[ቴዲ ድንቅ – አትላንታ]
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን የሚያመሳስላቸው ብዙ ነገር አለ። ሁለቱም የሚያምኑበትን ነገር ፊት ለፊት ይናገራሉ። ሁለቱም ቀጥታ ወደ ነጥቡ ገብተው ያወራሉ እንጂ ዝባዝንኬ አያውቁም። ሁለቱም የሚናገሯቸው አርፍተ ነገሮች ለጥቅስ የሚበቁ ናቸው። ሁለቱም ፈጣሪን የሚፈሩ መንፈሳውያን ናቸው። ሁለቱም ብዙ የጭቃ ጅራፍ ወርዶባቸው በሰፊ ትከሻቸው ችለዋል። ሁለቱም ለእርቅና ለፍቅር ትልቅ ልብ አላቸው።
…… ሁለቱም ያለፈውን በደል ይቅር በማለት ያምናሉ። ሁለቱም በሰላማዊ ሽግግር እንጂ በጦርነትና በፍልጠው ቁረጠው አያምኑም። ሁለቱም ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ያለፉትን በማሰርና በመግደል ሳይሆን በይቅርታና በምህረት ሰላማዊ ሽግግር እንድታደርግ አጥብቀው ያምናሉ። ሁለቱም አከራካሪና ብዙ ውዝግብ ሊፈጥርባቸው እንደሚችል እያወቁም ቢሆን ያመኑበትን ነገር ከማድረግ ወደኋላ አይሉም። ሁለቱም ደፋሮች ናቸው። እነዚህ ሁለቱ የኢትዮጵያ ኩራት ናቸው።
ሁለቱም ለኔ ቀና ብዬ የማያቸው የሞራል ልዕልና ያላቸው ሰዎች ናቸው። ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በህይወት እያሉ ዕድሜያቸውን ሙሉ ሲመኙት የነበረውን፣ ለሁላችንም ከሳቸው ቅርብ ለነበርን ሁሉ በየቀኑ “ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት የይቅርታና የምህረት፣ የፍቅርና የሰላም ጉዞ – የማንዴላ ዓይነት ሰው ነው” እያሉ ሲነገሩን የነበረውን በዓይናቸው ለማየት በመብቃታቸው ከሳቸው ባላነሰ ተደስቻለሁ።
ፖለቲካዊ ፋይዳቸው ሁሉንም በፍቅር መግደል እና በእውነተኛነት ጽናት ፣ትክክለኛውን ነገር በግልጽ መናገር ነው።
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating