ባሳለፍነው፡ወራት፡ነበር፡የአስመራው፡የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ልኡካን እና የኢትጵያው አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር የመጀመሪያ ጥሪ በተደረገላቸው መሰረት በቀጥታ ከአስመራ ወደ አዲስ አበባ በመብረር የዲፕሎማሲ ውይይት ያደረጉት የነበረው ፣ከዚያም በመቀጠል የዶክተር አብይ ወደ አስመራ መጓዝን ተከትሎ ፣ በአሁን ሰአት በአፍሪካ ውስጥ የእረጅም ጊዜ ስልጣን ባለቤት የሆኑትን የአስመራውን ፕረዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂን ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ በደማቅ ሁኔታ ያስተናገደችው ።
ለእረጅም ጊዜያት የደስታ ስሜት የራቃቸው እኝሁ ፕረዚዳንት ፣ለመጀመሪያ ጊዜ ከልባቸው ሲሰቁ እና ሲፈነድቁ ዋሉ እየተባለም ሲነገርላቸው ከርሟል።
የአዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር መመረጥ በሃገሪቱ ላይ ያለውን ፖለቲካ አካሂያድ ወደ ታች እንዲያንሸራትት የዳረገ ከመሆኑም በላይ የስደተኛውንም የፖለቲካ አቅታጫ በማስቀየር ወደ አንድ ሃገራዊ ስሜት ያመጣ እና ከመከፋፈል ያዳነ መሆኑ ተመስክሮለታል።
ለዚህም የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የሰላም መንገድ በህወሃት መንደር ተወዳጅነት ባይኖረውም በመላው ሃገሪቱ እና ሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ምሳሌ ሆኖ ሊቀርብ በሚችል ጅምር ልላይ መሆኑ ተመስክሮለታል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ለዚህ የሰላም ምስክርነት ይሆን ዘንድ የየተባበሩት አረብ ኢምሬት አልጋ ወራሽ ሼህ መሃመድ ቢን ዘይድ ለሁለቱ ሃገራት የሰላም ትብብር ማስቀበት የወርቅ ሽልማት ያበረከቱ ሲሆን ፣በሁለቱ ሃገራት ላይ የሚከናወነውንም የሰላም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች በጋራ እንደአወያዩ የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃኖች ጠቁመዋል።
አልጋ ወራሹ ልዑል ሼክ መሃመድ ቢን ዘይድ በሁለቱ ሃገራት መካከል ሰላም ማውረድ በመቻላቻው ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድና የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሜዳልያ ሽልማት ማበርከታቸው የሚደገፍ ነው ሲሉ የአረብ ሃገራት ማህበረሰቦቻቸው በትዊተር አካውንቶቻቸው እና በፌስቡክ ገጽ ላይ ባሰፈሩት አስተይየት ገልጸዋል።፡፡
ይህም ለሁለቱ አገራት መሪዎች የተበረከተው ሜዳሊያ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሚበረከተው ከፍተኛ የክብር ሜዳሊያ ሽልማት ነው፡፡
Average Rating