እስክንድር ነጋ የሚዲያ ቢሮ ከፈተ!
ላለፉት 12 አመታት በህወሀት/ኢህአዴግ አገዛዝ በኃይል ተዘግተው ከነበሩት የነፃው ፕሬስ ቢሮዎች መካከል አንዱ የነበረው የእነ እስክንድር ቢሮ ዳግም ተከፈተ። በቅርቡም በተለያዩ የሚዲያ ውጤቶች ከህዝቡ ጋር ለመገናኘት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል…..ጋዜጠኞች ተሰባስበውም ኬክ በመቁረስ መልካም የስራ ዘመን ተመኝተዋል….ነፃው ፕሬስ ታፍኖ አይቀርም….የህዝብ አደራ አለብን በማለት ገልጸዋል ! ባሳለፍነው ወር ጋዜጠኛ እስክንድ ነጋ በሰሜን አሜሪካ ባደረገው ጉዞ ከተለያዩ የቀድሞ የስራ ባልደረቦቹ ጋር በዳላስ ቴክሳስ የሚዲያ ምክክር እና የስራ ሂደት አስመልክቶ ስብሰባ ማካሂያዱ ይታወቃል በዚህም መሰረት በስደት ላይ ያሉትን ጋዜጠኞች እን በሃገር ውስጥ ያሉትን ትንታግ የሚዲያ ሰዎች በማሰባሰብ ጠንካራ የሆነ አለም አቀፋዊ የቴሌቪዥን ተቋም ለማቋቋም እና ስራውን በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲከንወን ለማድረግ ቃል ገብተዋል።
ጋዜጠኞች እንደጋዜጠኝነታቸው ለፖለቲካ ፓርቲዎች ወይንም ለመንግስት እና ወኪሎቻቸው የሚወክል ሳይሆን ህዝብን እና ሃገርን ሊጠቅም በሚችል መልኩ ተአማኒነትን የተሞላ የመረጃ ሃይል ፍሰትን ይዞ እንዲጓዝ የሚያስችል ፣ትልቅ ተቋም መፈጠር አለበት ሲሉም አምነዋል። በዚህም ሂደት ወደፊት የቦርድ አባላትን እና የሼር ሆልደር አባላትን የማሰብሳሰብ እና የማጠናከር ስራ ይሰራል በማለት መክረዋል፡፤
ድል ለዲሞክራሲ!!
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating