www.maledatimes.com “መለስን ከሞት አስነሰዋለሁ ” እስራኤል ዳንሳ በታደለ ጥበቡ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

“መለስን ከሞት አስነሰዋለሁ ” እስራኤል ዳንሳ በታደለ ጥበቡ

By   /   August 3, 2018  /   Comments Off on “መለስን ከሞት አስነሰዋለሁ ” እስራኤል ዳንሳ በታደለ ጥበቡ

    Print       Email
0 0
Read Time:49 Second

“መለስን ከሞት አስነሰዋለሁ ” እስራኤል ዳንሳ

ይሄን የተናገረው እስራኤል ዳንሳ ሐዋሳ ላይ በነበረው አገልግሎት ላይ ነው።

እስራኤል ዳንሳ እንዳለው ከሆነ “የ6 አመቱን ሬሳ መለስ ዜናዊን ከሞት የማስነሳት መንፈሳዊ ብቃት ላይ እገኛለሁ።ሰውን ማስነሳት ለኔ አዲስ አይደለም ከዚህ ቀደምም ሁለት የሞቱ ህጻናትን አስነስቻለሁ”ሲል ከሞት የማስነሳት ልምድ እንዳለው በኩራት ተናግሯል።

እስራኤል ዳንሳ ይቀጥልና “ዋናው በጌታ በኢየሱስ ማመን ነው።የስንፍጭ ቅጣት ታክል እምነት ያለው ሰው የኪሊማንጆርን ተራራ ወደ ኢትዮጵያ ማምጣት ይቻላል ወይንም አዲስአበባን ወደ ሐዋሳ ሐዋሳን ወደ አዲስአበባ መቀያየር ይቻላል፤ጌታ ኢየሱስም ይሄን ቃል አስተምሯል”ሲል ነው ለታዳሚው የገለጸው።

ታዳሚውም “ይቻላል”በማለት በጭብጨባ አጅቦታል።

እስራኤል ዳንሳ እንዳለው ከሆነ “ወ/ሮ አዜብ መስፍን የመለስ መቃብር እንዲቆፈር ከፈቀደች ካለምንም ክፍያ አስነሳዋለሁ፤ከኔ የሚጠበቀው በጌታ በኢየሱስ ሥም ብቻ መጸለይ ነው” ብሏል።በርግጠኝነትም ከመቃብሩ እንደ አልዓዛር ተነስቶ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር “ይደመራል”ሲል ነው የጌታ የኢየሱስን ስምን እየጠራ የተናገረው።

አንድ ታዳሚ ይሄ ነገር በወለጋ ቄሌም ወረዳ ተሞክሮ እንደከሸፈና ውርደት እንዳያመጣ ሲጠይቀው “እሱ ሐሰተኛ ነው።ከሐሰተኞች ሰዎች መጠንቀቅ አለባቸው።በኛ ስም የሚነግዱ ብዙ ሐሰተኞች እንደተነሱ እያየን ነው”ሲል መልሶለታል።
Editorial Event Platform

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar