www.maledatimes.com አሳዛኝ መረጃ … የአለማችን ወፍራሟ ሴት አረፈች :( - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

አሳዛኝ መረጃ … የአለማችን ወፍራሟ ሴት አረፈች :( 

By   /   September 25, 2017  /   Comments Off on አሳዛኝ መረጃ … የአለማችን ወፍራሟ ሴት አረፈች :( 

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 9 Second

=================================
* ግብጻዊዋ ኢማን 500 ኪሎ ትመዝን ነበር
* ያረፈችው አቡዳቢ ውስጥ ቡርጅ ሆስፒታል ነው

500 ኪሎ ግራም በመመዘን በአለማችን ወፍራሟ ሴት እንደሆነች የምትገመተው ግብጻዊዋ እመቤት ኢማን አብ ኢል አታይ ዛሬ ሰኞ መስከረም 15 ቀን 2010 ዓም ማረፏ ከዱባይ የተሰራጨው መረጃ ያስረዳል ። ከአሌክሳንደርያ ግብጽ ወደ ህንድ በመጓዝ የተሳካ ህክምና ካደረገች በኋላ ከወራት በፊት ወደ አቡዳቢ ለህክምና ያቀናቸው ኢማን በ20 ያህል የህክምና ዶክተሮች አቡዳቢ ውስጥ በሚገኘው የቡርጅ ሆስፒታል ስትረዳ ቆይታለች ። የ 37 ዓመቷ ኢማን በግብጽ አሌክሳንደርያ ነዋሪ የነበረች ሲሆን ዱባይ ላይ ይሰጣት በነበረ ህክምና በጥሩ ሁኔታ የነበረች ቢሆንም ባጋጠማት የልብና የኩላሊት ክሽፈት ህይዎቷ ማለፉ ተሰምቷል ።

የአለማችን ግዙፍ እመቤት ተብላ የምትገመተው ኢማን ባሳለፍነው አመት የካቲት ወር 2009 የመጀመሪያ ሳምንት ዓም ከግብጽ አሌክሳንደርያ ለህክምና ወደ ህንድ ሞምባይ መወሰዷ ይታወሳል ። እመቤት ኢማንን ከአሌክሳንደርያ መኖሪያ ቤቷ ወደ አየር መንገድ ለማጓጓዝ ከመኖሪያ አፖርታ ማዋ በኮንቴነር መጫና ማውረጃ ክሬን ከመጠቀም ነበር ከቤቷ በማውረድ በካርጎ መጫኛ ትሬላ ወደ አውሮፕላን ጣቢያ መወሰዷ ብዙዎችን አስገራሞን መነጋገሪያ ሆኖ ማለፉ ይጠቃሳል። የአለማችን ወፍራሟን ሴት የእመቤት ኢማንን ማጓጓዝን ሌላው አነጋጋሪ ያደረገው ወደ ህንድ የተጓጓዘችበት ኤር ባስ አውሮፕላን የህዝብ ማመላለሻ አውሮፕላን ሳይሆን ለማጓጓዝ በልዩ ሁኔታ ተስተካክሎ የተዘጋጀ የእቃ መጫኛ አውሮፕላን መሆኑ እንደነበር አይዘነጋም ። ኢማን ወደ ህንድ ለህክምና ከተወሰደች በኋላም የተሻለ ህክምና ከማግኘት ባለፈ ውፍረቷን ለመቀነስ በተደረጋት ቀዶ ጥጋና ግማሽ ያህል ክብደት ቀንሳ እንደነበር ከህንድ ወደ ዱባይ በተደረገቅ ሽኝቷ ወቅት ዶክተሮች አሰወታውቀው ነበር።

በመጨረሻም ” የሰው ልጅ የሚወለድበትን እንጅ የሚሞትበ ትን አያውቅም! ” እንዲሉ የግብጽ አሌክሳንደርጋዋ የአለማችን ግዙፍ እመቤት መቀበሪያ ያልተጠበቀውና ያልተገመተው አረባዊት ኢምሬት አፈር ሆኗል: (

ነፍስ ይማር

ነቢዩ ሲራክ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar