www.maledatimes.com የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራን ወደብ አጠቃቀም የሚያጠና ቡድን አቋቋመ (ምንጭ ዋዜማ ሬዲዮ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራን ወደብ አጠቃቀም የሚያጠና ቡድን አቋቋመ (ምንጭ ዋዜማ ሬዲዮ)

By   /   August 11, 2018  /   Comments Off on የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራን ወደብ አጠቃቀም የሚያጠና ቡድን አቋቋመ (ምንጭ ዋዜማ ሬዲዮ)

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 24 Second

ዋዜማ ራዲዮ- በቀድሞ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ግርማ ብሩ የሚመራ ቡድን ኢትዮጵያ የኤርትራን ወደቦች የምትጠቀምበትን ሁኔታ ማጥናት እንደጀመረ ከኢትዮጵያ የማሪታይም ጉዳዮች ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያሳያል ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሁለት ሳምንታት በፊት በሀገሪቱ ካሉ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር ባደረጉት ቆይታ ሀገሪቱ አሁን ላይ የምጽዋ ወደብን በተቻለ ፍጥነት ወደመጠቀም እንደምትገባም ተናግረው ነበር ።
ኢትዮጵያ የኤርትራን ወደቦች የምትጠቀምበትን ሁኔታ አስመልክቶ ጥናት የሚያደርግ የተለያዩ ዘርፍ ባለሙያዎችን የያዘ የጥናት ቡድንን የቀድሞው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አምባሳደር ግርማ ብሩ እየመሩት ነው ።
በጥናቱ ውጤት ላይም ኢትዮጵያ ምጽዋና አሰብን ስትጠቀም ምን አይነት ስትራቴጂ ይኖራታል ? ሁለቱ ሀገራትስ ከወደብ አንጻር ምን አይነት ግንኙነት ነው የሚኖራቸው ? የሚለው ጉዳይ ግልጽ ተደርጎ እንደሚቀመጥም ምንጮቻችን ነግረውናል ።

ይህም ብቻ ሳይሆን ወደቦቹን መጠቀም ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚያዊ አዋጭነታቸውስ ምን ይመስላል ? የሚለው ጉዳይም እየተፈተሸ እንደሆነ ስምተናል። ።
የጥናቱን ሂደት ከሚያውቁ ባለሙያዎች እንደሰማነው ኢትዮጵያ አሁን ላይ የአሰብንና ምጽዋ ወደብን መጠቀም መጀመሯ በጅቡቲ ላይ ብቻ ከተንጠለጠለው አካሄዷ አንጻር እንደ አማራጭ መቀመጡ መልካም መሆኑ ቢነሳም ፤ ወደቦቹ አሁን ካሉበት ሁኔታ አንጻር ግን ኢኮኖሚያዊ አዋጭነታቸው በተወሰኑ ምክንያቶች ሳቢያ ብዙም እንዳልሆነ ይነሳል ።

ከምክንያቶቹ አንዱ የኤርትራ ወደቦች አሁን ላይ ያላቸው አቋምና ኢትዮጵያ ከጦርነቱ በፊት ስትጠቀምበት ታስገባ የነበረቻቸው እቃዎች አንጻር አሁን ላይ ልዩነታቸው እየሰፋ መምጣቱ ነው ።
ኢትዮጵያ ባለፉት አመታት እጅግ እያደገ ከመጣው የገቢና ወጪ ንግድ አንፃር የመርከቦቿ የጭነት አቅምም ከጊዜ ወደጊዜ በእጅጉ ጨምሯል ።

ጅቡቲም በወደብ ላይ ብዙ ኢንቨስት ያደረገችው ከኢትዮጵያ የምታገኘውን ተጠቃሚነት ከፍ ለማድረግ መሆኑ ይታወቃል። ።
ኢትዮጵያም ከዲፒ ወርልድ(DP World) ጋር በርበራ ድርሻ ወስዳ በአመት 1.3 ሚሊዮን ኮንቴነር የሚያስተናግድ ወደብ ለማልማት የተዘጋጀችውም ለዚሁ ነው ።
የኤርትራ ሁለቱ ወደቦች ደግሞ የኢትዮጵያን ግዙፍ የገቢ እቃ ድርሻ ከመያዝ አንጻር አሁን ላይ ብዙ እንደሚቀራቸው የሚሰራውን ጥናት በቅርበት የሚያውቁ ምንጮቻችን ያስረዳሉ ።
ኢትዮጵያ አሁን ላይ ካሏት 11 መርከቦች ዘጠኙ በእለት ከእለት ስራ ውስጥ ናቸው ።
የሀገሪቱ ህዝብ ፤ የግንባታው እና የኢንዱስትሪው ዘርፍ የገቢ እቃዎች ፍላጎት መጨመሩን ተከትሎ የመርከቦች የመሸከም አቅምም ጨምሯል ።
የመርከቦች የመሸከም አቅም ሲጨምር ደግሞ በወደቦች ዳርቻ ያለው የማንሳፈፊያ ውሃማ ቦታ መርከቡን እንዲያንሳፍፍ ዝቅ ብሎ እንዲለማ ማድረግ ያስፈልጋል ፤ ካልሆነ መርከቡ ከመሬት ጋር የሚጋጭ ይሆናል ።
ጅቡቲ በቻይናውም ሆነ በዲፒ ወርልድ ያለማቻቸው የወደቦች ዳርቻ ጭነታቸው የከበዱ መርከቦችን ማንሳፈፍ በሚያስችል ሁኔታ ጥልቀት እንዲኖራቸው ሆነው ተሰርተዋል ።
አሰብና ምጽዋ ግን የድሮ የኢትዮጵያን መርከቦች የመሸከም አቅምን ከግንዛቤ ያስገቡ ናቸው ።
በሌላ በኩል የወደቦች ዳርቻ በአንዴ የሚያራግፉ መርከቦችን የመያዝ አቅማቸውም ዝቅተኛ ነው።
የጅቡቲ ወደብ በአንዴ 14 መርከቦችን እንዲያራግፉ የሚያስችሉ በርዞች (መቆሚያና ዕቃ ማራገፊያ) አሉት ።
የኤርትራው የአሰብ ወደብ ግን የመርከቦች ክብደት ውስንነቱ እንዳለም ሆኖ ሰባት መርከቦች በአንዴ የሚያራግፉበት ዳርቻ ነው ያለው።

እነዚህ ሁሉ ጉድለቶች ቢኖሩም ኤርትራ ምጽዋ ወደብን ኢትዮጵያ እንድትጠቀምበት በሳምንታት ጊዜ ውስጥ ዝግጁ ለማድረግ አሰናድታዋለች ።
ኢትዮጵያም ወደቡን ለመጠቀም ዝግጁ ናት መባሉ የተጀመረው ዲፕሎማሲ ላይ የኢኮኖሚ ትስስር ለመፍጠርና መጠነኛ አማራጭ ለማምጣት ያለመ እንጂ ከዚያ የሚያልፍ ጥቅም የሚያመጣ አይደለም ይላሉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ባለሙያዎች ።
አምባሳደር ግርማ ብሩ የሚመሩትና ከማሪታይም ጉዳዮች ባለሰልጣንና ከባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት የተውጣጡ ባለሙያዎችን ያካተተው የጥናት ቡድንም እነዚህን የወደቦቹን ጎድለቶች እንዴት ማሻሻል ይቻላል የሚሉ ጉዳዮችን ጨምረው እየተመለከቱ ነው።

ምናልባትም ኢትዮጵያ ከወደቦቹ ላይ ድርሻ በመውሰድ ልታለማ የምትችልበት አማራጭ አብሮ እንደሚታይ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያ የኤርትራን ወደቦች ስትጠቀም በክፍያ ይሁን አይሁን እስካሁን ባይገለጽም የጥናት ቡድኑ የወደብ ታሪፍ ጉዳይንም እንዲያጠና ታዟል ።
ሁለቱ ሀገራት በእንዲህ አይነት መሰረተ ልማቶች ሲተሳሰሩም የሚሰሩባቸው ህጎች አምባሳደር ግርማ ብሩ ከሚመሩት ቡድን የሚጠበቅ ነው ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar