www.maledatimes.com የዘሪቱ ከበደ በመደረከ ላይ ልቅ የሆነ አለባበሷ ብዙ ኢትዮጵያኖችን አስቆጣ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

የዘሪቱ ከበደ በመደረከ ላይ ልቅ የሆነ አለባበሷ ብዙ ኢትዮጵያኖችን አስቆጣ

By   /   November 5, 2017  /   Comments Off on የዘሪቱ ከበደ በመደረከ ላይ ልቅ የሆነ አለባበሷ ብዙ ኢትዮጵያኖችን አስቆጣ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 24 Second


በድምጻዊቷ ላይ ቅሬታ የሚያቀርቡ ሰዎች “መድረክ ለይ ለብሳው የወጣችው ለብስ በኢትዮጵያን ማህበረሰብ ላይ ቁጣን የሚቀሰቅስ ከመሆኑም በላይ ከብርን ይነካል ሲሉ ቢደመጡም ዘሪቱ ግን ልብሱን ለማስተዋወቅ ተብሎ እንጂ ሆን ተብሎ ለመድረክ ተዘጋጅቼ የለበስኩት አይደለም ብላለች::

ባሳለፍነው ሳምንት በአዲስ አበባ በተደረገው ጊዜ ኮንሰርት ቁጥር 2 ላይ የወቅቱን የሃገራችንን ሁኔታ በማስመልከት ዘፈኗን አቋርጣ “አማራ ፣ ኦሮሞ ጉራጌ አይታየኝም ለኔ የሚታየኝ ሰው ነው” በማለት ዘረኝነትን በተቃወመችበት መድረክ ላይ በፎቶግራፉ ላይ እንደሚታየው የሁለት ጡቶቿን በጡት መሸፈኛ በማድረግ ጡት ማስያዥዋን በማሳየትና ደረቷን በመክፈት ረዥም ቀሚስ ለብሳ መድረኩን ተቆጣጥራው ነበር::

ድምፃዊት ዘሪቱ፣ ይህንን የሴትነቷን ክብር የሚያሳይ ድርጊት በማሳየቷ አንዳንዶች “የእድገታችን ለውጥ ነው ፣ መብቷ ነው ቢሉም ሌሎች ደግሞ “የዘሪቱ ድርጊት ባህርይን ፣ ስነ ምግባርን እና ግብረ ገብነትን የማይለዩ ወጣቶች ላይ ከባህላችን አንፃር የሚያመጣውን አሉታዊ ተፅእኖ አላዩትም ሲሉ የዘሪቱ ደጋፊዎችን ይቃወማሉ

የሀገራችን እሴቶች እያሉ የሰዎችን ለማስተዋወቅ እንዲህ አላማ ለሌለው ነገር ጡት ማስያዣን በወንዶች በአደባባይ መታየት ከማይገባችው አካላት ወይንም ከሰውነት ክፍል እንዲህ ተጋልጦ መውጣት ክብረ ነክ ነው የሚሉት እነዚሁ አስተያየት ሰጪዎች ዘሪቱ ተሳስታለች ሲሉ ወቅሰዋል::

ዘሪቱ በኩሏ ትናንት በፌስቡክ ገጿ ላይ በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ በመስጠት ይቅርታ እጠይቃለሁ ብላለች::

የዘሪቱ መግለጫ እንደሚከተለው ይነበባል
“ይህን መልዕክት ለመጻፍ የተነሳሁበትና ሁላችሁንም ይቅርታ የምጠይቅበት ጉዳይ የማፍርበትና በብዙ ግለ ወቀሳ ውስጥ ያለፍኩበት ነው። በአምላኬ ፊት ተናዝዤ ንስሐ የገባሁበት ቢሆንም፤ በአደባባይ የበደልኩት በደል ነውና በአደባባይ ልናዘዝ እንደሚገባኝ አምኛለሁ።
ከታች የምትመለከቱት አለባበስ ከቀናት በፊት በተካሄደው ጊዜ ኮንሠርት 2 ላይ የለበስኩት ነበር። ይህን ልብስ ከመልበሴ ጀርባ የነበረው intention የዋህና ንጹሕ የነበረ ቢሆንም፤ ልብሱን ለማገዝ የተጠቀምነው የውስጥ ልብስ material በልብሱ አካልነት ሳይሆን በውስጥ ልብስነቱ በመጋለጡ ነውር እንዲሆንብኝ ሆኗል፤ በዚህም ልወሰድ የሚገባኝን ጥንቃቄ ባለመውሰዴ አዝኛለሁ።
እግዚአብሔርን ከምትፈራና ራሷን ከምታከብር ሴት የማይጠበቅ ተግባር ፈጽሚያለሁ።
ላዘናችሁብኝ ሁሉ በብዙ ትህትና ይቅርታ እጠይቃለሁ::
/እንዲሁም ሴቶች በጨዋነትና ራሰን በመግዛት ተገቢ የሆነ ልበስ ይልበሱ … እግዚአብሔርን እናመልካለን የሚሉ ሴቶች ሊያደርጉ እንደሚገባ በመልካም ተግባር ይዋቡ። (1 ጢሞ. 2: 9-10) /”

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar