www.maledatimes.com እኛ የምንመኘው ሰላም የትኛውን ነው? አንተነህ ጌትነት (የሶማው) ከባዕድ ሀገር ሜልበርን አውስትራሊያ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

እኛ የምንመኘው ሰላም የትኛውን ነው? አንተነህ ጌትነት (የሶማው) ከባዕድ ሀገር ሜልበርን አውስትራሊያ

By   /   August 12, 2018  /   Comments Off on እኛ የምንመኘው ሰላም የትኛውን ነው? አንተነህ ጌትነት (የሶማው) ከባዕድ ሀገር ሜልበርን አውስትራሊያ

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 0 Second

ሳላም ከሌለ ምንም ነገር የለም።በሰላም ጊዜ ሁሉም ነገር ይኖራል፤ሰላም ከጠፋ ግን ያለውም ሁሉ ይወድማል።
ለዚህም ምስክሩ የኢትዮጵያው ሱማሌ የቅርብ ጊዜ አስከፊ ትውስታችን ምስክር ነው።አሁንም ይህን እያየን በጎሳ
ፖለትካ እንገዳገዳለን።ስለዚህ እኛ ልንመኘው የሚገባን ሰላም ዘለቄታ ያለውን እንጂ ለጊዜው እፎይታ የሰጠንን ከሆነ
ነገ የበለጠ ዋጋ የሚያስከፍለንና ተስፋ የሚያስቆረጠን እንዳይሆን ከወዲሁ መጠንቀቅ ይገባናል።ለዚህ መፍትሔው የጎሳ
ፖለትካ ይብቃን የሽግግር መንግስት ይቋቋም ማለት የሚገባን ሳይረፍድብን አሁኑኑ መሆን እንደሚገባው ልንረዳ
ይገባናል ።ሰላም የሚመጣም የጎሳ ፖለቲካ ከኢትዮጵያ ምድር ተጠራርጎ ሲወጣና በምትኩ የሽግግር መንግስት
በማቋቋም ወደ ሕዝባዊ መንግስት የሚወስደንን ጎዳና ስንጠርግ ብቻ ነው።ይህ ሲሆን ጢቂቶቹ ሳይሆኑ የኢትዮጵያ
ሕዝብ ሙሉ በሙሉ የስልጣን ባለቤት ይሆናል ማለት ነው። ይህ እንዲሆን ነው የሽግግር መንግስት አስፈላጊነቱ።ይህ
ካልሆነ ግን ታጥቦ ጭቃ ከመሆን የዘለለ አይደለም!!!
ዶ/ር አብይ የተቀበሉት የምክክር ጉባኤ ሆነ የሽግግር ጉባኤ እኛ ለጊዜው ያልተረዳነው ትላንት በአንድ ዘር ጥላቻ
ላይ ፕሮፓጋንዳ ሲረጩ የነበሩት ቡድኖች በመሰብሰብ ከሆነ “አልሸሹም ዞር አሉ” እንደሚባለው ከዛሬ ፳፮ ዓመት
በፊት እንደነበረው ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ተብየው ከተከበሩ ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ በስተቀር ሁሉም ከአንድ ባህር የተቀዱ
ስለነበሩ የተፈፀመውን ሁኔታ የምናስታውሰው ነው።አሁንስ ያ ሁኔታ እየተደገመ እንደሆነ ፍንጭ ያሳየን በአንድ ዘር
ጥላቻ ብቻ የነበረቻውን ቡድኖች የተለየ ክብርና ትኩረት መስጠት ከአለፈው ጊዜ የተለየ የሚያደረገው የሰዎች መልክ
ስለተለወጠና እነዚህ ቡድኖች ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ በማለታቸው ብቻ ነው።ይህ የሚያሳየን ነገሮች ሁሉ “ከድጡ
ወደማጡ” እየሄዱ መሆነችውን ነው።
እስኪ ዶ/ር አብይ ስለ ሽግግር ቃል በድምጽ የሰማነውን በጽሑፍ እንደሚከተለው ይነበባል፦ ”ጉባኤን
በሚመለከት ይለያያል እግዲህ፦
-የምክክር ጉባኤ፣የሽግግር መንግሥት፣የሽግግር ጉባኤ እነዚህ ሃሳቦች በሁለት መንገድ ተነስተዋል።የሽግግር መንግሥት
የሚለው ከሆነ በግሌ ብዙ ያስፈልጋል ብዬ አላምንም፤አያስፈልግም ይጥፋ አይጥፋ በሚል ሳይሆን አላምንም በሱ።
ለምንድን ነው የማላምነው? በእኔ እምነት ሁሉም መንግሥት የሽግግር መንግስት ነው።ሁሉም መንግስት ቆይታው
አምስት ዓመት ነው።የማይሽጋገር ቋሚ የሆነ ስትራክቸራል / structural/ ነገር ሕዝብና ሀገር ነው እንጂ መንግስት
ተብሎ ቋሚ የሚባል ነገር የለም።ይህ ሃሳብ ለረዥም ዓመታት ከተቀመጡ የማይነሱ ሰዎች ስለምናውቅ የድሮ ጥያቄ
ነው ብየ የማስበው።እኔ አስፈላጊ ነው ብዬ አላስብም።ኢትዮጵያን ጠንካራ ሰው ከሆነ ለሁለት ተርም/term/ በላይ
ማገልገል አስፈላጊ ነው ብዬ አላምንም።መስረቅ፣ኒፖቲዝም/ nepotism/ እና ሌላ ኢንተረስት/interest/ ካለ ጥሩ ሊሆን
ይችላል።ለማገልገል ከባድ ነው።ሁለትነ ሦስት ሰዓት እየተተኛ ማገልገል አይቻልም።የሽግግር መንግስት የሚለው ሃሳብ
ድሮ ተቀምጦ የማይነሱ ሰዎች ስላስቸገሯችሁ ከፍራቻ የመጣ ይመስለኛል።አሁን የሚያስፈልገው የሽግግር ሃሳብ ነው።
የሽግግር ሃሳብ ነው የሚያስፈልገው።እንዴት ነው አኮሞዴት/ accommodate/ የምናደርገው፧ኢትዮጵያዊያን ተምረው
አውቀው ማገዝ ሲሽሉ እንዲያገለግሉ እንዴት ነው ማድረግ ያለብን የሚለውን ሃሳብ ብናስብ ይሻለናል።ለምንድ ነው
ብትሉ ቱ ቢ ዘ ሆነስት/ to be the honest/ ፕራክቲካሊትም/practicality/ የለውም።እንኳን የሽግግር መንግሥት
ሰዎችም ሲመጡ ሲስተሙ/ the system/ በጣም ያስቸግራል።አሁንም ኢትዮጵያ ውስጥ የሽግግር መንግሥት ብናቋቁም
የሽግግር ፖሊስ፣የሽግግር መከላከያ፣የሽግግር ቴሌፎን ልንል ነው!!!” ነበር ያሉት።
እንግዲህ እኔ እንደተረዳሁት ችግሮችን እንደሚመለከተው አቅርቢያልሁ፦
ሀ/ የሽግግር መንግሥት በግሌ ብዙ አያስፈልግም ላሉት፤በቅድሚያ በግሎ ሳይሆን መንግሥትዎን ወክለው እስከመጡ
ድረስ በግሌ የምትለው ቃል ትልቅ ማጭበርበሪያ ሆና ነው የታየችኝ።ይህ የድርጅቶ አቋም እንጂ የግሎ አቋም
አይደለም!!!
ለ/ ጥያቄው የድሮ ጥያቄ ነው ላሉት በኢትዮጵያ ይህንን ሁሉ ችግር የፈጠረው አሁን የሚመሩት ድርጅቶ መሆኑን
እንዴት ዘነጉት እርሶ እየመሩት ያለው እኩ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግን እንደሆነ በግልጽ እንደነገሩን ኢ.ህ.አ.ዴግ አልደከመም
ከምንጊዜውም በላይ ጠነከረ እንጂ እንዳላሉ የሽግግር መንግስት ጥያቄ ሲነሳ የድሮ ጥያቄ ነው ያሉት ለትልቅ ትዝብት
አጋልጦታል።
ሐ/ የሽግግር መንግሥት የሚለው ሃሳብ ድሮ ተቀምጦ የማይነሱ ሰዎች ስላስቸገሯችሁ ከፍራቻ የመጣ ነው ላሉት አዎ
በግሌ እጅግ በጣም እፈራለሁ ምክንያቱም ድሮም ዛሬም በስልጣን የተቀመጠው ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ በመሆኑ ይህች የድሮ
የሚሏት ቃል ተራ ብልጣብልጥነት ናት።
መ/ ቋሚ መንግሥት የለም ላሉት አዎ የለም።ነገርግን በኢትዮጵያ ታሪክ የታዘብነው ስልጣን ከመያዛቸው በፊት ህዝባዊ
ሥልጣን ከያዙ በኋላ አምባገነናዊ መሆን የተለምደ ስለሆነ ሁሉም ህዝባዊ ሆኖ መጥቶ ዘላለማዊ እንሆናለን ሲሉ
ተገፍተው መውደቃቸውን የምንዘነጋው አይደለም።የእርሶም መንግሥት እየተንገዳገደ ባለበት ሰዓት አዲስ ስልት
በመወጠን ዘላለማዊ የመሆን ህልሙን እውን ለማድረግ እየተሯሯጠ እያየነው ነው። የእርሶ መንግሥት ቢሆንም በዝች
ምድር ላይ ዘላለማዊ የሚሆን ነገር ስሌሌለ የጊዜ ጉዳይ እንጂ መንኮታኮቱ አይቀርም።
ሠ/ ስለ እውነት እንኳን የሽግግር መንግስት የሽግግር ሰዎችም ሲመጡ ለአሰራር በጣም አስቸጋሪ ነው። ምኑ ላይ
አስቸጋሪ እንደሚሆን አልገባኝም።ለዝህ ጭንቀትዎ በፖለትካውም ይሁን በተለያዩ ዘርፎች በውጩ ዓለም ብዙ
እውቀትና ልምድ ያካበቱ ኢትዮጵያዊያን ስላሉ እነዚህ ባለሙያዎች/ሙሁራን/ መፍትሄ ሊኖራቸው/ ሊዘይዱ/
ስለሚችሉ ይህ ሊያሰጋዎት አይገባም ዋናው ነገር ቅንነት ነው። የገዛ ራሳቸውን የፖለቲካ ሳይንቲስት የሚያደርጉትን
ካማከሩ ግን መፍትሄ የከፋ እንጅ የተሻለ አይሆንም ። እርሶ እንደተናገሩት የሽግግር መንግሥት መንግስት ቀርቶ
የሽግግር ሰዎች ሲመጡ ለአሰራር በጣም አስቸጋሪ ነው ላሉት አዎ አስቸጋሪ ነው።ምክንያቱም አንድ ዓይነት ሪዮት
ዓለም ባላቸው ሰዎች መካከል የተለየ ሃሳብ ያለው ሰው መገኘት ምን ያህል ከባድ እንደሆነ በ1983 ዓ. ም ክቡር
ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ መገኘት ምን ያህል አስፈሪ እንደነበር የምናስታውሰው ሃቅ ነው።ስለዚህ እርሶም
የሚፈልጉት ድርጅቶ የሚፈልገውን በመሆኑ አሁንም በኢትዮጵያ የሰበሰቧቸው የአንድ ዘር ጥላቻ ያላቸውን ግለሰቦች
በመሆናቸው አዲስ ነገር መጠበቅ ጅልነት ይመስለኛል።
ለውጡ ውጤታማ እንዲሆን ከሽግግር መንግሥት ውጭ ምርጫ የለም።ምርጫዎ ሌላ ከሆነ ያሳምኑን
እንቀበለዎታታለን።ካልሆነ ለሀገራችን ዘለቄታዊ ሰላም የሚያመጣውን መንገድ መያዝ የግድ ነው።
ቅዱስ መጽሐፍም የሚለው ”በእናንተ ዘንድ ሁሉም በፍቅር ይሁን።” በመሆኑም ነገሮችን በማድበስበስ ማለፍ መቀነስን
እንጂ መደመርን ስለማያመጣ ለዘላቂው ሰላም “የሽግግር መንግሥት” የማያጠያይቅ ነው።

“ፈጣሪያችን ሆይ እስራኤሎችን በተደጋጋሚ ይቅር እንዳልካችው ልጆችህ ነንና ይቅር በለን!!!
አሜን አሜን አሜን

አንተነህ ጌትነት (የሶማው) ከባዕድ ሀገር ሜልበርን አውስትራሊያ
አስተያየት ካላችሁ መዚህ ኢሜል ጻፉልኝ፡muluadamche@gmail.com

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar