የደርግ መኮንን መቶ አለቃ እሸቱ በዘ ሄግ የፍርድ ከዜግነቱ ሆላንዳዊነቱን ከቀየረ በሁዋላ የሆላንድ መንግስት ከ፳፮ አመታት በፊት በተከሰተ ወንጀል እንደከሰሰው ተገልጿል ፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት የማለዳ ሬዲዮ በwghc98.3 የአየር ሰአታቸው ልይ በዜና መልክ ያቀረቡት ይህ ሮፖርት እንደሚያመለክተው ከሆነ ፣ መቶ አለቃ እሸቱ የተሳሳተ ሰው ነው የያዛችሁት በማለት ለመርማሪ ፖሊሶቹ ገልጾ እንደነበር የማለዳ ታይምስ ተባባሪ ሪፖርተር ፣ከሆላድ መዘገቡን ገልጸናል።
በአሁኑ ሰአትም ሪፖርተራችን እንደገለጸው ከሆነ መቶ አለቃ እሸቱ አለሙ በዚህ በሚመጣው ሳምንት መጀምሪያ ማክሰኞ በፍርድ ቤት ቃሉን የሚሰጥ ሲሆን ፰ የሚሆኑ ኢትዮጵያኖች ምስክርነት ቃላቸውን ለመስጠት ከዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ወደ ሆላንድ እንደተጓዙ እና ወጭው በሆላንድ መንግስት የታገዘ መሆኑን መረጃውን ለማግኘት ችለናል።
ላለፉት ሁለት አመታት በእስር ቤት ውስጥ መከራውን ሲያይ የነበረው መቶ አለቃ እሸቱ አለሙ በጎጃም ክልል ውስጥ በተፈጸመው የጅምላ ግድያ ወንጀል ተከሶ ፍርድ በዘሄግ (አለም አቀፉ ፍርድ ቤት እየጠበቀ መሆኑን ተጠቁⶁል )
በደርግ መንግስት ዘመን ተከሰው እስር ቤት ውስጥ ዘመናቸውን ያሳለፉት ኢትዮጵያኖች ከዘመናት በኋላ ከእስር በይቅርታ መለቀቃቸው ይታወሳል አሁን ግን የተቀሩት እና አገር ለቀው የተፉት የደርግ መኮንኖች እየታደኑ በመታሰር ላይ ናቸው ፣ከጥቂት አመታት በፊትም አንድ ነፍሰ ገዳይ ከኮልራዶ ስቴት ወደ ኢትዮጵያ ለእስር እንደ ተወሰደ መረጃዎች ይጠቁማሉ ።
ማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል የእናንተው የተጣራ መረጃ መድረክ !!
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating