በኢትዮጵያዊቷ የ28 አመት ወጣት ፀሎት ዘውዴ የተከፈተው ቡና ታይም (ጊዜ) ከፍተኛ ህዝብ በሚገኝበት የችካጎ ከተማ በሊንከን ፓርክ ዙሪያ ተከፈተ ፣ ይህ አይነቱ የንግድ ተቋም ለሃበሻው ማህበረሰብ የሚያበረታታ ነው ።
እንደ ፀሎት አገላለጽ ከሆነ በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች የሚመረተውን ቡና በአለም አቀፍ ደረጃ ጥራት ያለው ከመሆኑ ባሻገር ፣ እውቅናው ከፍ ያለ ቢሆንም የሃገራችን ገበሬዎች ከሚያመርቱት ምርት ጋር ምንም አይነት ጥቅም የላቸውም ስለዚህ ይህንን ምርታቸውን እኛም ለማገዝ ስንል ከምንሸጠው ቡና ላአይ የተወሰነ ፐርሰንት ለሃገራችን ገበሬዎች የሚያግዝ አላማ ላይ የተመረኮዘ የቡና መሸጫ መደብር ነው ትለናለች ።
እንደ እነ ስታር ባክስ ያሉት ትልልቅ ፍራንቻይዝ ካምፓኒዎች ከሃገራችን የሚያመጡትን ቡና እየሸጡ ምንም አይነት ክፍያ ለሃገራችን እንደማይሰጡ ይታወቃል ፣ ይህንን ደግሞ በስታር ባክስ በሰራሁበት ወቅት ለመረዳት ችያለሁ ፣ስለዚህ ለምን የሃገሬ ገበሬ አይከፈለውም የሚለው ደግሞ ከፍተኛ የሆነ ስሜት እውስጤ ነበር ሆኖም አለመከፈላⶨው ብቻም አይደለም ምርቶቻችውን በደንብ አለማስተዋወቃቸው እራሱ ያማል ፣ ትርለናለች ጸሎት ።
ለእንደ እነ ኬንያ እና ብራዚል ሜክሲኮ ላሉ ቡና አምራች አገሮች እየተከፈለ ኢትዮጵያን ገበሬዎችስ እኛ ለምን አናግዛቸውም የምትለው ፀሎት ሁለት የተለያዩ የቡና አሰራር የትምምህርት እድል በማግኘት ሰርተፊኬቷን ይዛለች ።
የይርጋ ጨፌ እና የሲዳማ ቡናን በጥራት ታስተናግድዎታለች ፀሎት ዘውዴ
በችካጎና አካባቢዋ ያሉ የንግድ ማህበረሰብ በጣምም ጥቂት እንደመሆናቸውም መጠን ብዙሃኑን ያሰባስባል እንዲህ አይነቱ የመገናኛ መድረክ መከፈቱ ሲሉ አንዳንድ አስተያየት ሰችዎች ለማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ገልጸዋል የቡና መሸጫ መደብሩን ለምትፈልጉ ማናኛውም ኢትዮጵያኖች 1552 Fullerton Ave Chicago il 60614 ሲሆን ይህችን ወጣት በአለን አቅም ያላትን ምርቶች በመግዛት እና የሃገራችንን ገበሬውች ለመደገፍ የሚያበቃ ስራ እንስራ ።
Average Rating