አሁን ወልቃይት ጠገዴ ለእርሻ የሚሆን ለም መሬት የለምን?
እነዚህ ወጣቶች የወልቃይት ጠገዴ አማሮች ሲሆኑ በጋምቤላ ክልል የእርሻ ኢንቨስትመንት የተሰማሩ ኢንቨስተሮች ናቸው። ወልቃይት ጠገዴ ውስጥ ለም የእርሻ መሬት ስለሌለን አይደለም ተሰደው የሚያርሱት፣መሬታችን የትግሬ ኢንቨስተሮችና ንብረትነቱ የህወሓት የሆነው የህይወት እርሻ መካናይዜሽን ስለወረረው እንጂ።
የወልቃይት ጠገዴ መሬት አይደለም ለ4ና 5 ወረዳዎች ህዝብ ለመላው አማራ የሚበቃ ነበር።
እነዚህ በፎቶ ላይ የሚታዩት በጣም ጥቂቶቹ ናቸው፣የተሰዳጁ ቁጥር ከዚህ በላይ ነው። በአማራ ክልል መስተዳድር ውስጥ ከፍተኛ ግፍ እና መከራ እየበዛበት ባለበት በአሁኑ ወቅት ፣ላለፉት ፳፯ አመታት በህወሃት ክንድ ስር ወድቆ የነበረው የአማራ ክልል ህልውና ሊመለስ ይገባዋል ሲሉ የክልሉ መስተዳድር ማህበረሰቦች ይገልጣሉ። በተለይም የአማራ ክልል ተወላጅ ሳይሆኑ ፣አማራውን ወክለው ለጭቆና የዳረጉትን ማህበረሰቦች ከክልሉ መስተዳድር መወገድ አለባአቸው ሲሉ እነ ህላዊ ዮሴፍን እና በረከት ስምኦንን ይከሳሉ ፣የእነዚህ በአማራው ውስጥ መሰካት እንደ አቀንጭራ አረም ህዝቡን በድህነት አቀጭ ጨውታል፣ገድለውታል፣ ነጻነቱን ገፈውታል ሲሉም ይገልጻሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአማራ እና ወልቃይት ማንነት ጥያቄ ወልቃይቶች አማራ ነን በሚለው ቢጸኑም የትግራይ መንግስት የእኔ ናችሁ ብሎ እስከ እነ መሬታቸው ሊወስዳቸው ማሰቡ ለግላዊ ጥቅሙ እንደፈለጋቸው እንጂ ማምንነታቸውን ኮርቶበት አይደለም በማለት አክለዋል።
በሌላም በኩል አማራውን ለግፍ እንዲቀመጥ ያደረጉት በስሩ ያሉት የህወሃት አገልጋዮች ናቸው ይህ ይብቃ ለሆዳችሁ አትደሩ ሲሉ ለዶክተር አብይ አህመድ ደግሞ ቀድሞ ሲበዘብዙን የኖሩትን ባለስልጣናት ከአባረርክ በሁዋላ መልሰህ ወደ ስልጣን ማምጣትህ ፣ሙሰኝነታቸውን፣ ገዳይነታቸውን፣ እና ማን አለብኝነታቸውን ወደኸው እና ተቀብለኸው እየሰራህ መሆኑ ላለህበት አላማ የሚያደናቅፍ መሰረት እየጣልክ ሲሆን በእኛ ላይም አመኔታ እንዳይኖርህ እያደረክ ነው ሲሉ ጠቁመዋል።
የወልቃይቱ አማራ ጋሻው ዳኘው በ3ሺ ብር ዋስትና ዛሬ ከእስር ተፈትቷል።
በወልቃይት ጠገዴ ማንነት ጥያቄ ላይ በተነሳው ከፍተኛ ነውጥ ታስሮ የነበረውን ጋሻው ዳኘው መለቀቁም ከጎንደር አካባቢ ካሉት ምንጮች ተሰምቷል
ህወሓት የወልቃይት ጠገዴ አማሮች እያሰረ በዋስትና መብት ሰበብ በወልቃይት ጠገዴ አማሮች ላይ እያደረገው ያለውን የኢኮኖሚ ብዝበዛ ሊያቆም ይገባል።
በተያያዘም ዜና ደግሞ
የጎንደር ከተማ ወጣቶች ወደ ጎንደር አንደኛ ፖሊስ ጣቢያ በማቅናት ታስረው የነበሩትን አቶ ዘለቀ አሰማራውን እና አስቴር ስዩምን አስፈትተዋል።
Average Rating