ከጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን በመንበረ ፓትርያርኩ ማረፊያቸው የጠየቋቸው፤ የክልል ትግራይ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል፤
“በአቡኑ መመለስ ሁላችንም ደስተኞች ነን፡፡ በአሜሪካ ሌላ ፓትርያርከ፣ በአገራችንም ሌላ ፓትርያርክ እየተባለ ለረጅም ጊዜ እንደቆየ ሁላችንም የምናውቀው ነው፡፡ ይኼ የነበረው መራራቅ፣ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን አሜሪካ ሔደው፣ ቤተ ክርስቲያናችንም በራሷ ጥረት ስታደርግ እንደነበር እናውቃለን፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ አሜሪካ ከሔዱ በኋላ መቋጫ ያገኘበት ነው፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩን አብረው ይዘው በመምጣታቸው በጣም ትልቅ ደስታ ነው የተሰማን፡፡ እኔ በአጋጣሚ መንገድ ላይ አልተሳተፍኩም፡፡ ነገር ግን ዛሬ እጎበኛቸዋለኹ ሲሉ በሌላ ሥራ አብረን ነበርንና፣ እኔም ስላልጠየቅኋቸው ከእርስዎ ጋራ መሔዱ በጣም ጠቃሚ ነው በሚል ነው የመጣኹትና በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ ቅዱስነታቸውንም አግኝቻቸዋለሁ፡፡
ሁለቱንም ፓትርያርኮች በጋራ ስላገኘናቸው፣ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ብቻ ሳይኾን ለአገራችን ሕዝቦችም ትልቅ አብነት ነው የሚያሳየን፡፡ ይኼ መራራቁ በጣም ጎጅ እንደነበረ፣ ከቤተ ክርስቲያንም አልፎ ሕዝቡ ላይ የነበረው ስሜት እንዲራራቅ አድርጎ ስለነበረ፣ አኹን አማኙ ብቻ ሳይኾን የኢትዮጵያ ሕዝብም አንድ እንዲኾን፣ ተባብሮ አገሩን ለማልማት፣ ተባብሮ የአገሩን ሰላም ለማስጠበቅ የራሳቸውን ሚና እንደሚጫወቱ ስለምናምን በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ በጥሩ ኹኔታም ነው ያገኘናቸው፤ በዚህ ዕድልም ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋራ ተያይዘን ስለመጣን በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ “
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating