ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
እራሱን እንደሰየመ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ተናጋሪ ሆኘ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፣ ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ እና ጠቅላላ የአብይ አህመድ የኢትዮጵያ ቡድን ልዑክ በርካታ ሺ ኪሎ ሜትሮችን በመጓዝ ከእኛ ጋር ለመሆን ወደ አሜሪካ በመምጣታችሁ በጣም እናመሰግናለን፡፡
ብዙ ጊዜ እንዲህ ይባላል፣ “ርቀት ማለት ምንም ማለት አይደለም፡፡ ሰው የሚወ ደውን ሰው ለማግኘት የሆነዉን ሩቅ መንገድ ይሄዳል ፡፡“ ሁላችሁም እኛን ለማየት መጣችሁ ምክንያቱም እኛ በአሜሪካ የምንገኝ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማለት ለእናንተ ትልቅ ነገር ነው፤ እናም ይህንን ዓላማ ሰንቃችሁ እኛ እናንተን እንደምንወዳችሁ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ እናንተም እኛን በመውደዳችሁ ልታዩን መጣችሁ!
በእርግጥ ከእኛ ጋር ለመሆን ወደ እኛ ወደ ወገኖቻችሁ ወደዚህ ስትመጡ ይህንን ለማድረግ ነገሮች ሁሉ ቀላል እንዳልሆኑ እናውቃለን፡፡
“ብዙውን ጊዜ ጉዞ ያደርጋሉ” … እየተባለ በተደጋጋሚ የሚነገር አሰልች ትችት እንደሚቀርብበዎ እንሰማለን፡፡
ምክንያታዊ ባልሆነ መንገድ፣ በተደጋጋሚ ወይም ደግሞ በሚቆጠቁጥ መልኩ እንዲህ በማለት ሲናገሩ እንሰማለን፣ “የዲፕሎማሲ ፕሮቶኮልን እየጣስክ ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ መንግስታዊ ጉብኝት ማድረግአለብህ“ ወዘተ፣ ወዘተ…
መንግስታዊ ጉብኝትን ወደኋላ በማቆየት እና በስደት ላይ ለሚገኙ ዜጎቹ ቅድሚያ በመስጠት የአንድ ሀገር መሪ እንደዚህ ያለ ጉብኝት ሲያደርግ ምን ያህል ታሪካዊ እና ያልተጠበቀ እንደሆነ እናውቃለን፡፡
በዓለም የዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ እንደዚህ ያለ ነገር በፍጹም ተከስቶ አያውቅም፡፡
ከእኛጋር ለመሆን ረዥሙን ጉዞ ተጉዘው ሲመጡ በርካታ ሰዎች ያላዩትን እኔ ጥቂት ነገሮችን ተመልክቻለሁ፡፡
በርካታ ሰዎች በማህበራዊ መገናኛዎች የእርስዎን ቪዲዮ በሚመለከቱ ጊዜ የአረብ ብረት ሰው ጠንካራ ሰው እያሉ እንደሚያስቡ እገምታለሁ፡፡
ሆኖም ግን ከእርስዎ ጋር በነበርኩባቸው በጥቂት ሰዓታት ውስጥ በጉዞው ጫና፣ በሚያደርጓቸው ንግግሮች እና እንቅልፍየለሽ ምሽቶች (የምን እንቅልፍ? የምን ምሽት?) ምን ያህል አድካሚ እና አስቸጋሪ እንደነበር አስተውያለሁ፡፡
ቅንጣት ያህል ጊዜ ሳይኖርዎ ፍጹም በሆነ ድካም ውስጥ ወድቀው እንደነበር አስተውያለሁ፡፡
ምንም ሳያቋርጡ ከአንድ ስብሰባ ወደ ሌላ ስብሰባ ለመሄድ ሲዘጋጁ እመለከት ነበር፡፡
ሆኖም ግን በእርስዎ ላይ በነበረው ጫና እና እርስዎን ለማግኘት በነበረው ከመጠን ባለፈ ፍላጎት አንድም ጊዜ ቅሬታ ሲያቀርቡ አልተመለከትኩም፡፡
ሆኖም ግን እኔ ለመመልከት የቻልኩት እንደ እኔ እና እኔን እንደመሳሰሉ ዓይነት ሰዎች ለሀገራቸው ደህንነትና ብልፀገና የደከመ አቅዋም ሲወስዱ ነው ያየሁት።
ይህንን ለማመን እቸገራለሁ፡፡ ሆኖም ግን እናንተን በማይበት መስታወት አኛን ራሳችንን ሳይ የተመለከትኳቸው ሲንሳፈፉ የነበሩ ምስሎች ስግብግብነት፣ ደንታቢስነት እና እብሪተኛነት ነበሩ፡፡
በዩቲዩብ ካወቀወኋችሁ ጊዜ ጀምሮ ለእናንተ ለሁላችሁም ታላቅ አክብሮት አለኝ፡፡
ሆኖም ግን ከእናንተ ጋር በአካል በማየቴ እና በመመልከቴ አክብሮቴን እጅግ በጣም አበዛው እና ገደቡን እንዲያልፍ አደረገው፡፡
ሊደረግ የማይችለውን ነገር በተግባር ፈጽማችኋል፡፡
በየቀኑ እንዲህ የሚለውን የማንዴላን መርህ በተግባር አረጋግጣችኋል፣ “ተግባራዊ እስከሚደረግ ድረስ ሁልጊዜየማይቻል ይመስላል፡፡“
የእኔ ታላቁ ህልሜ የኢትዮጵያ ወጣቶች የሀገራቸውን ዕጣ ፈንታ እራሳቸው ሲወስኑ መመልከት ነበር፡፡ ለዚህም ነው ላለፉት አስራ ሶስት ዓመታት ያህል ያለምንም ማቋረጥ ስሰብክ የቆየሁት፡፡
ሆኖም ሌት እና ቀን መከራዬን ሳይ የቆየሁ ቢሆንም የማይቻል ህልም ነው የሚል ስሜት ይሰማኝ ነበር፡፡
ሁልጊዜ መጨረሻውን ባሰብኩ ቁጥር አቅሌን በመሳት እንቀጠቀጥ ነበር፡፡ ከፍተኛ ጩኸት በማሰማት ወይም ደግሞ በመንሾካሾክ ሊጠናቀቅ ይችላልን? ወይም ደግሞ በአንድ ትልቅ መተቃቀፍ ዓይነት ሁኔታ?
የሚያሳዝነው ከሁሉም ለረዥም ጊዜ ኢትዮጵያ የተረገመች ሀገር መሆን አለባት በማለት አምን ነበር፡፡
ይህንን የማስበው ለምንድን ነበር?
ኢትዮጵያ ለበርካታ አስርት ዓመታት የረኃብ፣ የጦርነት፣ የሙስና እና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መገለጫ መታወቂያ ሰሌዳ ነበረች፡፡ በዚህ ምክንያት ልቤ ሁል ጊዜ ይሰበር ነበር ።
በአንድ ወቅት በጣም ተስፋ ቆርጨ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ ጋና እንድትሆን እመኝ ነበር፡፡
እ.ኤ.አ በ2009 ዓ.ም በተስፋ መቁረጥ ጥልቀት ውስጥ ሆኘ “ጋናውያን እኛ ያላገኘነው እነርሱ ያገኙት ምንድን ነው?“ በሚል ርዕስ ትችት ጽፌ ነበር፡፡
እንደ ጋናዊ ለመሆን እመኛለሁ በማለት ነበር ለዓለም ስናገር የቆየሁት፡፡
ጋና እና ኢትዮጵያ የተለያዩ ሀገሮች ቢሆኑም ቅሉ ሊጋሯቸው የሚችሏቸው በርካታ ተመሳሳይነቶች አሏቸው፡፡ ለዴሞክራሲ እና ለነጻነት የአፍሪካ መለያዎች/ፖስተሮች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ለረኃብ፣ ለተመጽዋችነት፣ ለጎሳ ክፍፍል እና የጥላቻ መለያ በመሆን ትታወቅ ነበር፡፡
እውነት ለመናገር በጋናውያን በጣም እቀናለሁ፡፡ ፍጹም የሆነ ዴሞክራሲ ስላላቸው ወይም ደግሞ ብዙም ጉዳት የሌለው ሙስና እና በሌሎችም ነገሮች ምክንያት አይደለም፡፡ ሆኖም ግን በትክክለኛው መንገድ ላይ በመጓዝ ላይ በመሆናቸው ምክንያት ነው፡፡ ሕዝቦቻቸው መንግስታቸውን የመምረጥ ስልጣን እንዳላቸው ተገንዝበዋል፡፡
ጎሳን እና ዘርን መሰረት ያደረጉ የፖለተካ ፓርቲዎችን በሚከለክለው እና እንዲህ በሚለው በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 55 (4) በጣም እቀናለሁ፣ “እያንዳንዱ የፖለቲካ ፓርቲ ሀገር አቀፋዊ መሆን አለበት፡፡ እናም አባልነትጎሳን፣ ኃይማኖትን ወይም ደግሞ ሌሎች ዓይነት ክፍፍሎችን መሰረት ያደረገ መሆን የለበትም፡፡“
ኢትዮጵያም አንድ ቀን የጋና ሕገ መንግስት አንቀጽ 55 (4) ዓይነት ቋንቋ እንዲኖራት ሁልጊዜ እመኛለሁ፡፡
እ.ኤ.አ በ2015 የአዲስ ዓመት መጀመሪያ በጣም ተስፋ ቆርጨ ነበር፡፡ በደርዘን የሚቆጠሩ ሊሆኑ የማይችሉ ህልሞች እና እስከዚያ ድረስ አልሜው የማላውቀው ዓይነት ህልሞችን በማለም ዝርዝራቸውን በትችቴ ውስጥ በማካተት አቅርቤ ነበር፡፡
ኢትዮጵያ በሰላም፣ በታሪኳ የተባበረች ሀገር እና ህዝቦቿ እየተሰቃዩ የሚገኙባት፣ እህትማማችነት እና ወንድማማችነት፣ በጎሳችን ሳይሆን ሰው በመሆናችን ብቻ መተባበር እንዳለብን፣ የመርህ መከበር፣ እኔ የወንድሜ እና የእህቴ ጠባቂ ነኝ፣ ሰብአዊ መብት በኢትዮጵያ የመንግስትን ስህተት መለየት እንዳለበት የሚሉ ህልሞች ነበሩ፡፡
ሆኖም ግን አመጾች ሲነሱ እና ህዝቦች ለአገዛዙ የማይበገሩ ሆነው የሚቀጥሉበትን ጊዜ በማስታወስ ላንግስተን ሁስ እንዲህ በሚሉት ግጥሞቻቸው እያዋዙ የሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች አእምሮዬን ኮረኮሩት፡
ህልም የተለየ ሲሆን ምን ይሆናል?
በጸሐይ ላይ እንደተሰጣ የወይን ፍሬ ብን ብሎ ሊደርቅ ይችላል?
ወይስ ደግሞ እንደ ቁስል ይመግላል እናም መምገሉን ይቀጥላል?
እንደበሰበሰ ስጋ ይሸታልን?
ወይስ ደግሞ እንደ ሽሩፕ ይጣፍጣልን?
እንደ ትልቅ ሸክም ሊወድቅ ይችላል?
ወይስ ደግሞ ሊፈነዳ ይችላልን?
ሙሉ በሙሉ ቢፈነዳስ?
በጣም በጣም አጭር ጊዜ ውስጥ አብይ አህመድ የሚፈነዳውን የጥላቻ ቦምብ አመከኑት!
ሆኖም ግን እንደ ላማንቻው ሰው እንደ ዶን ኩይቴ በማይደረሰው ኮከብ ላይ ለመድረስ ሁልጊዜ እንደማምነው የማይቻሉ ህልሞችን ከማባረር በፍጹም አልቆምም፡፡ እናም ሁልጊዜም አልማለሁ፡፡ የማይቻለው ህልም/አዎ እናም እደርሳለሁ/ በማይደረሰው ኮከብ፡፡
የማይደረስበት የኢትዮጵያዊነት ኮከብ ህብረት በኢትዮጵያ ሰብአዊነት፣ ነጻነት፣ ዴሞክራሲ፣ ሰብአዊ መብት፣ የሕግ የበላይነት…. ናቸው?
በሎስ አንጀለስ በአንድ ክፍል ውስጥ ከእርስዎ ጋር ተቀምጨ በነበርኩበት ጊዜ እርስዎን በማየት እደነቅ እና ታላቅ ክብር በመስጠት ድብልቅልቅ ባለ ስሜት ውስጥ ነበርኩ፡፡
ሌሎቻችን ከዳር ቆመን ስናጨበጭብ እና ስናደንቅ እርስዎ ከባዱን ሸክም ሁሉ ሲሸከሙ እመለከት ነበር፡፡
በርካታዎቻችን በአሜሪካ የምንኖር ሰዎች የተደላደለ ኑሮ እየኖርን ህዝባችን ሲጎዳ መመልከት ፍትሀዊ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን ልናደርግ የምንችለው ነገር እናንተን ማገዝ ነው፡፡
ሁሉንም ከባድ ሸክም ሁሉ እርስዎ እየተሸከሙ እኛ በርካታዎቹ እየተመለከትን ዝም በማለት ያለስራ የምንቀመጥ ከሆነ ይኸ አሳዛኝ ሁኔታ ነው፡፡
እኛ ልንሸከመው የምንችለው ብቸኛው ነገር ከስሞቻችን በኋላ የሚቀርቡትን አህጽሮዎች ማለትም ፒኤች .ዲ፣ ኤም.ዲ፣ ጀ.ዲ፣ ኤም.ኤ፣ የዲግሪ ጋጋታ ነው፡፡
እኔ በጣም ሀፍረት ይሰማኛል!
እያንዳንዱ ሰው እርስዎ ሁሉም ዓይነት መፍትሄዎች እንዳሉዎት አድርጎ ያስባል፡፡
በእርስዎ ላይ የሚቀርቡት ትችቶች ምን ስህተቶች እንደሰሩ፣ ምን እንዳላደረጉ ወይም ደግሞ ምን ማድረግ እንዳለብዎ ይነግሩዎታል፡፡
የእርስዎ ደጋፊዎች ለእርስዎ መልካም ነገርን ይመኛሉ፡፡ እናም ጸሎት ያደርጉልዎታል፡፡
በሎስ አንጀለስ ከእርስዎ ጋር በአንድ ክፍል ውስጥ ተቀምጠን በነበርንበት ጊዜ ማድረግ የምችለው ነገር ቢኖር ለእራሴ ምቾት የሚሰጡኝን (ለእርስዎ ሳይሆን) እና እንዲህ የሚሉትን ከሮበርት ፍሮስት የስንኝ መስመሮች ላቅርብ፡
ጫካዎቹ አስደሳች፣ ጥቅጥቅ ያሉ እና ጥልቅ ናቸው፡፡
ሆኖም ግን ለመጠበቅ ቃልኪዳን አላቸው፡፡
እናም ከመተኛታቸው በፊት ብዙ ኪሎ ሜትሮችን መጓዝ አለባቸው፡፡
መልካም ኃያሉ አምላክ ሆይ በኔልሰን ማንዴላ እና መልካም ነገር እና ይቅርባይነት እየተባለ በሚጠራው መንገድ ለመጓዝ በርካታ ኪሎ ሜትሮች ይቀሯችሃል፡፡
ማንዴላ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ታላቁን ተራራ ከወጣህ በኋላ ሌሎች ሊወጡ የሚችሉ በርካታ ትናንሽ ኮረብታዎች ይቀራሉ፡፡“
በመልካም ነገር እና ይቅርባይነት መንገድ በመጓዝ በዚያ በተራራው ጫፍ ወደምትገኘው እና ኢትዮጵያ እተባለች ወደምትጠራው ከተማ ለመድረስ ስንት ትልቅ ተራራ እና በርካታ ትናንሽ ኮረብታዎችን መውጣት ያስፈልጋል?!
ምንም ዓይነት ፍርሀት እንዳይሰማዎት! ብቻዎትን አይደሉም፡፡ እኛ ወገንዎችዎ ከእርስዎ ጋር ነን፡፡
በአሜሪካ በሚገኙት ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች ላይ የተመለከቷቸው ፍቅር፣ መከባበር እና አድናቆት በመልካም ነገር እና በይቅር ባይነት መጨረሻ በሌላቸው መንገዶች ሲጓዙ እና ወደ ሀገር ቤትም ሲመለሱ የፍቅር ባቡሩን በቀጣይነት በሚሾፍሩበት ጊዜ ከጎንዎ ያለ መሆኑን ያመላክታል፡፡
አሜሪካንን ሲያቋርጡ እና ከእኛ ጋር ለመነጋገር እና እኛን ለመጎብኘት ሲመጡ ጥልቅ ፍቅር፣ ክብር እና አድናቆትን አሳይተውናል፡፡
በእኛ ፍቅር እንደ ማግኔት ስበነዎታል፣ ባሳየንዎት ክብር ብርታትን ሰጥተንዎታል፣ እናም ባሳየንዎት አድናቆት ስሜትዎን እንደ ኤሌክትሪክ ነዝሮዎታል በማለት ብናገር አጋነንክ እንደማልባል አስባለሁ፡፡
በሎስ አንጀለስ ባደረግንልዎት አቀባበል ያልተደነቁ መሆንዎን በይፋ ተናግረዋል ምክንያቱም ሎስ አንጀለስ የዓለም የመዝናኛ ከተማ እንደመሆኗ መጠን ከዚህም በላይ የበለጠ ትይንት ማሳት እንዳለብን ይጠብቁ ነበር፡፡
ለዋሽንግተን ዲሲ እና ለሚኒያፖሊስ እንደሰጠነው ክብር ሁሉ እኛ በሎስ አንጀለስ የምንገኝ ወገኖችዎ እርስዎ ከሚጠብቁት በላይ በፍቅር እናንበሸብሸዋለን፡፡ እንግዲህ በዚህ ዓይነት መንፈስ ነው በሎስ አንጀለስ በገፍ በመውጣት አቀባበል ያደረግነው፡፡ ስለሆነም በቀጣይ ጊዜ ወደ ከተማ ሲመጡ ምን እንደሚጠብቁ እናውቃለን፡፡
በሎስ አንጀለስ ስለሚያደርጉት ጉብኝት በሚናገሩበት ጊዜ በጋላን ማዕከል እርስዎን ለመቀበል ሲጮሁ የነበሩትን እና በደስታ መንፈስ እንባቸውን ሲያፈሱ ስለነበሩት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ያስታውሳሉ፡፡
ሁላችንም እንባዎቻችንን ለማስቆም ስንታገል ስናሳይ የነበረውን ፈገግታ ያስታውሳሉ፡፡
እንግዲህ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ነው በሎስ አንጀለስ ፍቅራችንን ለማሳየት የቻልነው፡፡
ላለፉት 27 ዓመታት በአሜሪካ የዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን መንፈሶች እንደበረዶ ቀዝቅዘው ቆይተዋል፡፡
በሶስት ቀናት ጊዜ ውስጥ እርስዎ በመምጣት እሳት ለኮሱበት፡፡
ለዚህም ነው አብይ ! አብይ! በማለት ስንጮህ የነበርነው፡፡ ወደ ሀገራችን ለመሄድ ዝግጁ ሆነናል፡፡
ዝም ብዬ የምጮህ መስየ እንድታይ አልፈልግም፡፡
እናም “ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከዚህ ቀደም ተናግሪያለሁ“ ስል ትንሽ ቅር ይለኛል ። ግን ያው እንዳልኮት ነው ሁሉም የተከሰተው ።
በዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ስም ሆኘ እባክዎትን፣ እባክዎትን ወደ ዩ ኤስ አሜሪካ ይምጡ እና እንግዳችን ይሁኑ በማለት እ.ኤ.አ ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ጽፌው በነበረው ትችቴ ላይ እንዲህ በማለት ቃል ኪዳን ገብቸ ነበር፡:
ወደ ዩኤስ አሜሪካ የሚመጡ ከሆነ “መጣሁ፣ አየሁ“ በማለት በአሜሪካ የኢትዮጵያውያኖችን እና የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያንን ልቦች እና አእምሮዎች በመማረክ ድል አድርጊያለሁ ብለው እንደሚያውጁ ምንም ዓይነት ጥርጣሬ የለኝም፡፡
ደህና፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በአሜሪካ የኢትዮጵያውያኖችን እና የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያንን ልቦች እና አእምሮዎች አልማረኩም ?
በዚያ ደብዳቤየ ውስጥ ሌላ ምን ተናግሬ ነበር? በአጭሩ እንዲህ ብየ ነበር፣
“የሚመጡ ከሆነ የህዝቡን ቀልብ በመሳብ ከፍተኛ አድናቆትን ያገኛሉ፡፡ በቀጥታ! ስለዚህ ጉዳይ ምንምዓይነት ጥያቄ የለም! ወለሉን ወደታች ያወርዱታል፣ ጣራውንም ወደ ላይ ከፍ ያደርጉታል፡፡ መድረኩን ሙሉበሙሉ ይቆጣጠሩታል፡፡ በኢትዮጵያውያን ወጣት ትውልዶች እንደ ሮክ ስታር የሙዚቃ አቀንቃኝ በመደነቅይስተናገዳሉ ፡፡“ ቤ ነበር ።
ደህና፣ በሚኒያፖልስ የቅዱስ ፓውል ፕሬስ እንዲህ በማለት ጽፏል፣ “በታርጌት ማዕከል ለኢትዮጵያውያንጠቅላይ ሚኒስትር በ10,000 ሰዎች የሮክ ስታር (የሙዚቃ ታዋቂ ያህል) ዓይነት ደማቅ አቀባበልተደረገላቸው፡፡“
ይህ እንደማያተራጥር እንደሚሆን ቀደም ሲል ነግሬዎት ነበር!
በዚያው ተመሳሳይ ደብዳቤዬ እንዲህ በማለት በተጨማሪ ነግሬዎት ነበር፡
“በዩኤስ አሜሪካ የሚኖሩት በርካታዎቹ እርስዎን ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጥልዎታለሁ፡፡በመካከላችን በመገኘት ስለብሄራዊ እርቅ፣ ስለሀገር አንድነት እና የተወደደውን የኢትዮጵያን ማህበረሰብእንዴት መገንባት እንደምንችል ሲናገሩ ለመስማት እንፈልጋለን፡፡ ባስቸክዋይ መምጣት አለቦት ብዬ ነበር” ።
ለበርካታ አስርት ዓመታት በተሳሳተ አገዛዝ እና በመጥፎ አስተዳደር ስትናጥ የቆየችውን ሀገራችንን ከውድቀትለማዳን ለሚያቀርቡት ጥሪ ምን ያህል ዝግጁ እንደሆንን እና ለተግባራዊነቱም ችሎታው እንዳለን ለመናገርምንም ዓይነት ጊዜ አናጠፋም“ ነበር ያልኩት፡፡
በእርግጥም ለበርካታ አስርት ዓመታት በተሳሳተ አገዛዝ እና በመጥፎ አስተዳደር ስትናጥ ለቆየችው ለእርስዎ የሀገር ማዳን ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁዎች ሆነን እና ብቃቱ ያለን ወገኖችዎ ሆነን አላገኙንምን?
“አብይ! አብይ! እርስዎን እንደግፋለን፣ እናም ወደ ሀገራችን ለመጓዝ ዝግጁዎች ነን” ስንል የነበረው ለዚህ እኮ ነበር !
በዚያ ደብዳቤየ ውስጥ ወደ እኛ ቢመጡ የምንናገረውን በተግባር የምናሳይዎ መሆናችንን አልተነበይኩምን?
ጥቂቶቻችን ስለብህራዊ እርቅ፣ ሰላም፣ ይቅርባይነት እና ስለዴሞክራሲ የሚናገሩትን በተግባር እንደሚያደርጉ እና ሌላ ምንም ማለት እንዳልሆነ ተናግረን ነበር፡፡ አሁን እግሮችዎ የት እንዳሉ መናገር እና ስለብህራዊ እርቅ፣ ሰላም፣ ይቅርባይነት እና ስለዴሞክራሲ የሚናገሩትን በተግባር እንደሚያሳዩ ይጠበቅብዎታል፡፡
በመካከላችን በመገኘት ስለብህራዊ እርቅ፣ ሰላም፣ ይቅርባይነት እና ስለዴሞክራሲ የሚናገሩትን በተግባር ያሳዩ በመሆንዎ ቃላት ሊገልጹት ከሚችለው በላይ ኮርቸብዎታለሁ፡፡
ሆኖም ግን እነርሱን እና እርስዎን እመለከት ነበር፡፡
ማንዴላ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ከመንጋው መካከል መሪ የሚወጣበት ጊዜ አለ፡፡ እናም በአዲስ አቅጣጫ እናበእራስ የመተማመን ስሜት በመመራት የእርሱን ህዝብ በትክክለኛው መንገድ ይመራል፡፡“
እነዚያ በሕዝብ የዘረፋ ሀብት የደለቡት እና ኃይል አለን ብለው የሚመኩት በአሉታዊ አስተሳሰባቸው እርስዎን ወደኋላ በመጎተት በጎሳ ፖለቲካ ሻወር ለመዘፈቅ፣ ወደ ቀድሞው የጥላቻ፣ እምነት ማጣት እና የጥርጣሬ ዘመን ለመመለስ ሲፍጨረጨሩ እመለከት ነበር፡፡
ጥቂቶች ከከንፈሮቻቸው የክፍፍል፣ የኃይማኖት ጽንፈኝነት እና ትምክህተኝነት ቃላትን እያወጡ እጆቻቸውን በአየር ላይ ሲያውለበልቡ አይቻለሁ፡፡
ጥቂቶች በጎሳ የክፍፍል ፖለቲካ ባህር ውስጥ ከሰመጠው እና አብረው የሰመጡት እርስዎንም ይዘው ለመስመጥ ሲፍጨረጨሩ ተመልክቻለሁ፡፡
ሆኖም ግን ምንም ነገር ማግኘት አይችሉም፡፡ እርስዎ በትክክለኛው መድረክ ላይ በመቆምዎ እኮራለሁ፡፡ ልክ እንደቶም ፔቲ ሙዘቃ፡፡
ደህና፣ እኔ ወደኋላ አልመለስም (ከእርቅ፣ ሰላም፣ ይቅርባይነት እና ዴሞክራሲ መልዕክት)፡፡
በፍጹም ወደኋላ አልመለስም፡፡
ከሲኦል በር ልትገትሩኝ ትችላላችሁ፡፡
ሆኖም ግን በምንም ዓይነት መልኩ ወደኋላ አልመለስም፡፡ (ከእርቅ፣ ሰላም፣ ይቅርባይነት እና ዴሞክራሲ መልዕክት)፡፡
በፍጹም በዓላማየ ጸንቼ እቆማለሁ፡፡ (ለእርቅ፣ ለሰላም፣ ለይቅርባይነት እና ለዴሞክራሲ)፡፡
ወደየትም አቅጣጫ ዝንፍ አልንልም፡፡
እናም ወደኋላ ከሚጎትተኝ (ከጥላቻ፣ ከኃይማኖት ጽንፈኝነት እና ከጥልቅ ጥላቻ) ከዚህ ዓለም እራሴን እጠብቃለሁ፡፡
በአቋሜ ጸንቼ እቆማለሁ፡፡
በምንም ዓይነት ሁኔታ ወደኋላ አላፈገፍግም፡፡
አሁን እርስዎ ምን ዓይነት ሰው እንደሆኑ እያንዳንዱ ሰው ያውቃል፡፡
አብይ አህመድ የተግባር ሰው ናቸው፡፡ የጥቂት ቃላት እና የብዙ ተግባሮች ባለቤት ሰው ነዎት፡፡ በሚናገሩበት ጊዜ ምን ለማለት እንደፈለጉ በትክክል ያውቃሉ፡፡ የሚያደርጉትን የሚናገሩ እና የተናገሩትን የሚተገብሩ ሰው ነዎት፡፡ አብይ አህመድ በሚናገሩበት ጊዜ እያንዳንዱ ሰው ያዳምጣል፡፡
የአብ አህመድ ቃላት የተጨቆኑ እና የተሰበሩ ልቦችን ይፈውሳሉ፡፡
ማንም ሰው ቢሆን የቃላትን ኃያልነት ለማወቅ ከፈለገ አብይ አህመድን ማዳመጥ ይኖርበታል፡፡
ከአፋቸው የሚወጣው እያንዳንዱ ቃል ስሜትን ይቀሰቅሳል፣ በፍቅር እና በጥበብ እንድንሞላ ያደርጋል፡፡ እናም በሰላ አመክንዮ እንድንሞላ ያደርገናል፡፡
ከጥላቻ፣ ከክፍፍል እና ከጥልቅ ጥላቻ ለመነገድ ስለሚናገሩ እርባና ቢስ ተናጋሪዎች በጣም አዝንላቸዋለሁ፡፡ የብልጠት ጥያቄዎችን በማቅረብ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ማጥመድ የሚችሉ ይመስላቸዋል፡፡
ሆኖም ግን የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ምላሾች ምንም ዓይነት እንከን በሌለበት መንገድ ይቀርባሉ፡፡ የጥላቻ አራጋቢዎች በጥላቻ የተሞሉ ጥያቄዎቻቸውን በልቦቻቸው ውስጥ አጭቀው የጎታች ድርጊቶቻቸውን ይቀጥላሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የእነርሱን አፍራሽ አሉታዊ ኃይል እንዴት አድርገው ወደ መልካሙ እና አዎንታዊ ኃይል እንደሚለውጡት መመልከት እጅግ በጣም አስደናቂ ነገር ነው፡፡
ላለፉት 13 ዓመታት እንዲህ በሚለው በማንዴላ መርህ ስመራ ቆይቻለሁ፣ “አንድ ሰው ከሌሎች በምላሹምንም ነገር ሳይጠብቅ ያለውን ጊዜ እና ኃይል ሌሎች ሰዎችን በመርዳት ከማዋል የበለጠ ስጦታ የለም፡፡“
ማንም ቢሆን ከማንዴላ መርህ ጋር አብሮ ካልኖረ በስተቀር ትክክለኛ ትርጉሙን ሊገነዘብ አይችልም፡፡ ከማንዴለ መርህ ጋር እየኖርኩ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ! ከፍተኛውን ከበሬታ ቸረውኛል፡፡ እናም “የኢትዮጵያ ስጦታ“ በማለት ሲጠሩኝ ቃላት ሊገልጹት ከሚችሉት በላይ በደስታ ተውጨ ነበር፡፡ ምንም ዓይነት ነገር መናገር የማልችል በድን ሆኘ ነበር!
በእውነት ከምንም ጥርጣሬ ወይም ጥያቄ በላይ በሰው ለኢትዮጵያ ከእግዚአብሄር የተሰጠ ስጦታ መባል በህይወቴ አግኝቸው ከማላውቀው ክብር በላይ ነው፡፡
በምወደው፣ በማደንቀው እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በማክብረው ሰው “የኢትዮጵያ ስጦታ” ተብሎ መጠራት በፍጹም ያልጠበቅሁት እና በእርግጥም የማይገባኝ ነው፡፡
ለተሰጠኝ ታላቅ ክብር እጅግ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ ለእርስዎም እግዚአብሄር ታላቁን ክብር እንዲያጎናጽፈዎ እጸልያለሁ!
ወደ አራት ወራት ገደማ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የፍቅርን፣ የይቅርባይነትን፣ የእርቅን፣ የጨዋነትን፣ የድፍረትን፣ የክብርን፣ የእውነተኛነትን፣ የታማኝነትን፣ የጓዳዊነትን እና የመተሳሰብን ሞገስ አስተምረውናል፡፡
በፍቅር፣ በነጻነት፣ በእኩልነት እና በፍትህ የመኖር የተለየ እና የተሻለ መንገድ እንዳለ አሳይተውናል፡፡
ማንዴላ እንዲህ ብለው ነበር፣ “አሸናፊ በምንም ዓይነት እጅ የማይሰጥ ህልመኛ ነው፡፡“
እርስዎ ወደ አሜሪካ በሚመጡበት ጊዜ ሁላችንንም አሸናፊዎች አድርገውናል፡፡
ሁላችንም ኢትዮጵያ ከአምባገነናዊ አገዛዝ እና ከጭቆና ነጻ እንድትሆን የምንመኝ ሁሉ በአሁኑ ጊዜ አሸናፊዎች ነን፡፡
ሁላችንም ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት የመንግስትን ስህተት የሚያርምባት ሀገር እንድትሆን የምንመኝ ሁሉ በአሁኑ ጊዜ አሸናፊዎች ነን፡፡
ሁላችንም ኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት የሚሰፍንባት፣ መንግስት ሕዝብን የሚፈራበት እና ፍትህ እንደ ምንጭ ውኃ የሚንቆረቆርባት ሀገር እንድትሆን የምንመኝ ሁሉ በአሁኑ ጊዜ አሸናፊዎች ነን፡፡
ሁላችንንም አሸናፊዎች አደረጉን፡፡ ምንም ዓይነት ተሸናፊዎች የሉም፡፡
ለአሸናፊነት ሚስጥራዊ ያልሆነው ቀመር ፍቅር፣ ይቅርባይነት እና ሰላም ነው፡፡ ማንም ቢሆን ይህንን ቀመር የሚጠቀም ሁሉ አሸናፊ ይሆናል!
በአሜሪካ የሚኖሩ ሁሉም መልካም ሀሳብ አላሚዎች እና ጥሩ እምነት ያላቸው ሁሉንም ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን በመወከል ማለት የምችለው እዚህ ከእኛ ጋር አብራችሁ ለመሆን በመምጣታችሁ “ጠቅላይሚኒስትር አብይ እና የአብይ ኢትዮጵያ ቡድን አመሰግናለሁ“ የሚል ነው፡፡
እርስዎ እዚህ በመገኘት አክብረውናል፡፡ እና እርስዎን በመልካሙም ሆነ በክፉው ነገር ከጎንዎ በመሆን ከልብ እንደግፈዎታለን፡፡
በወጣትነት ዘመኔ የጂሚ ሄንድሪክስ የአይዶል ሙዚቃ እንዲህ ይል ነበር፣ “የፍቅር ኃይል የኃይልን ፍቅርበሚያሸንፍበት ጊዜ ዓለም ሰላምን ታውቃለች፡፡“
ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አመራር የፍቅር ኃይል የኃይልን ፍቅር አሸንፏል፡፡ ሰላምን እናውቃለን፡፡
ዓለምን ለማሸነፍ ለእያንዳንዳችን የፍቅርን ኃይል ስለሰጡን እናመሰግናለን፡፡
ለአስራ ሶስት ዓመታት በስልጣን ላይ ላሉት እውነትን በመናገር እራሴን የሾምኩ ሰው ሆኘ ቆይቻለሁ፡፡
እ.ኤ.አ ሀምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም እርስዎ እውነትን ለእኛ ሲነግሩን በጋለን ማዕከል ተቀምጨ ነበር፡፡ እንዴት ዓይነት የሚጣፍጥ ክስተት! በህይወታችን በፍጹም ልንረሳው የማንችለው አጋጣሚን ነበር የሰጡን፡፡
ጥንታዊው የሮማን ገጣሚ አንድ ሰው እትብቱ ከተቀበረበት ሀገር በፍጹም ሊለያይ እንደማይችል ያለውን እንቆቅልሽ አቅርቧል፡፡ ጣፋጭነት ምን ማለት እንደሆነ እና በፍጹም ለመርሳት እንደማንፈቅድ ባላውቅም የእኛ የትውልድ ሀገራችን አፈር ሁላችንንም ይስበናል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ! እርስዎን፣ ለማ መገርሳን እና የአብይ አህመድ-ኢትዮጵያን ቡድን እቅፍ አድርጌ በምስምበት ጊዜ ወደ ግማሽ ምዕተ ዓመት ገደማ ያህል እረስቸው የቆየሁትን የትውልድ ሀገሬን አፈር ጣፋጭነት ቀምሸዋለሁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፣ ለማ መገርሳ እና የአብይ አህመድ-ኢትዮጵያ ቡድን ኢትዮጵያን ወደ ሎስ አንጀለስ ይዛችለሁልኝ ስለመጣችሁ እጅግ እጅግ በጣም አድርጌ አመሰግናችኋለሁ!
እንደመር፣ አንቀነስ፣ እንባዛ፣ አንከፋፈል!
ኢትዮጵያዊነት ዛሬ!
ኢትዮጵያዊነት ነገ!
ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ሀምሌ 30 ቀን 2010 ዓ.ም
Average Rating