0
0
Read Time:45 Second
በሂፕ ሆፕ ዘፈን እራሷን በማሳወቅ ላይ የነበረችው እና በተለያዩ የሞዴሊንግ ካምፓኒ የሞዴሊንግ ስራ ስትሰራ የነበረችው አስቴር ታደሰ ህይወት ማለፏን ከቅርብ ወዳጆች የሰማነው ዜና ያረጋግጣል።
የሰላሳ ሰባት አመቷ አስቴር ታደሰ ለድምሳዊት ቻቺ ታደሰ የመጀመሪያ ልጇ ስትሆን ለእረጅም ዘመናት በካሊፎርኒያ ግዛት የኖረች ሲሆን ከቅርብ ጊዜ በሁዋላ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ በማቅናት ኖሮዋን አድርጋ ሁለት ልጆች መውለዷን እና በትዳሯም ስኬትን የተሞላች እንደነበር ይታወቃል።
አስቴር ታደሰ በተለያዩ ጊዜያት ስለ ኢትዮጵያ እሴታዊ ስራዎችን ስታንጸባርቅ የቆየች ሲሆን እንደ እናቷ ዘመናዊ ሙዚቃዊ ስልትን ለአለም አቀፍ ለማሳየት ትልቁ ፍላጎቷ እንደነበር ቀደም ባለው ጊዜ ለማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል መግለጿ ይታወሳል፡፤
ድምጻዊት ቻቺ ታደሰ በዚህ ድንገተኛ አደጋ ሳቢያ ለልጇ ስርአተ ቀብር ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ያቀናች ሲሆን የልጇ የቀብር ስነስርአት በዋሽንግተን ዲሲ ሃሙስ እለት ይሚክከናወን ሲሆን ፣የስርአተ ቀብር ፕሮግራም የሚከናወንበትን ደብር እና ሰርአተ ፍትሃት የሚደረግበትን ቦታ ለዝግጅት ክፍላችን ሲደርስ እናቀርባለን። ማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ፣ለመላው ቤተሰብ መጽናናትን ይመኛል።
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating