www.maledatimes.com አቶ ያሬድ ጥበቡ (ጌታቸው ጀቤሳ) ስታዘበው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አቶ ያሬድ ጥበቡ (ጌታቸው ጀቤሳ) ስታዘበው

By   /   October 27, 2012  /   Comments Off on አቶ ያሬድ ጥበቡ (ጌታቸው ጀቤሳ) ስታዘበው

    Print       Email
0 0
Read Time:20 Minute, 58 Second

አቶ ያሬድ ጥበቡ (ጌታቸው ጀቤሳ) ስታዘበው

“ከአህያ የዋለች ጊደር ….ተምራ ትመጣለች” አበው እንዲሉ ዉሎውን ከቀጣፊ ጋር ያደረገ ምን ያህል ቀና ሰው ቢሆን ያዋዋዩን አጉል ምግባር ማንጸባረቁ የማይቀር ነገር ነው ።ይህን ያነሳሁት ያለ ምክንያት አይደለም ያኔ በሃገር ቤት እያለሁ በነጻ ጋዜጦች ላይ ሃሳቦቹነን አንብቤና በሠውየው ግርማ ሞገስ ጭምር እምነት አድሮብኝ ትልቅ ግምትና አክብሮት እሰጠው የነበረው የቀድሞው የኢህዲን (ብአዴን) መሪ የነበረው አቶ ያሬድ ጥበቡ (ጌታቸው ጀቤሳ) ካለው ጥልቅ ተሞክሮ ልምድና እውቀት አንፃር የማይመጥን እንደ ውሃ ላይ ኩበት የሚዋልል የረጋ አቋም እንደሌለው ስታዘበው የቆየሁ ቢሆንም እንደዚህ ሰሞን ጽሑፉ ግን የወረደና ከአንድ ገበሬ ማህበር ካድሬ ያነሰ አመለካከትና አቋም ይኖረዋል ብዬ ፈጽሞ ለመቀበል ቢያስቸግረኝም ግለሰቡ ግን ራሱን በዚህ ያህል ደረጃ ዝቅ አድረጎታል ።
አቶ ያሬድ ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ግዜ በአካል ያገኘሁት የዛሬ አራት አመት አካባቢ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገርና የጋራ ወዳጃችን ዶክተር አረጋዊ በርሔ መጽሐፉን ለማስመረቅና እግረ መንገዱንም ሃገራዊውን ትግል ለማጠናከር መጥቶ በነበረበት በዚያን ወቅት በአንድ አክቲቪስት የሕግ ምሁር ቢሮ ውስጥ ተሰባስበን በምንወያይበት ወቅት ዘግይቶ በመምጣት የተቀላቀለን አቶ ያሬድ ጥበቡ ማናችንም አስቀድመን ያላደረግነውንና ያላሰብንበትን የዶክተር አረጋዊን መምጣትና ዶክትሬቱን በማጠናቀቁ የተሰማውን ደስታ ገልጾ ይዞ የመጣውን ኬክ በመቁረስ በምርቃትና በጎ ምኞቱን በመግለጽ ያሰየው ወንድማዊ ፍቅርና ወገናዊ አክብሮት ካስደመመኝ በላይ በእለቱ በነበረው ውይይት ላይ በአቶ ያሬድ ይቀርብ የነበረው ፖቲካዊ ትንተና ስለ አገዛዙ ባህሪና ስለ መሪዎቹ ስብዕና በአጠቃላይ ይህ ቀረሽ የማይባልና ጋዜጣ ላይ የማውቀው ሰው ከጠበኩትም በላይ የበሰለ ሆኖ በማግኘቴ በጣም ከመደንቄ የተነሳ አወይ ያ ትውልድ በጎ ሲሉት መጥፎ ደግ ሲሉት ክፉ ሆኖ ጭራው የማይጨበጥ ግራ እንደተጋባና ግራ እንዳጋባን የጎጥ የአንጃና የጥቅም መደቦች ተከፋፍሎ ዋና ተጋዮችን ስደት እየበላቸው ከዚህ ሁሉ የፖለቲካ ገበያ የኔ ትውልድ ምን ይማር ይሆን የሚል ሃሳብ በግዜው ጭሮብኝ ነበር።
የአቶ ያሬድን ስብዕና እየካብክ ናድከው አትበሉኝና ግለሰቡ ሃገር ቤት በሚታተም ዕንቁ መጽሔት ላይ የጻፈውን ከዘ ሐበሻ ድህረ ገጽ ላይ በስካነር ኮፒ ተደርጎ የወጣውን ጽሑፍ ሳነብ በወጣትነቱ በረሃ የተንከራተተው በአቋም ልዩነት ለስደት የበቃው ያሬድ ጥበቡ የሰፈር አሮጊቶች እንኳ ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም ብለው ያጣጣሉት የሃይለማርያምን ሹመት አወዳድሶና አንቆለጻጽሶ የሚካሄደው የስልጣን ሽግግር ታሪካዊነትንና የወደፊቷን ኢትዮጽያ ወደ ተሻለ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ተደርጎ በአቶ ያሬድ የቀረበው ውሃ የማይቋጥር ትንተና በእኔ አቅም ግለሰቡን አላዋቂ ለማለት የሚያስችል አቅም ባይኖረኝም የጽሁፉ ጽንሰ ሃሳብ ከመነሻ እስከ መድረሻው የውሸት አባት የሆነው በረከት ስሞን ጽፎ ያሬድ በሚል ስም ያወጣው የሚል የዋህ ግምት የሚያሰነዝር አለያም የባልቴቶች ተረት ተረት የሚሰኝ አይነት ነው የሆነብኝ።
የአቶ ያሬድን ታሪክ ከራሱም አንደበትና ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች ለመረዳት እንደቻልኩት እናት ድርጅቱን ከአሲንባ ከድቶ የያኔውን ተጋድሎ ሐርነት ትግራይ (ተሐት) የዛሬው ሕወሐት ጉያ ገብቶ የሃገራችንን ዳር ድንበር ለማስከበር ከገንጣይ አስገንጣይ የወንበዴ መንጋ ጋር ለመተናነቅ የተመመውን ህዝባዊ ሰራዊት በመውጋት የሻብያና የወያኔ ጨለምተኛ ቡድን ለስልጣን መብቃት ያሬድና ጓዶቹ
2
2
በትግሬው ነጻ አውጪ ሸበጥ ስር ተንበርክከው የፈጸሙት ታሪካዊ ስህተት ሂሳቡ ሳይወራረድ በምርጫ ዘጠና ሰባት የቅንጅት የሰሜን አሜሪካ አመራር አባል በመሆን አቶ ያሬድ ያደረገው ተሳትፎ ያለ ውጤት በትርምስና በሁከት ተበትኖ የህዝብን ተስፋ ያጨለሙት አንሶ ሠው በላው መለስ ዜናዊ ያስፈጃቸው ጨቅላ ሕጻናትን ጨምሮ ያለቁት ወገኖቻችን ትዝታው ባልጠፋበት ቁስላችን ፍትህና ርዕትህ አግኝቶ ባልሻረበት ሁኔታ ላይ አቶ ያሬድ እነዚህን ግፉዐን ዘንግቶ ያለበትን ሞራላዊ ሃለፊነት ረስቶት ለመለስ አምርሮ ለማልቀስ የአንዲት መበለት ደረት መምታት ምክንያት ሆነኝ ሲል ያቀረበው ሃተታ አሳፋሪነት የሚያጠናክረው ግለሰቡ ይህን ሲል በመለስ ዜናዊ ትዕዛዝ የእንቦቃቅላ ደረት በጥይት የተነደለው አሳዝኖት አልነበረም ማለት ነው ወይስ ሌላ ? ለኔ እንደገባኝ የአቶ ያሬድ አዛኝ ቅቤ አንጓችነት ምንጩ ለመለስ ካለው ፍቅር አለያም ከሰባዊነት የመነጨ ሳይሆን በዲያስፖራው ፖለቲካ ውስጥ ከቅንጅት መፈረካከስ በኋላ በአቋሙ መዋዠቅ ተቀባይነት አጥቶ በመገፋቱ በተለያዩ ድርጅት ውስጥ ያሉ ጓዶቹን ለማብሸቅና ዲያስፖራውን ለማናደድ ግለሰቡ የጨዋታውን መስመር አልፎ የፈጸመው የፖለቲካ ዝሙት ታረኩን የሚያቆሽሽ ብቻ ሳይሆን በወዲያኛውም ሰፈር ተቀባይነት የማይስገኝለት ከንቱ ድካም ከመሆን የዘለለ አንዳችም ትርፍ የማያስገኝ የሞራልና የስብዕና ክስረት ነው።
በመሰረቱ አቶ ያሬድ ሁኔታዎች መለወጥ ሲጀምሩ እንደለመደው መልሶ እንባዬን መልሱልኝ ላለማለቱ ማረጋገጫ ባይኖረንም እንደ ቀደመ ባህሪው ግን በረከት ስምዖን ናፈቀኝ የአዲሱ ለገሰ ሳቁ ትዝ አለኝ ያለው የሚታወስ ሲሆን ወዲያው ብዙም ወራት ሳይቆይ ናፍቆቴን መልሱልኝ ሲል ተሰማ አክሎም የበረከት መጽሃፍ በሃሰት የተበረዘ መሆኑን በመግለጽ ለውሸታምነቱ ወደር የማይገኝለትን እውነት መናገር ለዛ የአሞራ አፉ አለርጂ የሆነበትን በዚህም ምግባሩ ህጻን አወቂ የሚያውቀውን የወያኔውን ቃል አቀባይ አቶ ያሬድ እንደ አዲስ ነገር ለቀባሪው ሊያረዳ ሞክሯል ፤ ሰውዬው በዚህም ባበቃ መልካም ነበር የመለስን ሁኔታ አስመልክቶ ኢሳት አስተማማኝ ምንጮቹን በመጥቀስ መለስ መሞቱን ያቀረበውን ዘገባ ለማስተባበል በረከት ስምዖን ለአዲሱ አመት ዋዜማ ስራ ይጀምራል ሲል የሰጠውን ጋዜጣዊ መግለጫ በመመርኮዝ አስተያየቱን የተጠየቀው አቶ ያሬድ የኢሳትን ዘገባ ለማኮሰስ የምንጮቹን ማንነት አጣርቶ ውሳኔ ላይ ከመድረስ ይልቅ በረከት ያለውን ለመቀበል ያቀረበው ምክንያት የበረከትን አይኖች አውቃቸዋለሁ የሚል የመጽሃፍ ገላጭ የደብተራ መልስ ሲሰጥ በአግራሞት ታዝቤዋለሁ።
ካፈርኩ አይመልሰኝ የሆነው የያሬድ ሙልጭልጭ አመለካከትና አቋም አልባነት ካንጸባረቀበት ከዚህ መጽሄት ጽሁፍ የመለስ ህልም ብሎ ሊተነትነው የፈለገው ነገር ፈጽሞ ሊገባኝ ያልቻለና ግራ የሆነብኝ በለጋ እድሜው በረሃ ለበርሃ የተንከራተተለት ድርጅት ራዕይ የሌለው የተነሳለትን አላማ የሳተ ነው ብሎ የተለየውን ይህን ህልም አልባ ስርዓት ለማስወገድ ከቅንጅት እስከ ኦነግ ሁሉን የሞከረ የስደት ፖለቲከኛ ጓደኞቹ ምኒስትርና አንባሰደር ሆነው አለማቸውን ሲቀጩ ጊዜውን ከአንዱ ጥግ ወደሌላው በሚል ያሰለፈው በእውነቱ ሊቆጨው ይገባል ለምን ቢባል አቶ ያሬድ መለስ በጎ ሕልም አለው ብሎ ያምን ከነበረ የበረከት ሳቅ የአዲሱ ለገሰ ጨዋታ ትዝታ ከሚሆንበት ለምን የማምሻ እድሜውን በስደት ለመግፋት እንደተገደደ ሳስበው ሳስበው መልስ የለኝም። የቀድሞ የትግል ጓዶቹ ባለሳቆቹና ህልመኞቹ ኢትዮጽያ በመዳፋቸው ውስጥ እንዳለች ወፍ አድራጊና ፈጣሪ አሳሪና ፈቺ ሻሚና ሻሪ ፍርድም እውነትም ሃይልም እነሱና እነሱ ብቻ በሆኑበት ሃገር ለያሬድ ቦታ ጠፍቶ ነበር እንዴ ፤ እንድ አድርጎኛል።
ያ በወጣትነቴ ጋዜጣ ላይ አይቼ ተስፋ እጥልበት የነበረ ሰው እንዲህ ሲምታታ ሳየ በጣም አዝኛለሁ። አቶ ያሬድን መነሻ ስላለኝ እሱ ላይ ብዙ አልኩኝ እንጂ በደምሳሳው የያሬድ ዘመን ትውልዶች መለስ ዜናዊ በረከት ስምዖን የደርጉ ግስላ የኢሃፓው ፋኖ የወያኔው ቀበሮ በአጠቃላይ የኔ የዚህ ዘመን
3
3
ትውልድ ካለፈው ትውልድ ከተማረው በጎ ነገር ይልቅ የቀሰመው አሉታዊ ነገር ይበዛዋል።እሱም ቡድናዊነት ዘረኝነት አንጀኝነት ኢዲሞክራሲያዊነትና አቋም አልባነት ጠቅሶ ማለፉ ተገቢ ይመስለኛል። በእርግጥ ከዛ ካለፈ ትውልድ ውስጥ በቅንነትና በታማኝነት እስከመጨረሻው የፀኑ ለዐርያና ተምሳሌትነት የሚጠቀሱ አያሌ ወገኖች ቢኖሩም አሉታዊያኑ ግን ደምቀው እንደ አቶ ያሬድ ያሉት በመታየታቸው የትውልዱን በጎ ታሪክ በማወየብ አስተዋፅዖ አድርጓል። እዚህ ላይ አቶ ያሬድን ልብ እንዲለው የምመክረው በተናጥል የሁለታችንም ልባዊ ወዳጅ የነበረውና በሞት የተለየን ሙልጌታ ሃይሉ ሁለታችንም በመቃብሩ ላይ አምርረን ያለቀስንለት እስከመጨረሻው ከአቋሙ ስንዝር ሳይነቃነቅ ጓደኝነት ጥቅም ምቾትና ሌላም ሌላም ነገር ሳያታልለው እስከሞት ለሚያምንበት አቋም የታመነ በመሆኑ እንደነበር ከኔ ይልቅ አቶ ያሬድ ጠንቅቆ የሚያውቅ በመሆኑ ምንም በእድሜ የአባትና ልጅ ያህል ብንራራቅም በድፍረት ግን አቶ ያሬድ ወጥና ጽኑ አቋም እንዲኖርህ እመክራለሁ።
ለማጠቃለለ ምንም በአቶ ያሬድ ላይ የራሴን ግንድ የሚያህል ሃጥያት ሳላጠራ ወቀሳና ትችት ብሰነዝርም አሁንም የታናሽነት ጥልቅ አክብሮት እንዳለኝ መግለጽ እወዳለሁ። ሌላው ሳልገልጽ የማላልፈው አቶ ያሬድ ስለ ሃይማኖቱ ተጠይቆ የሰጠው መልስና ሌሎችም የሱ ዘመን ሰዎች ያየሁትና ያደመጥኩት ከዛ ሁሉ አበሳና መከራ በኋላ እንኳ የእግዚያብሄርን ሕልውና ለመቀበል መቸገራቸውንና ሃይማኖት አልባ ጉግማንጉግ መሆናቸውን ሳስብ ለበረከት መቀላመድ ለመለስ ጨካኝነት ለያሬድ መዋዠቅ አንዱ ምክንያት የመንፈሳዊ ህይወት ድርቀት የፈጠረው ምክንያት ይሆን ወይ እንድል አድርጎኛል ፤ ሃይማኖት የሞራል ልጓም መሆኑን ሳይንሳዊው አለም እንኳ የተቀበለው ሃቅ እንደመሆኑ የማይዳሰሰውና የማይጨበጠው ተምኔታዊው የማርክሲስቱ አስተምህሮ ካስከተለብን የማንነት ቀውስና የባህል ጉዳት ባሻገር ዛሬም ድረስ ከማጡ ልንወጣ ያልቻልነው ምድራዊያን ፈላስፎቹን አምነንና ተቀብለን ዘላለማዊውን አምላክ በመካዳችን በመሆኑ ፤ ወደ ልቦናችን ተመልሰን መቅሰፍትና መዓቱን እንዲያበርድልን ሃገራችንንም ከትርምስ ክእርስ በእርስ ግጭት አርቆ ወደ ተሻለ ምዕራፍ እንዲያሸጋግርልን ሁላችንም ከልቦናችን ላይ የተሰካውን የጥላቻ የሐሰተኝነት የመለያየት የክፋትና የዘረኝነት አሽክላ ነቅለን ፤ የፍቅር የእምነትና የበጎነት አፀድ እንተክል ዘንድ እግዚያብሄር ይርዳን።አሜን!!!

(ምንሊክ ሳልሳዊ)

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on October 27, 2012
  • By:
  • Last Modified: October 27, 2012 @ 10:48 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar