Read Time:3 Minute, 36 Second
-
ኦገስት 18 ቀን የፊታችን ቅዳሜ በቦስተን ስለሚደረገው ታላቅ የመደመር ድጋፍ የተሰጠመግለጫ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
።። የእንንቁራሪቷ ታሪክ እንደይደርስብን ወደተግባር እንሸጋገር…
።.።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።በመላው ኢትዮጵያ የተጀመረው የለወጥ ንፋስ ፍጥነትና አቅጣጫውን እየለዋወጠ መክነፍ ቀጥሏል። መልካም የመፈቃቀር፣ የመረዳዳት፣የሰላምና የዴሞክራሲ ተምሳሌት የሆነች ኢትዮጵያንም እውን ለማድርድረግ፤ ለዘመናት የተከፈለው መስዋእትነት ፍሬን እንዲጎመራምህዝቦች ከመቸውም በላይ ከለውጥ ሐይሉናከጠቅላይ ሜኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጎንመሰለፉን እየገለፀ ነው ።በሌላ በኩል የተፈጠረውን ተስፋ ለማጨለምየራሳቸውን ጥቅም ለማሳደድ፣ ጭቆናን በመቃወምስም ተረኛ ጨቋኝ ለመሆን የተሳሳተ እቅድ ይዘውእዚህም እዚያም ዜጎች ለይ ሞት ፣ መፈናቀል በአጠቃላይ ኢ ፍትህአዊነት የሚያውጁ ግለሰቦችና ድርጅቶች እየተበራከቱ መጥተዋል። በዚህ አጋጣሚ በህዝቦች ለይ እየተደረገ ያለውን ማፈናቀልመግደል፣ በማንኛውም ምክኒያ ሚፈጠር ኢሰባዊ ድርጊትን በየትኛውም አካል፣ በይትኛውም ግለሰብይፈፀም የቦስተን የመደመር ድጋፍ ቀን አስተባባሪ ኮሚቴ በፅኑ ያወግዘዋል።ኦገስት 18 ቀን የፊታችን ቅዳሜ ከ10:00Am – 2:00pm በሚደረገውም የመደመር እርምጃን የማወጅና ተግባራዊነቱንም የማፅናት ቀን፤ መደመርን በተግባር እንድንጀምር እንደምንቀሰቅስ ሁሉ፤ ከቦስተን ህዝብ ጋር በመሆን በማንኛውም መንገድና ምክኒያት በህዝቦች ላይ የሚፈፀምን የመግደል፣ንብረት የማውደም፣ የማፈናቀል፣ሰቆቃ የመፈፀም በመብት ሰም የሚፈፀም ኢሞራላዊነትን፣ ኢሰብአዊነትን በይፋ ስናወግዝ እንደምንውል ከወዲሁ ማረጋገጥ እንፈልጋለን።“የመደመር ሰልፍ ምን ያደርጋል? እኛ አስበን ነበር።እኛ ተደምረናል፣ዲሲ ሄደን ሄደን መጥተናል። ከእኛ ውጪ ይሄን ሥራ መስራት የለባችሁም።” ላላችሁን ከዚህ አልፋችሁም”አያገባችሁም” ስትሉን የነበራችሁ ሁሉ “እኛ ካልነካንው ነገር ሁሉ እርባና የለውም” የሚለውን ጉዳይ ትታችሁ በጋራ ተመካክረን ባልተሄደበት አዲስ የመገነዛዘብ፣የመናበብና የመዋሐድ ደልድይ ለይ ተሻግረን ትውልዱን እንድናሻግር ተዘጋጅታችሁ ትመጡ ዘንድ ከልብበመነጨ ኢትዮጵያዊነት ስሜት እንለምናችኋለን።በአንድ ብሄር፣ ብሄረሰብ ወይም ህዝብ ሰም ኮሚኒቲ ስላቋቋማችሁ የብሄሩ የብሄረሰቡ፣የህዝቡ ብቸኛ ወኪል እኛ ነን በሚል ስሜት ለተያዛችሁትም መልዕክት አለን ። የተነጋገርነውንም ታውቃላችሁ። በደብዳቤ ለደረሳችሁ” የኑ እንተባበር” የፍቅርመልእክት በደዳቤ እንደ አንድ ማህበር ማሳወቅሲገባችሁ፤ቆምንለት የንትሉትን ማህበረሰብ እስከ ግለሰብ ደረጃ በመነጠል በመደመር ጅማሮው ሰነ ሰርረአቱ እንደይታደም በስወር ስትቀሰቅሱ የቆያችሁ አካላት አሁንም አረፈደምና በስፍራው ተገኝታችሁ ስሜታችሁን በመስላችሁና በሚመቻችሁ መንገድ ብትገልፁ ሊገነባ ባለው የመግባባት፣ የፍቅር፣የበጎነት የአንድነት የትውልድ መሽጋገሪያ ድልድይ መሰረት ላይ የራሳችሁን በጎ ተምሳሌት ማኖር ይቻላችኋለና “ኑ ኑ በፍቅር እንተቃቀፍ” ያን ማድረግ ካላቻላችሁ ግን ሌሎችን ጎትቶ ለማስቀረት አትሞክሩ። አሮጌው መንገድ ውጤቱ ኪሳራ ብቻ ሆኗልና እንላችኋለን።ቊምነገሩ የመደመር ሰልፉ አላማና ቀጣይውጤቱእንጂ የባለቤትነት፣ እኔ የጠራሁት፣ እኔ የአስተባበርኩ የሚለው ጬኽት አይደለም። እሳት እየነደደ ነው።ተስፋ በአገራችን አየር ለይ የመንገሱን ያህል አገሪቱን የተለያየ ስጋትም እያመሳት ነው። እዚህ ለይ የመግለጫችን ርእስ ያደረግናት እንስሳን ታሪክመቀንጨብ እንወዳለን። በአንድ ደን ውስጥ ሐይለኛሰደድ እሳት ይነሳና እንስሳቱ ሁሉ በመሰለው መንገድና ዘዴ ከእሳት ለማምለጥ መራወጥ ይይዛል። በውሀ ጒድጓዷ ዙሪያ በእሳት ቀለበትየታጠረች እንቁራሪት ግን ሞት አፈጠጠባት።ይህንየተረዱ ሁለት አሞራዎች ግን ደረሱላት።እሷም የቅርንጫፍ ስባሪ እነሱ ግራና ቀኝ ይዘው ቢበሩእሷ ቅርንጫፉን ነክስ ብትይዝ ከሞት ማምለጥእነደሚቻል ተረዳች አደረጉትም። እቴ እንቁራሪትምከእሳቱ መቅሰፍት ተርፋ ከአሞራዎች መሀል ያለክንፍ አየር መቅዘፍ ተቻላት።ክምድር ያሉ እንስሳት አድናቆት ጎረፍ። ይህን ብልሀት ማን ፈጠረው የሚልጬኸትም በረታ።እንቊራሪትዬ አላስቻላትም ” እኔ’ኮነኝ” ለማለት አፏን ስተከፍት እንጨቱን ለቀቀችውከእሳቱ ብትተርፍም የአፍ አመሏ፣ የእኔነት ህመሟተፈጥፍጦ ከመሞት አላዳናትም።የእኛም ጉዳይ እንዲያ እንዳይሆን። የሚቀድመውን እናስቀድም። በእርግጥም በተግባር እንለወጥ።በግልፅ በመነጋገር እንተራረም።የግለኝነት፣ የቡድነኝነት፣የእኔ ብቻ ልክ ነው ፈሊጥን እናቊም።ከመገናኛ ብዙሀንም የቦስተን የመደመር ተግባራዊ ድጋፍ መጀመሪያ ስነሰርአት እንዳለ መረጃው ደርሷችሁ። እንደምትገኙም ገልጣችሁ ፣ በፌስቡክ ቀጥታ እናስተላልፋለን ብላችሁ ።ቀጥተኛ ባልሆነ በማድበስበስ መንገድ ክስተቱን አይቶ እንዳላየ ለማለፍ እያመካኛችሁ ያላችሁ የሚዲያ ተቋማትለሙያችሁ ቅድሚያ በመስጠት የሚጠበቅባችሁንሀላፊነት እንድትወጡ እንጠይቃለን። በአፍየህዝብ በተግባር የጥቂቶች መሆን አለመለወጥነወና።በሌላ በኩል….ይህን የመደመርና በተግባር ከተደመረ ኀይል ፣የሚጠበቀውን ሐላፊነት ተረድተን ዝግጅቱንስናስተባብር ቀና ትብብራቸው ያልተለየን የሚዲያተቋማት መድረካችሁን በመስጠት ሞያዊ ግዴታችሁቢሆንም ላሳያችሁን ቀጥተኝነት እንዲሁ ትጋት ሳናመስግን አናልፍም።በተጨማሪ መላው የቦሰተን ነዋሪ ኢትዮጵያዊያንን ፣ የማሳቹሴት ከተማ አስተዳደር እና ፓሊስን፣ በቦስተን መሰረታቸውን ያደረጉ አብረውን የቆሙ የተለያዩ ማህበረሰባትን፣ የኤርትራ ወንድሞቻችንን ከልብ ማመስገን እንወዳለን።የኢትዮጵያ ኤንባሲን (በዋሽንግተን ዲሲ)የሚገኘውን በተመለከተበራስ አነሳሽነት የተጀመረው የመደመር ሰልፍ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ በላከው ኢሜል እንዳሳወቀ በስልክም ከሚመለከታቸው የኤንባሲው ሐላፊዎች ጋር እንደተነጋገረ፣ጉዳዩንም እንደሚያደንቁና የሚገባውን መረጃናሥራ እንደሚከውኑ ተስፋ ሲሰጡን ቆይተዋል።“አንባሳደሩ በሚገኙበትም ጒዳዩቀርቧ ውሳኔ ያገኛል” እያሉም ነበር። ቀናቶቹ ሲቃርቡ ግን የምናናግርው አካልን በስልክ ማግኘት ሰማይን ተንጠራርቶ በእጅ መዳፍ የመንካት ያክል ከባድ እንደሆነብን ሳንገልፅ ማለፍ አንወድም። ለዚህን ያህል ጊዜ በኛ በኩል ጥረት ሲደረግ ኤንባሲው ስልክ የሌለው፣ ሌሎች የመገናኛ መንገዶችንም የማያውቅ ይመስል ከኛ ብቻ መጠበቊ አሰገርሞን መቆየቱን መሸሸግም አይቻለንም።ሆኖም ያሰብነውን የሰሙ ያህልዛሬ እኛን ፈልገው አፈላልገው በቅዳሜው የቦስተን የመደመር እና በቶሎ ለውጡን የማገዝ የዲያፓራው እንቅስቃሴን እንደሚያግዙሐላፊነታቸውንም እንደሚወጡ አረጋግጠውልናል።ለዚህም ሁለት ተወካዮቻቸው ቦስተን ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።ከዚህ በኋላ ኤንባሲው የሁሉም ኢትዮጵያን የጋራ እውነተኛ መድረክ እንዲሆን አዲስ ድልድይ ይገነባል ብሎ የቦስተን የመደመር ሰልፍ አስተባባሪኮሚቴ ያምናል።እግዚአብሔር ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ !በራስ አነሳሸነት የተጀመረውየመደመር ሰልፍ።አስተባባሪ ኮሚቴ (ቦስተን)ለበለጠ መረጃ* አቶ ብሩክ ገብረአምላክ(ሰብሳቢ)617 312 06 91*አቶ አማረ ለማ617 513 4911================================== *አቶ ሰሎሞን ወልደመድህን857 230 9717 ( የሚዲያ ክፍል)===================================== * አቶ ፍቃዱ ረጋሳ6174128375
Average Rating