www.maledatimes.com ቴዲ አፍሮ “ሎሬት” በሚለው የክብር ማዕረግ የመጠራት ፍላጎት እንደሌለው ተገለጸ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ቴዲ አፍሮ “ሎሬት” በሚለው የክብር ማዕረግ የመጠራት ፍላጎት እንደሌለው ተገለጸ

By   /   September 24, 2017  /   Comments Off on ቴዲ አፍሮ “ሎሬት” በሚለው የክብር ማዕረግ የመጠራት ፍላጎት እንደሌለው ተገለጸ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 10 Second
 እጅግ በጣም ተወዳጁ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ! በኪነጥበብ ሙያ ላበረከተው የጎላ አሰተዋአዖኦ የተለያዩ ሽልማቶች የተበረከተለት ሲሆን ወደፊትም በአገር ውስጥ እና በውጪ የሚበረከትለት ሽልማት እንዳለ መረጃዎች ያመላክታሉ። ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ በአገር ውስጥ እና በውጪ የተበረከተለት ሽልማት እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በአቢሲንያ የሽልማት ድርጅት አማካኝነት ቴዲ አፍሮ በኪነጥበብ ዘርፍ ሁለንተናዊ አስተዋጽዖ የ”ሎሬት” የክብር ማዕረግ መጠሪያ ስም መስጠቱ የሚታወስ ነው።

በአቢሲንያ የሽልማት ድርጅት አማካኝነት “በሎሬት” ማዕረግ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ መጠራቱን ተከትሎ ፤ የተለያዩ አሰተያየት ሰጪዎች የየራሳቸውን የድጋፍ እና የተቃውሞ ሃሳብ ሲገልጹ እንደነበር የሚታወስ ነው። በጉዳዩ ዙሪያ ቴዲ አፍሮ እስካሁን በይፋ ምንም አይነት ምላሽ ያልሰጠ ሲሆን፤ “ሎሬት” በሚለው የክብር ማዕረግ የመጠራት ፍላጎት እንደሌለው፤ ተዋቂው የፊልም ዳይሬክተር ያሬድ ሹመቴ በማህበራዊ ድረገጽ በአጽንዖት ገልጸዋል ። ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን “ኢትዮጵያ” ከተሰኘው አዲሱ የሙዚቃ አልበም ውስጥ “ማር እስከ ጧፍ” በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ የሆነ ሙዚቃ ነው። ይህ ሙዚቃ ወደ ቪዲዮ ክሊፕ በቅርብ ቀን ተሰርቶ ለአድማጭ ተመልካች ቀርቦል። የሙዚቃ ቪዲዮ ክሊፕ ኤዲተር ያሬድ ሹመቴ ነው።

የፊልም ዳይሬክተር ያሬድ ሹመቴ፤ ቴዲ አፍሮ “ሎሬት” በሚለው የክብር ማዕረግ የመጠራት ፍላጎት እንደሌለው ሲገልጽ፤ “በተደጋጋሚ አጠገቡ ሆኜ ባስተዋልኩት መሰረት፤ ቴዲ ሽልማቱን ለሰጡት አካላት አክብሮት ያለው ቢሆንም ይህ የክብር ስም በፍፁም ለሱ የሚገባ እንዳልሆነ በተደጋጋሚ ሲናገር ሰምቼዋለሁ ! ” በማለት ያሬድ ሹመቴ በጽሑፍ የገለጸ ሲሆን፤ “ሎሬት” በሚለው ማዕረግ በርካታ አድናቂዎቹ እየጠሩት መምጣቱ ቴዲ አፍሮ’ን “ሲረብሸው” ተመልክቻለሁ፤ “በዚህ ስም “የመጠራት ፍላጎት የለውም !! በማለት አበክሮ ገልጸዋል ። አድናቃዎቹም ይሄን ተረድተው “ቢተባበሩት መልካም ነው” በማለት መልእክቱን ያስተላለፈ ሲሆን ፤ ድምጻዊ ቴውድሮስ ካሳሁን ከአቦጊዳ ባንድ አባላት ጋር የሙዚቃ ኮንሰርቱን ለአድናቂዎቹ ለማቅረብ በከፍተኛ ጥናት ላይ እንደሆነ ጨምሮ ገልጾዋል ።

(ይድነቃቸው ከበደ)
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar