56 የግንቦት7 እና 41 የኦነግ እስረኞች

ከእነዚህም በተጨማሪ ውሳኔ አግኝተው በጎንደር እና በጭልጋ ማረሚያ ቤቶች የነበሩ 55 ፍርደኞች በይቅርታ ከእስር እንዲለቀቁ ተወስኗል።

የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ የጎንደር ቋሚ ምድብ አስተባባሪ አቶ ብስራት አበራ ክሳቸው የተቋረጠውና በይቅርታ የሚፈቱት ተጠርጣሪዎች እና ፍርደኞች ባለፉት ጊዜያት በሽብር፣ ሁከትና አመፅ ተሳትፎ ተጠርጥረው እና ተከሰው የነበሩ ናቸው።

በክስ ሂደት ላይም ያሉ አብዛኛዎቹ በዋስትና መብት ላይ ያሉ ሲሆን፥ ተጠርተው የተሃድሶ ስልጠና ከወሰዱ በኋላ ከክሳቸው ነፃ ይሆናሉ ብለዋል።

በማረሚያ ቤት የሚገኙ ፍርደኞች እና ተጠርጣሪዎች ከነገ ጀምሮ እንደሚለቀቁ የገለፁት አቶ ብስራት፥ እስካሁንም አምስት ፍርደኞች ተገቢውን የይቅርታ ሂደት አልፈው መለቀቃቸውን አስታውቀዋል።