www.maledatimes.com በግማሽ አቅሙ ሥራ የጀመረው የረጲ የደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ ውዝግብ ፈጥሯል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

በግማሽ አቅሙ ሥራ የጀመረው የረጲ የደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ ውዝግብ ፈጥሯል

By   /   August 23, 2018  /   Comments Off on በግማሽ አቅሙ ሥራ የጀመረው የረጲ የደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ ውዝግብ ፈጥሯል

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 14 Second
በግማሽ አቅሙ ሥራ የጀመረው የረጲ የደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ ውዝግብ ፈጥሯል
የረጲ ደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ ሲመረቅ ከግራ ወደ ቀኝ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አዜብ አስናቀ (ኢንጂነር)፣ የውኃ ኤሌክትሪክና መስኖ ሚኒስትር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) እና ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ይታያሉ

በ2.6 ቢሊዮን ብር ወጪ የተገነባውና ማለቅ ከነበረበት በሁለት ዓመት ዘግይቶ ለአገልግሎት የበቃው የረጲ ደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ በግማሽ አቅሙ ተመረቀ፡፡ ፕሮጀክቱ ከደረቅ ቆሻሻ 25 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው ቢገለጽም፣ ከአራት ዓመታት በፊት የኮንትራት ስምምነት ሲፈረም 50 ሜጋ ዋት ለማመንጨት እንደነበር ይታወሳል፡፡ ሆኖም ግንባታውን ያከናወነው ካምብሪጅ ኩባንያ በውሉ መሠረት 50 ሜጋ ዋት ለማመንጨት የሚያስችል ሥራ ባለማከናወኑ፣ ከመንግሥት ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብቷል፡፡

ፕሮጀክቱ በ25 ሜጋ ዋት ሥራ እንዲጀምር ቢደረግም፣ በውሉ መሠረት 50 ሜጋ ዋት ማመንጨት የሚያችል ሥራ አላከናወነም የተባለውን ኩባንያ በሕግ እንደሚጠየቅ ተገልጿል፡፡

በምረቃ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አዜብ አስናቀ (ኢንጂነር)፣ ‹‹ከውላችን ውጪ የተከናወነ ስለሆነ ጉዳዩን ወደ ሕግ እንወስዳለን፤›› ብለዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ማለቅ ከነበረበት በሁለት ዓመት የዘገየው በዲዛይን ለውጥ መሆኑን፣ የፕሮጀክቱ የሥራ ተቋራጭ ካምብሪጅ ኩባንያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ዓለማየሁ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ ድርጅቱ ፕሮጀክቱን ጨርሶ ለማስረከብ ከአራት ዓመት በላይ ፈጅቶበታል፡፡

ፕሮጀክቱ በዓመት 185 ጊጋ ዋት አወር ኃይል ያመነጫል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ በቀን ከሚያመነጨው ሦስት ሺሕ ሜትሪክ ቶን ደረቅ ቆሻሻ ውስጥ ግማሽ ያህሉን እየተጠቀመ እንደሚገኝ፣ በነበረው የሁለት ወራት የሙከራ ጊዜ ከ28 ሺሕ ሜትሪክ ቶን በላይ ቆሻሻ መጠቀሙ ተገልጿል፡፡

እሑድ ነሐሴ 13 ቀን 2010 ዓ.ም. በይፋ የተመረቀው ይህ ፕሮጀክት፣ በአዲስ አበባ ያለውን የኃይል መቆራረጥ ችግር ለማቃለል ያግዛል ተብሏል፡፡ ፕሮጀክቱ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል፡፡

FacebookTwitterLinkedInShare

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar