ከዘለአለም ገብሬ ዳላስ – ቴክሳስ
አመታዊውን የሰሜን አሜሪካ ስፖርት ፌስቲቫል ለመታደም ዳላስ ስቴት ገብተናል። እንደወትሮው ለመታዘብ እና ለመገምገም። የ2018 የሰሜን አሜሪካ ስፖርት ፌደሬሽን ዝግጅት አጀማመሩ አሳፋሪ ነበር። ዝግጅቱ በእርስ በእርስ ጭቅጭቅሲጀመር ታዘብን። የክብር እንግዶች ወደ ስታዲየም በሚገቡበት ሰዓት የእንኳን ደህና መጣችሁ ስነስርዓቱ ፍጹም ልምድ ካካበተ አካል የሚጠበቅ አልነበረም። ሰላሳ አምስተኛ አመቱን የደፈነው ይህ ዝግጅት መልካም ስነ ስርአት አልታየበትም። ግን ገና በጅምሩ በስድብ እና በድብድብ መጀመሩ ስንታዘብ ፌደሬሽኑ ያሰማራቸው ሰራተኞችም ጭምር ስርአት አልበኝነት የሚያሳይ መሆኑን ምስክሮች ነን።እይንዳንዱን ችግር በዚህ ጽሁፍ መግለጽ ባይቻልም፤ በግል የታዘብኳቸውን ባካፍል ለወደፊት ትምህርት ይሆናል።
እይታ ቁጥር አንድ
ለበአሉ ድምቀት ተብሎ በሙያቸው ትርኢት ሊያቀርቡ ወደ ስታዲየም ተጠርተው ከነበሩት ውስጥ ነርሶች እና ዶክተሮችበር ላይ ተግተው ነበር። ምክንያቱም ወደ ግቢው መግቢያ መታወቂያ አልያም የተለየ መግቢያ አልነበረም። ከሩቅ ስፍራ ገንዘብ እና ግዜያቸውን መስዋዕት አድርገው የመጡ በርካታ ባላሙያዎች በዚህ መልኩ ሲያጉሏሏቸው ማየቱ በጣም አሳዛኝ ነበር።
ኢትዮጵያውያንን ከየማእዘናቱ ያገናኛል በሚል እሳቤ በዚህ ዝግጅት ድምቀት መጥተው የነበሩ የበርካታ ሙያ ባለቤቶችእንዲህ አይነት እንግልት ሲደርስባቸው ፣ለወደፊቱ በዚህ ዝግጅት ላይ ላለመገኘት ቢወስኑ አያስደንቅም። ፌደሬሽኑንእንዳያድግ ከሚያደርጉት መሰናክሎች ውስጥ እንዲህ አይነቱ ድርጊት የመጀመሪያውነው ።
ለድንኳን ባለቤቶች እና ለመገናኛ ብዙሃን መዘጋጀት የሚገባው መታወቂያም እንደወትሮው በወቅቱ ባለመዘጋጀቱተመሳሳይ ችግር ታዝቤያለሁ። ታዳሚ እንግዶች የመግቢያ ዋጋም ጨምሯል። ገና በጅምሩ $20 የዋጋ ተመን ማውጣታቸው ህብረተሰቡ ወደ ሜዳ እንዲገባም ሆነ ከነጭራሹ እንዳይመጣ የሚጋብዝ ድርጊት ነው ሚመስለው። አጀማመሩ እንዲህ ከሆነወደ የፍጻሜው ፕሮግራም ላይ የመግቢያውን ዋጋ ተመን መጨረሻው ላይ እስከ አርባ የአሜሪካን ዶላር ሊያደርጉት ይችልሉ። ይህ ደግሞ ግለሰቦች ለመዝናናት እና ለመደሰት ሳይሆን ለመበዝበዝ ነው የሚመጡት።
እይታ ቁጥር ሁለት
ፌደሬሽኑ በሚያዘጋጅበት በዚህ ስታዲየም ዙሪያ የመኪና ማቆሚያ ክፍያ የሚያስከፍል ፈቃድ የለውም። ስፍራውማንኛውም ሰው መኪናውን በነጻ ማቆም የሚችልበት ሲሆን ፌደሬሽኑ ግን ጉልበተኞችን እና ስርዓት አልበኞችን በማስቀመጥ ከእያንዳንዱ ግለሰብ ከ፭ ዶላር ጀምሮ ፲ ድረስ እንደፈለጋቸው ታዝበናል። ይህ ክፍያ ያለደረሰኝ መሆኑ ደግሞ ጉዳዩን የከፋ ያደርገዋል።
ይህ ተቋም፣ ታክስ የማይከፈልበት ትኬት፣ እና ትክክለኛ የመኪና ማቆሚያ ባልሆነ ስፍራ ገንዘብ በመቀበል ማጭበርበር መጀመሩ እንዲህ በቀላሉ የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም። ይህንን የፓርኪንግ ክፍያ ጉዳይ አጣርተን እንደተረዳነው፤ የካውንቲ አስተዳደሩም ሆነ ከዚህ በፊት በስታዲየሙ ባለቤቶች ምንም አይነት ክፍያ ለተጠቃሚዎች አስከፍለው እንደማያውቁን ተገንዝበናል። ፈቃድ የላቸውም። እንግዶቹ በነጻ እንዲያቆሙ የተሰጣቸውን ይህንን ቦታ ከግለሰቦች ከፍተኛ ገንዘብይመነዘብራሉ። በር ላይ የገጠመኝን ክስተት ይገርማል። የፓርኪንግ ገንዘብ መክፈል አለብህ ሲል አንዱ ስነምግባር የጎደለው ሰውዬ ጠየቀኝ። ያለምክንያት እና ያለ ደረሰኝ መክፈል እንደሌለብኝ ስከራከረው የሰጠኝ ምላሽ “ከፈለግክ ሜድያ ላይ አውጣው” የሚል ነበር። እነሆ አዋጣሁት!
በመክፈቻው እለት በፓርኪንግ እና በመግቢያ በር ላይ የነበሩት በተቃዋሚ ፓርቲ የተሰባሰቡ ቡድኖች እንደነበሩም ታዝበናል። በአዘጋጅነት የተሰገሰጉት የዳላስ የግንቦት ሰባት አባላት ከኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች ጋር ግብግብ ፈጥረው ነበር። ፌደሬሸኑ የሰጠውን የፕሬስ ካርድ ጭምር አናከብርም የሚሉ ደነዞች ተሰባስበው እውነትም ድርጅቱ ለሙስና ስራ ብቻ የቆመ እንደሆነ ይጠቁመናል።የቀድሞው የፌደሬሽኑ ፕረዚዳንት የነበረው አቶ ጌታⶨው አበስብሶት የነበረው ይህ ቡድን፣ሰውዬው ከስልጣን ከወረደ በሁዋላ ይስተካከል ይሆናል ብለን ስንጠብቅ እንደገና ወደ ዝቅጠት መግባቱ አሳዝኖኛል።
ከአባሎቹ አንዱ በፓርኪግ ቦታ ላይ በመምጣት “ብትፈልጉ ጻፉብን። እናንተ ምን ታመጣላችሁ። ከመሳደብ አታርፉም በማለት ጋዜጠኞችን እና የጋዜጠኝነትን ስነ ምግባር በማጉደፍ ነበር ስራውን የጀመረው። ሙስና እና ዘረፋ ባለበት ሁሉ ጋዜጠኛ እንዳማይወደድ ግልጽ ነው። የኢትዮጵያ ጋዜጠኛ አባላት ለዚህ አንጋፋ ድርጅት በየአመቱ የምንሰጣቸው ገንቢ አስተያየቶች በየጊዜው ተሻሽለው፣ እነርሱን ብለው ሌሎች ወዳጆቻቸውንም ሆነ ዘመዶቻቸውን አገር አቋርጠው የሚመጡትንም ማህበረሰባት አስደስተው ፣ድርጅቱም አድጎ እና በልጽጎ የማየት ተስፋችን ይለመልማል ብለን በማሰብ ነው። የውድቀቱን ጎራ ብቻ ይዞ መጓዙ ሊዋጥልን ባለ መቻሉ ብቻ ነው ወቅታዊ አስተያየቶችን የምንሰጣቸው። ሆኖም ግን ፣በድርጅታዊ የፖለቲካ አቋም ያላቸው ሰዎች በዚህ ፌደሬሽን ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመሰግሰጋቸው ምክንያት ሊያጠራው የማይችላቸው ችግሮችን ተሸክሞ ይዞራል። ይህ አይነቱ የቆሸሸ አሰራር ደግሞ ከወያኔ የተወረሰ ነው። በመሳደብ እና በጉልበተኝነት ስሜት የተደራጁ ቡድኖች አሁንም ድርጅቱ በራሱ እንዳይንቀሳቀስ ሽባ አድርገውታል። ዋና አላማቸው ገንዘብ መስራት መሆኑ ደግሞ የበለጠ ያሳምማል። አምስት እና ስድስት ድንኳን በድርጅት ስም ይወስዱና ባንዲራችንን ይነግዱባታል።
ዝግጅቱን እንበጠብጣለን፤ ዶ/ር አብይ ከተማችንን አይረግጥም… በማለት እያስፈራሩ ዶክተር አብይ እንዳይመጣአድርገዋል።
እይታ ቁጥር ሦስት
አዘጋጅ ቡድኖቹ እኔ ነኝ አለቃ ባይነት እርስ በርስ ሲጣሉ ታዝበናል። ይህንን ማየቱ አሳፋሪ ነበር። ይህ ደግሞ በፌደሬሽኑአሰራር የእያንዳንዳቸውን የስራ ድርሻ ባለማወቅ የተነሳ ይሁን እንጂ እርስ በእርሳቸው ሲሰዳደቡ መታየታቸው ከግምት ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋቸዋል። በክብር እንግዶች ፊት ለፊት የሚደረገውን ትርኢት ሳይሆን ውዝግብ ትኩረት ስቦ ነበር። እንግዳ ጠርቶ ድብድብ!
እይታ ቁጥር አራት
የመድረክ አስተዋዋቂዎች ማይክ ለመጨበጥ የሚያደርጉት ጸብ። አቶ ዘውገ ከሚኪ ጋር በየአመቱ በዚህ አይነት ልዩ ፕሮግራም ላይ መጣላታቸው የተለመደ ከመሆኑም በላይ አስቸጋሪ ባህርይ ያላቸው አቶ ዘውዱ ማይክ አልሰጥም ብለው በማለታቸው ሁል ጊዜም ጸቡ ይፈጠራል። ተባብሮ እና ተከባብሮ የሚሰራበት የሚዲያ መድረክ በእነርሱ አተካሮ ጊዜ ያልፋል ሲሰዳደቡ እና ሲደነቃቀፉ ማስተዋል ደግሞ ይደብራል።መድረኩ የሁሉም ነው ። አቶ ዘውገ ቃኘው ተንቀሳቃሽ ማይኩን ይዘው በየቦታው እየዞሩ ባለበት ሁኔታ ፣ማስታወቂይ የሚናገር ሰው በመጥፋቱ ፣ሚኪ እንዲናገር ከአመራር አካላቶች ትእዛዝ ቢተላለፍም ፣በአቶ ዘውገ የተያዘው ብቸናው ማይክ ደብዛው ጠፍቷል ከእርሳቸው ጋር ፣ታዲያ እንዲህ አይነቱ የተቀናበረ ሃሳብ ከሌለው ሰው ጋር አብሮ መስራቱ ምን ይሰራል በማለት ሚኪም ስታዲየም ውስጥ ደብዛውን አጠፋ ። እነዚህ እርምቶችን ቢሰተካከሉ ብለን ልንጽፍበት ያሰብነው ምክንያት ለብዙ ጊዜያቶች እያየን ፣ታዝበን እነዚህንም ሰዎች ክብራቸውን አነካውም በሚል ነበር ሆኖም ዛሬ ይህ ጉድይ በሰፊው እንዲታይ ያደረገው ፣ የአቶ ዘውገ ቃኘው ከስፒከር እና የማይክ ሞኒተር በከፍተኛ እርቀት ላይ በመሆናቸው የተነሳ ፣ሚኪ ነው የማይኩን ሞኒተር ይጠፋብኝ በማለት ለተለያዩ ክፍል አመርር ቁጣቸውን ለመግልጽ ስልክ ሲደውሉ አግራሞታችንን ሳበው። የፌደሬሽኑ ብቸኛ የሚዲያ ሰው እባክዎትን እንዲህ አይነቱ አሰራር ለማንም አልበጀም እና በጋራ በፍቅር ከስራ ባልደረቦቾት ጋር ይስሩ ።
በአመትም ሆነ በስድስት ወር አንድም ጊዜ በኢትዮጵያኖች ኦዲት ተደርጎ የማያውቀው እና ለሰላሳ አምስት አመታት ህዝብንሲበዘብዝ እና በሙስና ሲከፋፈል የነበረ ድርጅት ስለሆነ እራሱን ማቆም እና የእራሱ የሆነ ስታዲየም መገንባት የሚገባው ይሄው ድርጅት በሙስና በመጨማለቁ በአመት አንድ ጊዜ የእኛን ኪስ ባዶ ያደርገዋል ሲሉ አስተያየት ሰጭዎች ተናግረዋል።
Average Rating