www.maledatimes.com ኢቲቪ እስከ ዶቃ ማሰሪያው ድረስ ተነገረው! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ኢቲቪ እስከ ዶቃ ማሰሪያው ድረስ ተነገረው!

By   /   October 27, 2012  /   Comments Off on ኢቲቪ እስከ ዶቃ ማሰሪያው ድረስ ተነገረው!

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 57 Second

በመላው ሀገሪቱ ለአረፋ በዓል የተሰባሰቡ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ዛሬም ተቃውሟቸውን አሰሙ።

ሙስሊም ኢትዮጵያውያኑ መንግስት በሃይማኖታችን ጣልቃ መግባቱን ያቁም (ነጠላ ሰረዝ) ኮሚቴዎቻችን እና ሌሎች ንፁሐን ይፈቱ (ነጠላ ሰረዝ) ምርጫው ህገወጥ ነው (ነጣላ ሰረዝ) ግድያው ይቁም (አራት ነጥብ) እና በሌላ ነጠላ ሰረዝ ደግሞ ሌሎች በርካታ ጥያቄዎችን ከቢጫ ካርድ ጋር አንግበው ለመንግስት አበርክተውለታል!

በተለይ ኢቲቪ በገዛ ደጃፉ እስከ ዶቃ ማሰሪያው ድረስ ተነግሮታል። ኢቲቪ፤ በእኔ ቁጥር የመገመት ችሎታ የማይደፈሩ በርካታ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጮክ ብለው ልክ ልኩን ሲነግሩት ህንፃው በሀፍረት ሽምቅቅ ብሎ አለመስመጡ እንዴት ያለ ግንበኛ ቢሰራው ነው ብለን እንድንደነቅ አድርጎናል።

“ኢቲቪ አሸባሪ” “ኢቲቪ ውሸት አውሪ” “ኢቲቪ የማታፍሪ” “ኢቲቪ ነሽ ደባሪ” “ኢቲቪ ወዲያ ቅሪ” ብለው መፈክር አሰምተዋል። (በቅንፍም መፈክሩን በግጥም ለማድረግ በማሰብ የራሴን የፈጠራ መፈክሮች መጠቀሜን እገልፃለሁ!) ከቅንፍ ውጪ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሚለቁ ተጨማሪ ሰራተኞችን እንደምናይ እናስባለን! ከእንዲህ ያለ ተቃውሞ ጋር ያለ እንከን ከሰሩ የጤና እንከን አለ ማለት ብለንም እንጠረጥራለን!

በአዲስ መስመርም መንግስት በመላው ሀገሪቱ የተሰማውን ተቃውሞ እየሰማ እንዳልሰማ ከሆነ የገዢው ፓርቲ አባላት ራሳቸው የመንግስት ተቃዋሚ ናቸው ማለት ነው ብለን እናስባለን!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on October 27, 2012
  • By:
  • Last Modified: October 27, 2012 @ 10:29 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar