www.maledatimes.com ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከእስር ተለቀቀ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከእስር ተለቀቀ

By   /   October 15, 2017  /   Comments Off on ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከእስር ተለቀቀ

    Print       Email
0 0
Read Time:45 Second
ተመስገን ደሳለኝImage copyrightTARIKU DESSALEGN 

በትላንትናው እለት በሬዲዮ ዘገባችን አለመለቀቁን ዜናውን መስራታችን ይታወሳል ዛሬ ደግሞ መለቀቁን ወንድሙ ታሪኩ ደሣለኝ ዘግቧል ። ለወዳጅ ዘመዶቹ ደስታንም ፈጥሯል ።

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከእስር ተለቀቀ።

የተዛባ መረጃን በማሰራጨትና ሕዝብን በመንግሥት ላይ በማነሳሳት ተከሶ የ3 ዓመት እስር የተፈረደበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከእስር ቤት ወጥቷል፡፡

አርብ ዕለት የእስር ጊዜውን ጨርሶ እንደሚፈታ ሲጠበቅ የነበረው ተመስገን ደሳለኝ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ እንደማይፈታ ከዝዋይ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ተነግሮት ለተጨማሪ ቀን እስር ቤት ቆይቷል።

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከዚህ በፊት በአመክሮ ይፈታል ተብሎ ቢጠበቅም የተፈረደበትን የሦስት ዓመታት እስር አጠናቆ ነው የተፈታው።

ተመስገን በማረሚያ ቤት ቆይታው በወገቡና በአንድ ጆሮው ላይ የጤና መታወክና ስቃይ አጋጥሞት እንደነበር ቤተሰቦቹ ይናገራሉ።

ባለፈው ዓመት ኅዳር ወር ማብቂያ ላይ ተመስገን በዝዋይ ማረሚያ ቤት ውስጥ እንደሌለ ለቤተሰቦቹ ተነግሯቸው ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ገብተው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ከቀናት ፍለጋ በኋላ ግን እዚያው ማረሚያ ቤት እንዳለ ታውቋል።

ተመስገን በጋዜጣና በመፅሔት ባለቤትነትና ዋና አዘጋጅነት በቆየባቸው ጊዜያት መንግሥትን በሚተቹ ጽሁፎቹ ይታወቃል። በተደጋጋሚ ጊዜያት የህትመት ሥራዎቹ እንዲቋረጡ ተደርግዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on October 15, 2017
  • By:
  • Last Modified: October 15, 2017 @ 10:38 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar