የጠቅላይ ምንስትሩ የሚዲያ አሰባሳቢ ኮሚቴ መግለጫውን ግልጽ አድርጓል ፡፡
ጉዳዩ የሚዲያ፡ስነ፡ምግባርን፡የሚጻረር ስራ ነው ማለዻ ታይምስ
በሰሜን አሜሪካ ለሚካሄደው የሃገራዊ ኮንፈረንስ ሁኔታ ጠቅላይ ሚንስትሩን ጥያቄዎች መጠየቅ የሚቻለው በዌብሳይት ላይ ጥያቄዎችን በማስገባት ብቻ መሆኑን የሚዲያ አሰባሳቢው ኮሚቴ ገልጧል ። እንደ ኮሚቴው ውሳኔ ከሆነ ማናቸውንም ሚዲያዎችም ሆኑ ግለሰቦች ጥያቄዎቻቸውን በዌብሳይ ማድረግ ያለባቸው እንደሆነ አሳውቀዋል። የዚህም ዌብሳይት አድራሻ የሚከተለው ሲሆን በሶሻል መገናኛም እንዲያቀርቡ ታዟል ።
Facebook: PM Abiy in DC, #መደመር, @DrAbiyUSVist
Instagram: MedemerUSA
Twitter: MedemerUSA
በሃገራችን ውስጥ ስላለው ለውጥ መወያየት የምንችለው በዌብሳይት በተሰጡ ጥያቄዎች መሆን የለበትም የሚሉት ሚዲያዎች ተቃውⶁቸውን ማሰማት ጀምረዋል።
የቀድሞውን ስርአት ለመመለስ የሚያስችል ከሆነ መገናኛ ብዟሓኖችን ለማፈን የሚረዳ አካሂያድ ከጅምሩ እየተከናወነ ነው ሲሉም መክረዋል።
በዚህ አይነት ሁኔታ የቀድሞው መንግስት ህወሃት ለሃያ አመታት ያፈነውን የመገናኛ ብዙሃን እግደት እና ሂደትን ዛሬ ዶክተር አብይ አህመድ ጥያቄዎችን ከመገናኛ ብዙሃኖች በቀጥታ የማይቀበል ከሆነ እና ለመገናኛ ብዙሃኖች የቀጥታ መግለጫ የማይሰጥ ከሆነ ምንም አይነት የለውጥ ሂደትም ሆነ የመደመር መንገድ የለውም ሲሉ ተችተዋል ።
በዚህም ሂደት የዶክተር አብይ መግለጫ መሆን ያለበት ተብሎ እንደታሰበው እና እንደተገመተው ከሆነ ፣ማንኛውም ሰው የፈለገውን ጥያቄ መጠየቅ የሚገባው በግንባር ቀደም ሲሆን ፣ከተቻለም ደግሞ ማህበረሰቡ ለመገናኛ ብዙሃኖች በመላክ ፣መገናኛ ብዙሃኖች ጥያቄውን ፣ በትክክለኛ መልኩ ህዝቡን በመወከል ማቅረብ አለባቸው ፣ እንጂ ፣የጠቅላይ ሚንስትሩ የሚዲያ አሰባሳቢ ኮሚቴ ማናቸውንም ሚዲያዎችንም ሆነ ፣የህትመት እና የሬዲዮ ድርጅቶችን ሊወክሉ አይችሉም በማለት ገልጸዋል።
በሌላም በኩል አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎችም በፌስቡክ ገጾቻቸው ላይ የሰጡት አስተያየት እንዳለም ለመግለጽ እንወዳለን።
ለኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን እታፈን ዋነኛ መንስኤ ባለስልጣናትም ሆኑ ፣ባለሃብቶች፣ የኪነጥበብ ሰዎች፣ ሙዚቀኞች፣ ዘፋኞች/አዝማሪዎች ፣ሌሎችም የሙያ አካላት፣ እና ምሁራን፣ ከጋዜጠኞች ለሚቀርብላቸው የቃለመጠይቅ ፎርም ወይንም ጥያቄ በቅድሚያ በደብዳቤ ጥያቄዎችን አሳውቀኝ በማለት እውነተኛውን ማንነታቸውን ላለማሳወቅ የሚጠቀሙበት ትልቅ አጀንዳ ነው ። በትክክለኛውም ለሚጠየቁጥ ጥያቄ የሚመልሱትን መልስ ሸምድደው በመምጣት ህብረተሰብን ባልታሰበበት አቅጣጫ ሊያስቱ እና ሊያስደስቱ ይሞክራሉ ፣አሁን ግን ይህ የነጻነት እና የእውነተኛ መረጃ የማቀበያ ዘመን ነው ፣ማንኛውም ጋዜጠኛ በቀጥተኛ መልኩ የሚፈልገውን ፣ያየውን እና የተሰማውን የሚጠይቀበት መድረክ ሊከፈት ይገብዋል እንጂ በደብዳቤ አስገቡ ማለት የሚዲያው መታፈን አባዜ ሁንም አለቀቀውም ማለት ነው።
Average Rating