www.maledatimes.com የታሪክ አረዳድ፡ ለመሰረታዊ ግንዛቤ (በግደይ ገብኪዳን ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የታሪክ አረዳድ፡ ለመሰረታዊ ግንዛቤ (በግደይ ገብኪዳን )

By   /   October 28, 2012  /   Comments Off on የታሪክ አረዳድ፡ ለመሰረታዊ ግንዛቤ (በግደይ ገብኪዳን )

    Print       Email
0 0
Read Time:13 Minute, 28 Second

“አለም የምትገዛው ከትእየቱ በስተጀርባ ያለውን የማያውቁ ሰዎች እንደሚያስቡት ሳይሆን በጣም በተለዩ ግለሰቦች ነው፡፡”

ቤንጃሚን ዲዝራኤሊ
ከላይ እንደተፃፈው ቤንጃሚን ዲዝራኤሊ የዩናይትድ ኪንግዶም ሁለት ግዜ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበረና ታዋቂ ፀሃፊም የሆነው ሰው እንደሚነግረን ዓለም የምትገዛው ተራው ሰው እንደሚያስበው የስልጣን ወንበር በተቆናጠጡት አይደለም፡፡ ዓለም የምትገዛው እነሱን በሚቆጣጠሩትና ያገዛዝ ፍልስፍና ወይም ርእዮተ አለሙን በሚቀርፁ ከትእይንቱ በስተጀርባ ባሉ ሰዎች ነው፡፡
ታሪክን በሁለት መንገድ መገንዘብ እንችላለን፡
አንድ ታሪክ የአጋጣሚ ክስተቶች ውጤት ነው የሚለው፣ ወይም በኦፊሻል ተቀባይነት ያለው የታሪካዊ ክስተቶች አረዳድ ወይም፣
ሁለት ታሪክ የተቀነባበረና የታሰበበት ክንውኖች ውጤት ነው የሚለው የሴራዊ ታሪክ ትንተና መመልከት ይቻላል፡፡
የታሪካዊ ክስተት እውነታ የሚታወቀው፡
·         አሸናፊዎች በሚፅፉት ታሪክ፣
·         ተቀባይነት ወይም የክብር ቦታ ያላቸው እንደዲዝራኤሊ ያሉ ሰዎች በሚናገሩት፣
·         ወይም የሚስጥር ማህበራት አባሎች ስለታሪካቸው በሚፅፉት ለምሳሌ እንደነ ማንሊ ፒ. ሃል፣ እንደነ አልበርት ማኬ የመሳሰሉት በሚፅፉት ብቻ አይደለም፡፡
ተቀባይነት የሌላቸውና የሚናገሩት ለህዝብ እንዳይደርስ የሚደረግ፡
·         አጋላጭ የታሪክ ተመራማሪዎች የሚፅፉትም አለ፡፡
በነዚህ ሁለት አይነት ፀሃፊዎች ማለትም በሚስጥር ማህበር አባል ሁነው ታሪኩን በሚፅፉትና በአጋላጮቹ መሃከል ያለው ልዩነት ስለሚስጥር ማህበሩ ድብቅ አምልኮ ምንነት ላይ ነው፡፡ እዚህም ላይ ቢሆን የሚገርመው ስለምንነቱ ልዩነት የላቸውም፡፡ ሁለቱም የሴጣን አምልኮ መሆኑን ይፅፋሉ፡፡ አባሎቹ ሲፅፉት ጥሩ አድርገው ሲሆን ተቃዋሚዎቹ ሲፅፉት ደሞ ክፉና አደገኛ ቀኖናውን በማጋለጥ ነው፡፡

በዚህ ብሎግ የሚስጥር ማህበራቱን ስራ በፅሁፍ ብቻ ከመንገር በራሳቸው በየቦታውና በየህትመቱ በሚለቋቸው ምስሎች፣ ቅርፆች፣ እና የምልክት ንግግሮች መሰሪ ስራቸውን እጅ ከፈንጅ ይዤ አቀርብላችኋለው፡፡

በታሪክ ሂደት የሴራዊ አተረጓጎምን እጅግ የሚጠራጠሩ የሚከተለውን ኬነዲን ያስገደለውን ንግሩን ማዳመጥ ይችላሉ፡
የንግግሩ ፍቺ፡
ክቡራን፣ ሚስጥራዊነት የሚለው ቃል በራሱ ለነፃና ግልፅ ማህበረሰብ አስፀያፊ ነው፡፡ እኛ ደሞ እንደ ህብረተሰብ ካወቃቀራችንም ከታሪካችንም የሚስጥር ማህበራትን፣ የሚስጥር ቃለ መሃላን እና ሚስጥራዊ ስነ ስርአቶችን የምንቃወም ነን፡፡ ሆኖም ግን በዓለም ዙርያ በጠጣር (በማይለወጥ) እና ግዙፍ ሴራ ተቃውሞ ገጥሞናል፡፡ በዋናነት ተፅእኖ አድማሱን ለማስፋት የሰው ንብረትን በመዝረፍ፣ በወረራ ከመያዝ ይልቅ ሰርጎ በመግባት፣ ከምርጫ ይልቅ በማታለል፣ ከነፃነት ይልቅ በማስፈራራት ላይ የተሞረኮዘ፡፡ ሰፊ ቁሳዊና ሰብአዊ ሃብቶችን በመመልመል ጥብቅና አዋጭ የሆነ ወታደራዊ፣ ዲፕሎማስያዊ፣ ስለላ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሳይንሳዊ እና ፖለቲካዊ ስራዎችን ያካተተ ማሽን በመገንባት ያሰማራ ስርአት ነው፡፡ ስራዎቹ ድብቅ እንጂ የሚታተሙ አይደሉም፣ ስህተቶቹ ይቀበራሉ እንጂ ርእሰ ዜና አይሆኑም፣ ተቃዋሚዎቹ ዝም እንዲሉ ይደረጋል እንጂ አይደገፉም፣ ምንም አይነት ወጪ ከማውጣት አይቆጠብም፣ የትኛውም ሚስጥርም አይወጣም፡፡ ለዚህ ነው የአቴንሱ ህግ አውጪ የትኛውም ዜጋ ከአወዛጋቢ ጉዳይ እራሱን የሚያገል ጥፋተኛ እንዲሀን ህግ ያወጣው፡፡ ከባድ ለሆነው የአሜሪካን ህዝብ የማሳወቅና የማንቃት ስራ ድጋፋችሁን እየጠየቅሁኝ ነው፡፡ ከናተ ድጋፍ ጋር ሰው ለተወለደበት ዓላማ፡ ነፃ እና እራሱን የቻለ እንዲሆን እንደምናደርግ ልበ ሙሉ ነኝ፡፡
የኬነዲ አገዳደልም ያጋጣሚ ነው ለሚሉ የታችኛውል ፊልም ማየት ይችላሉ፡
ኬነዲ በህዳር 22፣ 1963 ዳላስ ውስጥ በጥይት ተመትቶ ሞተ፡፡ the Zapruder film – ተሸሽጎ የነበረ ፊልም በግልፅ እንደሚያሳየው፡– መጀመርያ ኬነዲ በክፍት መኪና እየሄደ ሳለ ከላይ የመጣና ያልታወቀ ጥይት ተመትቶ ከቀኝ ወደ ግራ ሲያዘነብል እና ቀጥሎ ሳትደናገጥ ሚስቱ ዞር ብላ ስታየውና ስትደግፈው -ቀጥሎ ከፊት በኩል የኬነዲ ሹፌር በቀኝ እጁ መሪውን á‹­á‹ž በግራ እጁ ሽጉጥ አውጥቶ በቀኝ ትከሻው በኩል አድርጎ ሲተኩስበት እና ኬነዲም ከግራ ወደ ቀኝ ሲያዘነብልና ባለቤቱ ደንግጣ እየበረረ ያለውን መኪና ጥላ ስትወጣ ያሳያል፡፡
እንዲህ ሚስጥራቸውን ማወቃችን ተስፋ ሊያስቆርጠን አይገባም፣ አንዳንዴም ሆን ብለው ሚስጥራቸውን እንድናውቅ የሚፈቅዱት እንዲህ ተስፋ ለማስቆረጥ የሚሰሩት የአይምሮ ውጊያ ነው፡፡ ሆኖም ግን በበኩላችን እነሱንና ሴራቸውን ለለመከት ያለን መፍትሄ፡
·         ሴራዊ አካሄዳቸውን ማወቅ፣
·         ግባቸውን ማወቅ፣
·         እና በበኩላችን ካወቅናቸው የጥፋት መንገዶች መቆጠብና ሌሎችም እንዳይስቱ መርዳት፡፡
ይህን ማድረግ የምንችለው አፍራሽ ፖለቲካዊ፣ ሃይማኖታዊ እና ስነ ልቦናዊ መርሆቻቸውን በማወቅ ከመከተል በመቆጠብ ነው፡፡ ለምሳሌ በፖለቲካው የተለያዩ ርእዮተ ዓለሞች አሉ፡፡ ከነዚህ የትኞቹ ለትክክለኛ ነፃነት የቆሙ የትኞቹ ለጨቋኞች አሳልፈው የሚሰጡ መርሆችን ይይዛሉ የሚለውን መለየት፡፡ ለምሳሌ የሶሻሊዝምን ታሪክ ማየት፡ ይህ ሁሌም የጭቁኖች እንቅስቃሴ የሚባል በውነቱ ውስጡ ሲመረመር ግን የቁንጮዎች የስልጣንና ሃብት ሞኖፖሊ እውን የሚያደርግ ባእድ እና ሁሌም በቁንጮ ቤተሰቦች በሚገኙ የሚመራ እንቅስቃሴ ነው፡፡ አሁን ሉላዊነት (ግሎባላይዜዥን) የሶሻሊዝምን አለምአቀፋዊነት ተክቶ እየሰራ ይገኛል….፡፡
በሃይማኖት በቅርቡ ከአክራሪነት እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ማን ማንን እየረዳ እንዳለ ማወቅ፡፡
በሌላ በኩል ደሞ በተለያየ ካባ ተከናንቦ ሴጣን አምልኮ እየመጣ ስለሆነ መጠንቀቅ ያሻል፡፡ በተለይ በቲዮሎጂ ፓንተይዝም የሚባለው ቀኖና ማለትም አምላክ በሁሉም ነገር በሰማይ፣ በምድር፣ በእንስሳት፣ በአትክልቶች፣ በድንጋዩ፣ በርሶ፣ በፀሃፊውና ባንባቢው…. ውስጥ የሚገኝ ነው እናም በተመስጦ የመጨረሻ የእድገት ደረጃ ስንደርስ እግዚአብሔርን እንዋሃዳለን የሚል ክርስትያናዊ፣ እስላማዊና ይሁዳዊ ያልሆነ ባእድ አስተምህሮ እየተስፋፋ ይገኛል፡፡
በስነ ልቦናም እንዲሁ የሚሰበክ ሲሆን ይበልጥ ደሞ ሰው ከቁሳዊ ስኬት ውጪ እንዳያስብ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡ ልብ በሉት፡፡ በዚህ መንገድ ሰላማዊ በሆነና በነቃ አካሄድ ሴራቸውን መመከት ይቻላል፡፡ ወደ ዓመፅ መንገድ የምንገባ ከሆነ የነሱ መሳርያ እንደምንሆን አንጠራጠር፡፡ እነሱ ከቀውስ ስርዓት ማምጣት የሴራ ስራቸው እቅድ አካል ነውና፡፡
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on October 28, 2012
  • By:
  • Last Modified: October 28, 2012 @ 8:01 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar