ባሳለፍነው ሳምንት ሰኞ ጀምረን እስከ ዛሬ ድረስ የማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ምንም አይነት ወቅታዊ ዜናዎችን ለመስራት አልቻልንም ነበር ምክንያቱም የማለዳ ታይምስ የመረጃ ማእከል የዜናዎቻችን አማካሪ የሆነችው (በዶክትሬት ድግሪ እጮ በመሆን በሆላንድ ደልፊን የእርሻ ምርምርን )ለማጠናቀቅ አንድ አመት የቀራት ወጣት ራሄል እሸቱ ሃይሌ እለፈተ ህይወት የተነሳ መረጃ ማእከላችን ምንም አይነት ዜናዎችን ሊያስተላልፍ ባለመቻሉ ፣ይቅርታ እየጠየቅን በአማካሪያችን እጩ ዶክተር ራሄል እሸቱ ሞት የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እንገልጻለን ፣ለቤተሰቦቿ መጽናናትንም እንመኛለን በደረሰብን ድንገተኛ አደጋ መሰረት በማናቸውም መልኩ ምንም አይነት ስራ ተቋቁመን መስራት አልቻልንም ነበር እና በድጋሚ ሃዘናችን ጥልቅ በመሆኑ ለነበረው የወቅታዊ ዜና መዘግየት ይቅርታችንን ከወዲሁ እንጠይቃለን !!
በዚሁ አጋጣሚ ባልደረባችን እና አማካሪያችን ራሄል እሸቱ በጡት ካንሰር በአጭር ጊዜ ህመም ምክንያት ከዚህ አለም በሞት ስለተለየች የማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል የራሄልን ፋውንዴሽን በማለት በኢትዮጵያ ለሚገኙት የካንሰር በሽተኞች መርጃ የሚሆን ማእከል ለማቋቋም ይፈልጋል ስለዚህ በአካል ፣በእውቀት ፣በገንዘብ እና በሌሎች ቁሳቁሶች መርዳት የምትፈልጉ ግለሰቦች በአድራሻችን ሊያገኙን ይችላሉ እና የሴት እህቶቻችንን ሞት ለመቀነስ በጋራ እንስራ !!
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating