www.maledatimes.com ከ65ቱ የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ውስጥ ፀረ አማራው እና መሀል ሰፋሪው ወይም ወላዋዩ ካምፕ ተለይቶ ታወቀ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ከ65ቱ የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ውስጥ ፀረ አማራው እና መሀል ሰፋሪው ወይም ወላዋዩ ካምፕ ተለይቶ ታወቀ

By   /   July 31, 2018  /   Comments Off on ከ65ቱ የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ውስጥ ፀረ አማራው እና መሀል ሰፋሪው ወይም ወላዋዩ ካምፕ ተለይቶ ታወቀ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 21 Second

ብአዴን በሽግግር ውስጥ ከፍተኛ የለውጥ አጋፋሪም ቢሆንም ከህወሃት ጋር ወግነው የለውጡን ሂደት ማደናቀፍን የሚጥሩ ብዙ ሰዎች እንዳሉም ለማወቅ ተችሏል።

ያገለግሉኛል ብሎ ያሰቀመጣቸውን ህዝብ ሳይሆን የሚመለከቱት የስርአቱን ጎፈሬ የሚያጎፍረውን የህወሃት ጡንቻን ነው ሲሉም ይወቅሳሉ፣፡ብአዴን ለአማራው የቆመ አይደለም ፣ለጥቅሙ እና ለስሙ ነው ብለው የገለጹም እንዳሉ ለመረዳት ተችⶀአል።

ከ65ቱ የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ውስጥ ፀረ አማራው እና መሀል ሰፋሪው ወይም ወላዋዩ ካምፕ ተለይቶ ታወቀ

ከ65ቱ የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ውስጥ .

Your Asian Dream Woman Is Waiting For You Here

15ቱ ፀረ አማራ/ፀረ ለውጥ፣
27ቱ የለውጥ ደጋፊ እና
23ቱ ወላዋይ ናቸው።
ማዕከላዊ ኮ.ያልሆኑ 7 አደገኛ ፀረ ለውጥ አቊም ያላቸው ሰዎችም አሉ።
በድምሩ 22 ፀረ ለውጥ አቋም ያላቸው አሉ

ብአዴን ከ65ቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ውስጥ 15ቱ በግልፅ ፀረ ለውጥ ወይም ፀረ አማራ ናቸው ተብለው ተለይተዋል።27ቱ የለውጥ ቡድን ሲሆኑ ቀሪ 23ቱ #ወላዋይ ተብለዋል።ከዚህ ቡድን ውስጥ አህመድ አብተውና አለምነው መኮነን ይገኙበታል።በእኔ እምነት ግን እነዚህ ሰዎች ፀረ አማራ ናቸው።

ከዚህም በላይ ለውጡን እጅግ የከፋ የሚያደርገው ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ውጭ ያሉ ነገር ግን በመመሪያ ስብሰባ መሳተፍ የሚችሉ አደገኛ ሰዎችም ተለይተዋል።መረጃው ከቅርብ ሰው የተላከ እንጅ የእኔ አይደለም።95% ግን አምንበታለው።

ብአዴን የአማራን ህዝብ ጥቅም እናስከብራለን ብለው እየታገሉ ያሉ የለውጥ ኃይሎች በድርጅቱ ውስጥ ተሰግስገው በገቡ የብሄሩ ውክልና በሌላቸው አዛውንቶችና ተላላኪ ባንዳዎች የሚደርሱባቸውን በርካታ ፈተናዎች እየተጋፈጡ አሁን እየታየ ያለውን የለውጥ ጭላንጭል እንድናይ ያደረጉ በርካታ ጀግና አመራሮች ያሉት ድርጅት ሆኖ ሳለ የግለሰቦች ድርጅት አድርገው የሚስሉት ግብዞች እንዳሉ መታወቅ አለበት፡፡

ለውጥ አደናቃፊዎች የሚያደርጉት ማናቸውም ዘመቻ ገብቷቸው እንጅ ተሳስተው የፈፀሙት እንዳልሆነ ማወቅ ይገባናል፡፡ ለምሳሌ ብናነሳ ገዱን ብቻ ቆርጦ መጣል ከተቻለ አዛውንቶቹ በብአዴን ውስጥ የነበራቸውን አዛዥነት አስጠብቀው መቀጠል እንደሚችሉ አድርገው ያሰርፃሉ፡፡ ሃቁ ግን ብአዴን የበርካታ ገዱዎች ስብስብ እንጅ የግለሰብ ድርጅት አለመሆኑ ነው፡፡ እናም አንድ ገዱን በማጥፋት ብአዴንን ማጥፋት እንደማይቻል ልብ ሊባል ይገባል፡፡

ሌላው የማደናገሪያ መረጃ የኃይል ሚዛኑ በለውጥ ኃይሉ እጅ ሳይሆን በአደናቃፊዎችና አድርባዮች እጅ እንደሆነና የለውጥ ኃይል የሚባሉት ጥቂቶች እንደሆኑ በማስመሰል ብአዴን ከህዝቡ ድጋፍ ተቀብሎ እራሱን እንዳያጠራ ለማድረግ የሚለቀቀው ሞገድ ነው፡፡

የኃይል ሚዛኑ አሁንም ለአማራ ህዝብ መብትና ጥቅም መከበር በቆሙ የለውጥ ኃይሎች እጅ እንጅ በአደናቃፊዎችና አድርባዮች እጅ እንዳልሆነ ህዝቡ በውል ሊገነዘብና ያልተቋረጠ ድጋፉን ሊሰጥ ይገባል፡፡ የአማራን ጥቅም ተፃራሪ ሆነው የቆሙትን ኃይሎች የለውጥ ደጋፊና ለህዝብ ጥቅም የሚታገሉ በማስመሰል የተደበላለቀ ሃሳብ እንደተያዘ እንዲቀጥል፣ብአዴን በጉባኤው ጠርቶ እንዳይወጣና ደካማ ድርጅት እንዲሆን በማድረግ የአማራን ህዝብ አሁንም እንደገና ለመጨቆን የተጠነሰሰው ሴራ ሌላኛው ስልት እንደሆነ ደርሰንበታል፡፡

ሌላውና በጣም የሚገርመው ብአዴን 15 ሴት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት አሉት፡፡ ከነዚህ ውስጥ የአማራ ህዝብ ጉዳይ የሚያንገበግባትና ፊት ለፊት እየታገለች ያለችው ወ/ሮ ሽታየ ምናለ ብቻ ናት፡፡ ቀሪዎቹ ሆዳቸውን ከመሙላት የዘለለ የአማራ ህዝብ ጉዳይ ጉዳያቸው አይደለም፡፡ ይሄም ብቻ ዓይደለም ብአዴን ብዙ ዶ/ር የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ነበሩት፡፡ ከዶ/ር አምባቸው መኮንን፣ ከዶ/ር ይናገር ደሴ እና ዶ/ር ስንታየሁ ወ/ሚካኤል ውጭ ያሉት ተምረው ያልተማሩ ሆድአደሮች እንደሆኑ መረጃው ተደርሶበታል፡፡

ሲጠቃለል ብአዴን እነዚህ ሁሉ ሸክሞች ያሉበት ድርጅት ነው፡፡ ህዝቡ ብአዴን ተጠናክሮ ወጥቶ እራሱን እንዲያጠራና ስነ-ልቦናውን በሚረዱ መሪዎች መመራት ይፈልጋል፡፡ ይህ ሁሉ እውን መሆን የሚችለው የለውጥ ኃይሉን ስንደግፍ በመሆኑ በማዕከላዊ ኮሚቴው ውስጥ ማነው ለአማራ ህዝብ ጥቅም የቆመ፣ ማነው መሃል ሰፋሪ፣ ማነው የለየለት ባንዳና አፍራሽ የሚለውን ህዝቡ እንዲያውቀውና በመረጃ ላይ ተመስርቶ እንዲታገል ቀጥየ አቅርቤዋለሁ፡፡

ፀረ ለውጥ ወይም አፍራሽ የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ዝርዝር፡-

1) በረከት ስምኦን
2) ከበደ ጫኔ
3) ፍሬህይወት አያሌው
4) ጌታቸው አምባየ
5) ዝማም አሰፋ
6) ታደሰ ካሳ
7) ምትኩ በየነ
8) ካሳ ተ/ብርሃን
9) ዘነቡ ታደሰ
10) ወለላ መብራት
11) ወርቅሰሙ ማሞ
12) ባዘዘው ጫኔ
13) ይልማ ወርቁ
14) ገነት ገ/እግዚአብሄር
15) ማዕዛ ገ/መድህን ናቸው፡፡

 ከማዕከላዊ ኮሚቴ ከተሰናበቱ በኋላ የድርጅቱን መተዳደሪያ ህግ ጥሰው አቅጣጫ በማሳትና በማደናገር የተጠመዱ፡-

1) አዲሱ ለገሰ
2) ህላዌ ዮሴፍ
3) መለስ ጥላሁን
4) ገነት ዘውዴ
5) ወንድወሰን ከበደ
6) ወርቅነህ መኮነን
7) ነጋ ፀጋየ ናቸው፡፡

መሃል ሰፋሪዎች/ወላዋዮች፡-

1) ዶ/ር ጥላየ ጌቴ
2) ዶ/ር አምላኩ አስረስ
3) ዶ/ር ተሾመ ዋለ
4) ዶ/ር ምስራቅ መኮንን
5) መኮነን የለውም ወሰን
6) ብርሃን ኃይሉ
7) ስዩም መኮነን
8) ፈንታየ ጥበቡ
9) ባንችይርጋ መለሰ
10) ትልቅሰው ይታያል
11) ውባለም እስከዚያው
12) ምስራቅ ማሞ
13) ብስራት ጋሻውጠና
14) ደሳለኝ አምባው
15) ደስታ ተስፋው
16) ጌታቸው ኃ/ማርያም
17) አየነው በላይ
18) አህመድ አብተው
19) አለምነው መኮነን (አወዛጋቢው አለምነው መከነን) ናቸው፡፡

ይህንን ሃቅ ይዘን ከለውጥ ኃይሉ ጎን በመቆም ከችግር ለመውጣት ሸር በማድረግ የበኩላችንን እንወጣ!!ከላይ የተዘረዘሩት የተስፋየን እና ቲሙን አደራ ይበላሉ ተብለው በብአዴን መንደር የተለዩና የተላኩ ናቸው።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar