"ጠቅላይ ሚንስትር ዶ / ር አቢይ አህመድ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ የፋይናንስ አማካሪ ካውንስል እና አባላትን ማቋቋሙን አስታውቋል::
ከካውንስሉ ጋር ለመተባበር ተነሳሽነት ያላቸውን ሁሉንም ግለሰቦች እና ቡድኖች ያመሰግናሉ።
"- ፍጹም አረጋ, ዋና ሰራተኛ, ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ / ቤት. በዚህም መሰረት የካውንስል ምክርቤቱ ሊመሩት የሚገባቸውን ሰዎች በግልጽ አሳውቋል።
አለማርያም እና ኤልያስ ክፍሌም የአማካሪነቱን ቦታ ይዘዋል ። ለዚህ ቦታ ይመጥናሉ
የተባሉ ሰዎች የገቡበት ሲሆን በመጠኑም ውስጥ ምንም የማይገባቸውም ግለሰቦች መታደማቸው ጥናቱን እንዲታሰብ ያደርጋል። በዚህም መሰረት አንዳንድ
አስተያየት ሰጭዎች እንደገለጹት ከሆነ "ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አብይ አህመድ የዲያስፖራ ትረስት ፈንድን እንዲቆጣጠሩ እና እንዲያስተባብሩ
የተመረጡ አባላት ስብጥርና ማንነት ሲታይ ከተለያዩ ድርጅቶች መሆናቸውና በዳያስፖራው ከፍተኛ እምነት የሚሰጣቸው መሆናቸው በጣም
ጥሩ ምርጫ ነው።በተጨማሪ ግን እንደአስተያየት መስጠት ምፈልገው ገንዘብ ማሰባሰብ ፈንድ ራይዚንግ ላይ ጥሩ ልምድ ያላቸው የማስተባበር ችሎታቸውም
በጣም ጥሩ የሆኑት ከዙህ ከDMV መምህር ዶ/ር ዘነበ እና አርቲስት አለምጸሀይ ወዳጆም ቢካተቱ ጥሩ ነው የሚል እምነት አለኝ።"
ስትል ሰላማዊት ፍሰሃ በፌስቡኳ ገልጻለች ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ በወቅቱ በውጭ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በየቀኑ ቢያንስ 1 የአሜሪካ ዶላር በመለገስ ለተለያዩ የልማት ስራዎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀው ነበር። ለዚህም ይረዳ ዘንድ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድን የሚያማክር ምክር ቤት ማቋቋማቸው ይፋ ሆኗል። የምክር ቤቱ አባላትም የሚከተሉት ናቸው።
1. ዶክተር አለምአየሁ ገብረማርያም – የምክር ቤቱ ሊቀመንበር
2. ዶክተር ብስራት አክሊሉ
3. አቶ ገብርኤል ንጋቱ
4. አቶ ካሳሁን ከበደ
5. ዶክተር ለማ ሰንበት
6. ወይዘሮ ሉሊት እጅጉ
7. ዶክተር መና ደምሴ
8. ወይዘሮ ሚሚ አለማየሁ
9. አቶ ሚኒልክ አለሙ
10. አቶ ኦባንግ ሜቶ
11. አቶ ሮብሰን ኢታና
12. አቶ ታማኝ በየነ
13. አቶ ተሽታ ቱፋ
14. አቶ ይሄነው ዋለልኝ እና
15. አቶ ኤሊያስ ወንድሙ የምክር ቤቱ አባላት ተደርገው ተመርጠዋል።
ምንም እንኳን በዝርዝሩ ውስጥ ጥሩ ጥሩ ስምና ዕውቀት ያላቸው ሰዎች ቢኖሩም፣ የዚህ የአንድ ዶላር በቀን ሃሳብ አፍላቂ፣ የህክምና ባለሙያና የአትላንታ ነዋሪ የሆኑት ዶክተር ተስፋዬ መኮንን አለመካተታቸው በርካታ ያነጋገርናቸው የአትላንታ ነዋሪዎችን ቅር አስኝቷል።
በዚሁ አጋጣሚ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በሚል ስም ሂሳብ መከፈቱ የሚታወስ ሲሆን፣ የሂሳብ ቁጥሩም 1000255726725 ነው። ከዚህ ውጭ ግን የራሳቸውን “ጎ ፈንድ ሚ” አካውንት ከፍተው ገንዘብ የሚሰበስቡም እንዳሉ ሰምተናል። እኛ ባለን መረጃ ግን በጎ ፈንድ ሚ የሚሰበሰብ ገንዘብ ትክክል አይደለም። ገንዘባችሁን ከመስጠታችሁ በፊት ትክክለኛውን መንገድ መጠቀማችሁን አረጋግጡ። ይህንና ሌሎችንም ጉዳዮች በተመለከተ አድማስ ሬዲዮ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደርን ለማነጋገር ይሞክራል።
Average Rating