0
0
Read Time:40 Second
/ደ.ብ.ፋ.ኤፍ.ኤም ነሀሴ 8.2010/
የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ምክትል ኮማንድር ወርቅ አገኘሁ ሸዋ ለፋብኮ እንዳሉት አደጋው የደረሰው ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ብርሃን 29 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ኮድ 3- 33889 አማ አይሱዙ የህዝብ ማመላለሻ ከደብረ ብርሃን ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ ከነበረ ኮድ 3- 55830 አአ ሲኖ ትራክ መኪና ጋር በተፈጠረ ግጭት ነው ብለዋል፡፡
አደጋው የደረሰው በአንጎለላና ጠራ ወረዳ ጽጌረዳ መገንጠያ ከተባለው ስፋራ ሲሆን በአደጋውም ሁለቱን አሽከርካሪዎች ጨምሮ 12 ሰዎች ወዲያው ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን አራቱ በደብረ ብርሃን ሪፈራል ሆስፒታል ከደረሱ በኋላ ህይወታቸው ማለፉን የገለጹት ምክትል ኮማንደሩ አምስት ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ነው ያሉት፡፡
ከባድና ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ተጊጂዎች በደብረ ብርሃን ሪፈራል ሆስፒል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው፡፡
የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ ነው ያሉት ኮማንደሩ የሟቾችን ማንነትና ቤተሰብ የማፈላለግ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አበበ የሸዋልዑል
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating