉ ለዘለአለም ሲዘምሩት የነበረው የአንድንነት መዝሙር በትግራይ አስተዳደር እና የአስተዳደሩ ደጋፊ በሆኑ ህዝቦች መሰበሩን እና ዛሬም ይህንን እየዘመርን ወደኋላ ከምንቀር በአጽንኦት አስበንበት አንድነታችንን ብናጠናክር ጥሩ ነው ሲሉ ከአዲስ አበባ ያሉ መገናኛ ብዙሃኖች ገልጸዋል።
Average Rating