www.maledatimes.com ሰበር ዜና የህዳሴው ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ አዲስአበባ መስቀል አደባባይ ላይ መኪናቸው ውስጥ ላይ ሞተው ተገኙ!! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ሰበር ዜና  የህዳሴው ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ አዲስአበባ መስቀል አደባባይ ላይ መኪናቸው ውስጥ ላይ ሞተው ተገኙ!!

By   /   July 26, 2018  /   Comments Off on ሰበር ዜና  የህዳሴው ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ አዲስአበባ መስቀል አደባባይ ላይ መኪናቸው ውስጥ ላይ ሞተው ተገኙ!!

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 32 Second

ኢንጅነር ስመኝ በቀለ በተገደሉበት ሰአት

ሰበር ዜና
የህዳሴው ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ አዲስአበባ መስቀል አደባባይ ላይ መኪናቸው ውስጥ ላይ ሞተው ተገኙ!!

የፖሊስ_ኮሚሽነር ጄኔራሉ ዘይኑ ጀማል ስለ ኢ/ር ስመኘው ግድያ የሰጡት መግለጫ፦ by Yoseph Tegania
* ኢንጅነር ስመኘው ጠዋት አንድ ሰዓት ከቢሮው ገብቶ ሲወጣ ታይቷል። መስቀል አደባባይ የታየው ሁለት ሰዓት ከሃያ ነው።
* የተተኮሰበት ጥይት ብዛት ያልታወቀ ሲሆን መኪናው ውስጥ የተገኘው ኮልት ሽጉጥ የእርሱ ይሁን አይሁን አልታወቀም።
* የተተኮሰበት ጆሮ ግንዱ (ጆሮው ስር) አካባቢ ነው።
* አብዮት አደባባይ ተገጥሞ የነበረው ካሜራ ለመንገድ ስራ ተብሎ ከተነሳ ቆይቷል። ምናልባትም የአይን እማኞች ያዩት እንደገና እየተገጠመ እያለ ሊሆን ይችላል።
* ከሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት ጋር ይያያዝ አይያያዝ በዚህ ሁኔታ ማወቅ አይቻልም።
*የሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት ምርመራ ውጤት የዘገየው ዲኤንኤ ምርመራ የሚደረገው ውጭ አገር በመሆኑ ነው።

“ከግድያው በስተጀርባ”
#ታደለ ጥበቡ በፌስቡኩ ያሰፈረው አንደምታ ይህንን ይመስላል
የኢጂነር ስመኘው በቀለን ግድያ ከህወሓት ውጭ ማንም ሊያቀነባብረው አይችልም።ህውሃት የኢትዮጵያን ህዝብ ለአባይ ቦንድ ግዙ እያለች በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ ዘርፋለች።ለምንጣሮ የተመደበው 2 ቢሊዮን ገንዘብ እንኳን የገባበት የውሀ ሽታ ሆኖ ቀርቷል።ለዚህ ዋና ተጣያቂዎች ደግሞ የሜቴክ ሀላፊ የነበረው ክንፈ ዳኘውና የInsA ዳይሬክተር ጄኔራል ተክለብርሃን ወልደ አረጋይ ናቸው።

ጠሚዶ አብይ አህመድ ወደስልጣን እንደመጡ ሁለቱም የዘረፉትን ገንዘብ ይዘው በአንድ ቀን ሥራ ለቀዋል።በአሁኑ ሰአትም ማንም አያስረንም በማለትም መቀሌ ውስጥ ምሽግ ይዘው ይገኛሉ።የተዘረፈውን ገንዘብ ደግሞ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ አያውቁም አይባልም።እያንዳንዱን ነገር ያውቃል።ስለዚህ ምስጢር ማውጣቱ አይቀሬ ነው።ዛሬም ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት እየሄደ ባለበት ሰአት ነው መስቀል አደባባይ ላይ የገደሉት።

በተደጋጋሚ እንደምንለው ህውሃት የሚባለ አሸባሪ ቡድን ከምድረ ገጽ እንደዳይኖሰር ካልጠፋ ኢትዮጵያ በየእለቱ እንደዚህ ያሉ አሳዛኝ ታሪኮችን ማስተናገዷ አይቀርም።በተለይ በስመኘው በቀለ ግዳይ ላይ ክንፈ ዳኘው እና ተክለብርሃን ወልደአረጋይ ተይዘው ምርመራ ሊካሄድባቸው ይገባል!!

ጠሚዶ አብይ አህመድም ሳናጣራ አናስርም የሚለውን ትርክታቸውን ማቆም አለባቸው።ሀገር እያፈረሱ፣ምሁራንን እየገደሉ ዝም ማለት ተገቢ አይደለም።

Image may contain: 5 people, people smiling, people standing and people sitting

ኢንጂንየሩ ከቤተሰቦቻቸው ጋር

Image may contain: 3 people, people standing

የኢንጅንየሩ ልጆች

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on July 26, 2018
  • By:
  • Last Modified: July 26, 2018 @ 11:32 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar