በህወሀት አስተዳደር እስርቤት ገብቶ በድብደባ ብዛት እግሩ አልንቀሳቀስ ብሎት ህክምና በሄደበት ሰአት በዶክተሮች ስህተት ተብሎ መቆረጥ የሚገባው እግሩን በመተው ጤነኛውን ከቆረጡበት በኃላ እንደገና በሽተኛውን ደግመው የቆረጡበት የቀድሞው እስረኛ እና የአሁኑ የአካል ጉዳተኛ አቶ ከፍያለው በደረሰበት የአካል እና የሞራል ጉዳት ማካካሻ ትሆን ዘንድ በማለት የሰበታ ከንቲባ ስጦታ ማበርከታቸው ተገለፀ።
በህይወቱ ይሄ ይደርስብኛል ብሎ አስቦ የማያውቀው እና በአሁን ሰአት ሙሉ በሙሉ በዊልቸር የሚንቀሳቀሰው የቀድሞ ታራሚው ወጣት ከአከላዊም ሆነ ከሞራላዊ ጉዳት መቼም የሚያገግም እንዳለሆነ ይታወቃል ።ይህ ብቻ አይበቃም በማለት የከተማው ከንቲባ ካላቸው መዋእለ ነዋይ ቀንሰው የሰጡት ፣ከተማዋ ምንም በቂ ገቢ የላትም ሆኖም ለደረሰበት ጉዳት ሞራልን መተካት ባንችልም ፣አካልን መቀጠል ባንችልም መደገፍ ግን ግዴታችን ነው በማለት ስጦታውን አቶ ለገሰ ሰጥተዋል
በእስር ቤት ሁለት እግሮቹ ለተቆረጡበት ወጣት ከፍያለው ተፈራ የሰበታ ከተማ ምክር ቤት 150 ሺህ ብርና መኖርያ ቤት የከተማው ባለሃብቶች ደግሞ 312 ሺህ ብር በጥቅሉ 462 ሺህ ብር ተበርክቶለታል።
ስጦታውን ያስረከቡት ከንቲባ ለገሰ ነገዎ እገዛው ቀጣይነት እንደሚኖረው ገልጸዋል።
ህወሃት ለአለፉት ሃያ ሰባት አመታት በወጣት ኢትዮጵያኖች ላይ ያደረገው ግፍ የትየለሌ ከመሆኑም የተነሳ ፣ከስልጣን የወረደ ጊዜ ከተወላጅ ህዝቡ ጋር የመተላለቅ ዘመን ይሆናል እያሉ በፍርሀት ዘመን የተጠመዱ ዜጎች እንደነበሩ ቢታወስም በአዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር የመደመር እና የይቅርታ ዘመን ጥያቄ መሰረት እኛ ዝቅ ብለን እንጠይቃለን ባሉት መሰረት ህዝቡ ይቅርታውን ተቀብሎ ህይወቱን ለመቀጠል ቢሞክርም የህወሀት ፅንፈኛ አካላት ግን ህዝብን ከመንግስት ጋር እንዲሁም ዘርን ከዘር ለማጋጨት በመቀሌ መምከር መያዛቸው የማያዋጣ መሆኑን በማስጠንቀቂያጭምር ተነግሯቸዋል።
Average Rating