www.maledatimes.com ብአዴን ለሱዳን የተሰጠው መሬት የሚመለከተው አካል ሳይወያይበት እንደተሰጠ አሳወቀ። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ብአዴን ለሱዳን የተሰጠው መሬት የሚመለከተው አካል ሳይወያይበት እንደተሰጠ አሳወቀ።

By   /   August 26, 2018  /   Comments Off on ብአዴን ለሱዳን የተሰጠው መሬት የሚመለከተው አካል ሳይወያይበት እንደተሰጠ አሳወቀ።

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 8 Second

ብአዴን ለሱዳን የተሰጠው መሬት የሚመለከተው አካል ሳይወያይበት እንደተሰጠ ገልፆአል። የብአዴን አመራሮች ያለ አግባብ ሲወቀሱበት እንደኖሩም ገልፆአል!

የዛሬው መግለጫ ይበል የሚያሰኝ ነው! ነገር ግን:_

1) ክልሉን አስተዳድራለሁ እያለ መሬቱ ከገበሬውና ከባለሀብቱ ተቀምቶ ለሱዳን ሲሰጥ፣ ባለፉት አመታት በርካታ ገበሬዎች ሲገደሉ፣ ሲቆስሉ፣ ሀብት ንብረታቸው ሲወድም አልሰማሁም አላየሁም ሊለን አይችልም። በጥቃቅን ነገር እነ መለስ ፊት “ሂስና ግለ ሂስ” እያለ ሲቀባጥር የኖረ ድርጅት ዛሬ የራሱን ጥፋትም ማመን አለበት። ፈርሞ አለመስጠት ሌላ አስተዳድረዋለሁ የሚለው ክልል መሬትን እነ አባይ ፀሀየ እየፈረሙ ወደሱዳን ሲከልሉ ብአዴን የማንን ጎፈሬ ሲያበጥር ነበር? ጊዜው ጥሩ ነው ሀቁን ለሕዝብ ተናግሮ ጥፋትን ከላዩ ማውረድ ይበጃል።

2) ብአዴን እንዳላየ እያረፈ እነ አባይ ፀሀየ ፈርመው ያስረከቡት መሬት ምክንያት በርካታ ገበሬዎች ህይወታቸው አልፏል። ብዙዎች ቆስለዋል። ንብረታቸው ወድሟል። የእነዚህ ድንበር ጠባቂ ገበሬዎች ጉዳይ ዝም ተብሎ መታለፍ የለበትም

3) እንደ መሬቱ ሁሉ ትህነግ /ህወሓት በቅማንትና በአገው ጉዳይ ላይ ገብቶ እየፈተፈተ ይገኛል። ብአዴን ይህንም በግልፅ ለሕዝብ ማሳወቅ አለበት። የራሱን ድክመትም እንዲሁ።

4) ብአዴን ባለፉት 2 አስርት አመታት በአማራ ክልል ለተፈፀመው ወንጀል ሁሉ የራሱን ድርሻ በግልፅ በመናገር ከሕዝብ ጋር መታረቅ አለበት። የትህነግና ሌሎቹንም እጅ እንዲሰበስቡ ግልፅ ማድረጉ መልካም ሆኖ የራሱን አድበስብሼ አልፋለሁ ቢል ነገም ከሕዝብ ጋር ሌላ ጠብ መግጠሙ ነው።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዜና ብአዴን ትህነግ/ህወሓት ለሱዳን አሳልፎ በተሰጠው መሬት ላይ መግለጫውን በይፋ  ሰጥቷል። እነ አባይ ፀሀዬ ፈርመው የሰጡትን መሬት የሚመለከተው አካል ያልተሳተፈበት ነው ብሎታል!

………………

“በመተማ ወረዳ ልዩ ስሙ ደለሎ በተባለው አካባቢ ታሪካዊ ዳራውንና ነባር የይዞታ መብታችንን ያላስጠበቀ፣ የሚመለከታቸውን አካላት ያላሳተፈና የጋራ አቋምም ያልተያዘበት ውሳኔ ተሰጥቶ እንደነበር አውቀናል፡፡ ይህ ውሳኔ ብአዴንና አመራሮቹ ለረጅም ጊዜ በህዝብ ዘንድ ባልተገባ መልኩ ሲታሙና ሲጠረጠሩ እንዲቆዩ አድርጓል”

………………………………………

” በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል ያለው የድነበር ማካለል ጉዳይ በዘላቂነት እስኪፈታ ድረስ የሁለቱም ወገን አርሶ አደሮች የያዙትን የእርሻና የደን መሬት እንደያዙ እየተጠቀሙ እንዲቆዩ በሁለቱ ሃገራት መንግስታት መካከል ስምምነት ተፈርሞ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጅ በተለይ በመተማ ወረዳ ልዩ ስሙ ደለሎ በተባለው አካባቢ ታሪካዊ ዳራውንና ነባር የይዞታ መብታችንን ያላስጠበቀ፣ የሚመለከታቸውን አካላት ያላሳተፈና የጋራ አቋምም ያልተያዘበት ውሳኔ ተሰጥቶ እንደነበር አውቀናል፡፡ ይህ ውሳኔ ብአዴንና አመራሮቹ ለረጅም ጊዜ በህዝብ ዘንድ ባልተገባ መልኩ ሲታሙና ሲጠረጠሩ እንዲቆዩ አድርጓል፡፡

በመሆኑም ውሳኔው በፌደራል መንግስት በኩል አስቸኳይ ማስተካከያ እንዲደረግበት እንጠይቃለን፡፡ ለጋራ የጸጥታ ማሰከበር ስራ ይጠቅማል የሚለውን ስምምነት ምክንያት በማድረግ በቋራ ወረዳ ልዩ ስሙ ነፍስ ገበያ በተባለው አካባቢ ለጊዜው ሰፍሮ የነበረው የሱዳን ወታደርም ይዞታ እያሰፋፋና ቋሚ ካምፕ እየገነባ ከያዘው ጊዚያዊ ይዞታ ሳይለቅ መቆየቱ ተገቢ እንዳልሆነ መዕከላዊ ኮሚቴው ገምግሟል፡፡

የካመፑም መኖር የድንበሩን ጉዳይ የበለጠ እያወሳሰበውና የክልሉ አርሶ አደሮችም የእርሻ ስራቸውን በሰላም እንዳያከናውኑ እንቅፋት እየሆነ ይገኛል፡፡ ከዚህ አኳያ የሱዳን ወታደር እስካሁን ድረስ ከያዘው ይዞታ ለቆ አለመውጣቱ ተገቢ ባለመሆኑ በፍጥነት ከይዞታችን ለቆ እንዲወጣና የፌደራል መንግሥትም ይህንኑ እንዲያሰፈጽምልን እንጠይቃለን፡፡ ብአዴን በክልላችን የሚገኘው ይህ የኢትዮ ሱዳን የድነበር ጥያቄ የነዋሪወችንና የአርሶ አደሮቻችንን ይዞታ መሰረት አድርጎ፣ ታሪካዊ ዳራውን ሳይለቅና የሃገርን ሉዓላዊ ጥቅም ባስከበረ መንገድ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድበት ጥረት ማድረግ እንደሚገባ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

በጌታቸው ሽፈራው

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on August 26, 2018
  • By:
  • Last Modified: August 26, 2018 @ 10:09 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar