www.maledatimes.com ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓልን በማስመልከት የመልካም ምኞት መግለጫ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓልን በማስመልከት የመልካም ምኞት መግለጫ

By   /   August 21, 2018  /   Comments Off on ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓልን በማስመልከት የመልካም ምኞት መግለጫ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 32 Second

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓልን በማስመልከት የመልካም ምኞት መግለጫ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓልን በማስመልከት የመልካም ምኞት መግለጫ

በሀገር ቤት እና ከሀገር ውጪ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ወገኖቼ፤
በመላው ዓለም በሚገኙ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት በየዓመቱ በክብር ለሚነሳው እና ዘንድሮም ለ1439ኛ ዓመተ-ሂጅራ ለሚከበረው የኢድአል አድሃ አረፋ በአል እንኳን በሠላም አደረሳችሁ- አደረሰን!

ኢድ ሙባረክ !!!

በፆም፣ በፀሎትና ክፉ ምግባርን በሚኮንን ሀይማኖታዊ ሥርዓት የሚከናወነው የአረፋና የሀጅ ሥርዓት ከአምስቱ የእስልምና መሠረታዊ ምሶሶዎች መካከል አንዱ ሲሆን በእስልምና ሃይማኖት ትልቅ ሥፍራ የሚሰጠው ታለቅ በዓል ነው፡፡ በእምነቱ አስተምህሮት በግልጽ እንደተቀመጠው በዙል ሂጃህ ወር ዘጠነኛ ቀን የሚከናወነው የአረፋ ሥርዓት የእስልምና ሃይማኖት የመጨረሻ ከፍታውን ያገኘበት እና የቁርአን የመጨረሻ አንቀፆች ለነቢዩ መሀመድ (ሠዓወ) የወረደበት እለት ከመሆኑም በተጨማሪ በአንድ በኩል አደምና ሀዋ ከጀነት ከወጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በምድር የተገናኙበትና አወቅኩሽ አወቅሽኝ የተባባሉበትን ድንቅ ተዓምራት ማስታወሻም ጭምር ነው፡፡ ነቢዩላ ኢብራሂም በፈጣሪያቸው ትዕዛዝ አንድ ልጃቸውን እስማኤልን ለመስዋዕት አቅርበው ለፈጣሪያቸው ትዕዛዝ ከመገዛታቸው የተነሳ በልጃቸው ምትክ የበግ መስዋዕትነት የተተካላቸው መሆኑን የምናስታውስበት ዕለት በመሆኑ ለሁላችንም የታዛዥነትን ከፍታ እና የእምነትን ልእልና የሚያጸድል ግሩም በአል ነው፡፡

ውድ የሀገራችን የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ወገኖቼ !!!

የዘንድሮውን የአረፋና ኢድ አልአድሃ በዓል ልዩ የሚያደርገው ሀገራችን በአዲስ የለውጥ እርምጃ መጓዝ በጀመረችበት ማግስት የሚከበር መሆኑ ብቻ ሳይሆን ለዓመታት ተከፋፍሎ የቆየው የሙስሊም ማኀበረሰብ አንድነቱን ለማጠናከር በጋራ መንቀሳቀስ በጀመረበት አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ላይ ሆነን የምናከብረው መሆኑ በዓሉን ድርብ ድርብርብ የደስታ በአል ያደርገዋል፡፡ የእስልምና እምነት ተከታይ በሆነው ኀብረተሰባችን መካከል የሚፈጠር አንድነት ለሙስሊሙ ወገናችን ብቻ ሳይሆን ለሀገራችንም አንድነትና ጥንካሬ ምንጭ መሆኑን መንግስት አበክሮ ይገነዘባል፡፡ አረፋ በዓልም የመስጠት፣ የደግነትና የቸርነት በዓል በመሆኑ የተቸገሩና አንዳች ጥሪት የሌላቸው ወገኖቻችንን በመርዳት በመልካምና ደግ ሥራ በዓሉን ከተቀረው ወገኖቻችን ጋር በጋራ እንድናከብር ጥሪዬን ላቀርብ እወዳለሁ፡፡

ውድ የሀገራችን ሙስሊሞች

በሀገራችን የዘመናት የአብሮነት ታሪክ ውስጥ መቻቻል፣ መተዛዘን እና መረዳዳት ያለውን ፋይዳ በውል የሚረዳው የሀገራችን ሙስሊም ማኀበረሰብ በሠው ልጅ የዘመናት ጥረትና ድካም የዘረጋናቸውን መልካም እሴቶች ኃላፊነት የማይሰማቸው አካላት በአንድ ጀንበር እንዲንዷቸው ብሎም ወደስርዓት አልበኝነት እንዲቀይሯቸው ፈጽሞ እንደማይፈቅድ እምነቴ ጽኑ ነው፡፡ በምንም መልኩ ቢሆን መንጋዎች እንዲሰለጥኑብን የማንመች ህዝቦች መሆናችንን ደግመን ደጋግመን ማሳየት በቻልንበት ውብ ታሪካችን ውስጥ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ሚና አጅጉን የላቀ እንደነበር እሙን ነው፡፡ አሁንም መላው ሙስሊም ወገኖቼ ይህንኑ ሀገርን በስርአት የማቆም ደማቅ ታሪኩን በአብሮነቱ እንደሚያስቀጥል ምንም ጥርጥር የለውም፡፡

መልካምን መውደድ፣ ክፉ ተግባርን ማውገዝ የሁሉም ሃይማኖቶች እሳቤና ዕሴት ነው፡፡ ክፉ ተግባር በአንድ አካባቢ ወይም አጋጣሚ ብቻ በመከሰቱ በፍፁም ዝም ያለማለት ባህላችንን ሙስሊሙ ማህበረሰብ በጠንካራ መሰረት ላይ የማነጽ ታሪኩን አጠናክሮ እንዲቀጥልም አደራ ለማለት እፈልጋለሁ፡፡ እንደ አንድ ሕግ አክባሪ ዜጋ መልካም ተግባርን የመውደድ እና ክፋትን የማውገዝ ኃላፊነት እንዳለብን ባለመዘንጋት የሀገራችንን ሁለንተናዊ ለውጥ በመደመር ለማስቀጠል ሙስሊሙ የሀገሬ ህዝብ የበኩሉን ሁሉ እንዲያደርግም ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡ የእኛ ዝምታ ሌሎች ሕገ-ወጦችን በህልውናችን ላይ የሚያዙ የጎበዝ አለቃ እንዳያደርጋቸው መንቃት የሚገባን ጊዜ ላይ መሆናችንንም በአክብሮት ላስታውሰችሁ አወዳለሁ፡፡ ምሁራን፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የእምነት አባቶች የማህበረሰባችሁ የእውቀት ቀንድ ናችሁና ሥርዓት አልበኝነት እንዳይሰለጥን ማኀበረሰባችሁን በሞራልና በሥነምግባር ተግታችሁ እንድታንጹ አደራ እያልኳችሁ የተከበራችሁ የሀገራችን ሙስሊሞች በዚህ ታላቅ እና በመስጠት ጸጋ የተቃኘ ታላቅ በዓል ወቅት ለእናንተ ለወገኖቼ የመልካም ምኞት መግለጫ ለማስተላላፍ በመቻሌ የተሰማኝን ከፍ ያለ ክብርና ልባዊ ደስታ ልገልጽላችሁ እወዳለሁ፡፡ በመጨረሻም በዓሉ አብሮነታችን የሚፈካ የሚያብብበት፣ ሰላምና ሀገራዊ አንድነታችን ስር የሚሰድበት የበረከት በዓል እንዲሆንላችሁ ከልብ እመኛለሁ፡፡

ኢድ ሙባረክ መልካም በዓል

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar