የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ታምራት ላይኔ ሃገራቸውንና መንበራቸውን ለቀው እንዲሄዱ በጭነት መኪና ወደ ኬንያ ያስወጧቸውን ቅዱስ ፓትርያርክ አባ መርቆሪዮስን ይቅርታ ጠይቀዋል።
በዛሬው እለት በደረሰን መረጃ መሰረት ፓትርያሪኩ ወደ ሃገራቸው በዶክተር አብይ አማካይነት እንዲገቡ እና መንበረ ስልጣናቸውን እንዲረከቡ ከተወሰነ ጊዜ ጀምሮ ብዙ የሃገረ ስብከት አስተዳዳሪዎች በተገኙበት ይቅርታ እንዲጠይቁ የተደረጉ የሃገረ ስብከት ፣እና የሊቀነ ጳጳሳት መናብርቶች ይቅርታ ማለታቸውን ተገልጾአል ፡፤ በዚህም ሁኔታ በቀድሞው ስልጣናቸርው ወቅት አማራውን ወክለው ሃገሪቷን ሲመሩ የነበሩት እና በአማራው ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛውን በደል እንዲፈጸምበት ትልቁን ሴራ ያሴሩት የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ታምራት ላይኔ በፓትርያሪኩ በጊዜአዊ በሚገኙበት ቢሮ በመገኘት ይቅርታ ማለታቸው ተገልጾአል።
እኝሁ ጠቅላይ ሚንስቴር ቀደም ባለው ጊዜ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዲወጣ በታዘዘ ገንዘብ ለህወሃት ወያኔ የሚያገለግል ንብረትነቱ የኢትዮጵያ ህዝብ የሆነ ገንዘብ በቁጥሩ ከሚሊዮን በላይ በፊርማቸው አረጋግጠው መስጠታቸው የሚታወቅ ሲሆን ፣ ብዙሃኑን ኢትዮጵያኖችን አስቆትቶም እንደነበር ይታወሳል።
በስልጣናቸው ወቅት በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስቴር (ሟቹ መለስ ዜኔዊ ) ስኳር ቅመሃል በማለት በሙስና እስርቤት እንደወሸቋቸው እና ለእረጂም ጊዜያት በእስር ሲማቅቁ ቆይተው ፣በእስር ቤት ውስጥ ሳሉ ጌታ ተገልጦልኛል በማለት በአሁን ሰአት የጌታ አገልጋይ ነኝ ብለው በፕሮቴርስታንትነት አማኝነት እየኖሩ እንደሚገኙ መዘገባችን ይታወሳል።
ታምራት ላይኔ ፓትርያሪኩን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብን በይፋ መጠየቅ አለባቸው፣ ለፈጸሙት እና ለበደልኩት በደል የኢትዮጵያ ህዝብ(ህዝበ ክርስቲያኑ) እንዲተላለቅ እንዲጠላላ እንዲሁም እንዲከፋፈል ትልቁን ስራ የሰሩት እርሳቸውን ናቸው እና ይህም በቂ አይደለም ሲሉ አስተያየት የሰጡ ሰዎች አሉ፡፤
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለአለፉት ሃያ ሰባት አመታት በደል ሲፈጸምባት፣ስትመዘበርት ፣ እና የእርስ በእርስ እልቂት እንዲኖርባት ትልቁ ድርሻ የታምራት ላይኔ የክፋት አለንጋ ነው በህዝቡ ላይ የወረደው ፣ ይህ ደግሞ ፓትርያሪኩን ብቻ ይቅርታ በማለት የሚያበቃም አልነበረም፣ ለአደረጉት ክፋት ቅጣት በተገቢው መንገድ ይገባቸው ነበር ፣ሆኖም ግን የይቅርታ እና የምህረት ዘመን ቢሆንም በአደባባይ ወጥተው አሁንም ህዝቡን በይፋ መጠየቅ አለባቸው ሲሉ የማለዳ ታይስምስ አስተያየት ሰጭዎች ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የዘመናት ሃዋርያ ብትሆንም ዛሬ ላይ ግን አንገቷን እንድትደፋ እና የመቶ አመት ታሪክ ነው ያላት እየተባለ እንዲነገርላት ካስደረጉት ሆነ ቅርሳቅርሶቿ ወደ ውጭም ሆነ በእሳት ቃጠሎ እንዲሁም በጂማ እና ሌሎችም አካባቢዎች የተደረጉት አበያተ ክርስቲያናት ቃጠሎ እርሳቸው ሊጠየቁበት ይገባል ያለው ወጣት ዘሪሁን የእኛነታችንን ህልውና ነጥቀውናል፣ ለሁለት አስርተ አመታት አታግለውን እንድንጠላላ ሆነናል ሲል ገልጧል።
Average Rating