ጋዜጠኛ እና ገጣሚ ሰለሞን ደሬሳ ለእረጅም ጊዜ በምንሶታ ኑሮውን አድርጎ በህክምና ባለሙያዎች ሲረዳ ቆይቶ ህይወቱ ማለፉን ከቅርብ ወዳጃችን ከቴአትር ባለሙያ ከእጩ ዶ/ር ሱራፌል ወንድሙ ለመረዳት ችለናል።
መልካም እና ቀና የነበረው ሰለሞን ደሬሳ በበሳሉ እና ጠንካራ ፅሁፎቹ የሚታወቅ የነበረ ሲሆን በፈረንሳይኛ፣እንግሊዝኛ እና አማርኛ ፅሁፎቹ ጥሩ አድርጎ የሚፅፍ እንደነበር ዘገባዎች ይጠቁማሉ ።
ሰለሞን ደሬሳ በወለጋ አካባቢ የተወለደ ሲሆን በ80 አመቱ ህይወቱ ማለፉን የደረሰን ሪፖርት ያመለክታል።
ስርአተ ቀብሩ በቅዳሜ እለት እንደሚከናወንም ጥንቅሩ ያመላክታል ።
በበሳል እና ጠንካራ ፅሁፎቹ የሚታወቀው ሰለሞን ደሬሳ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን በማለዳ ታይምሰ ዝግጅት ክፍል እናቀርባለን
ኒርቫና
እንዲህ ነው መነጠል
እንደዚህ ነው ማለፍ
ፀዳል ተጎናፅፎ
አክሊል ተከናንቦ …
እያበሩ መሄድ
እየበሩ መምጣት …
እንዲህ ነው ሳምሳራን
ሰንክሳሩን መስበር
ማለፍ ላለማለፍ
ላለማረፍ ማረፍ
ስለ እውነት መንቃት
በዓለም ላይ መብቃት
ዕውነት፣ ትሁት መሆን
መጠየቅ ማስተንተን …
መፍጠርና ማድነቅ
ቋሚን አለማምለክ …
ገላ ሰጋን መጣል
ሰውነትን ማንሳት
የሰው “ዚነት” ሆኖ ካ’ለም “ናዲር” መራቅ
መጓዝ በጥሞና ፀጥ ብሎ መሳቅ …
ባ’ማዲየስ ሞዛርት፣ በቤቶቨን ፈረስ
በስትራቭንስኪ፣ በባህ በብራህምስ
በሾፐን በሄንድል በቪቫልዲ መፍሰስ …
በሜሪ በአስናቅች በጂጂ ሙዚቃ
በባቲ ዜማ ግርፍ ባዝማሪዎች ጭራ
በወለሎ ቅኝት በድቤ ዝየራ …
በእስክንድር በገብሬ፣ በተስፋዬ ስብሃት
ካገርህ ተድረህ አገርክን ፈታሃት …
ከጩታ አዲሳባ፣ አልፎም እስከ ፓሪስ
ከውቤ በረሃ ቃጠሎ ካዛንቺስ
እስከ አምባ ቆራ ነጭዋ ምኒያፖሊስ …
ሰው ሆነህ ተገልጠህ
ሰው ሆነህ ተነጠልህ
ሰው ሆነህ ተመለስህ …
Average Rating