www.maledatimes.com ጅምሩ ጥሩ ነው – ግን እነ በረከትና ካሣ ብቻ አይደሉም! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ጅምሩ ጥሩ ነው – ግን እነ በረከትና ካሣ ብቻ አይደሉም!

By   /   September 3, 2018  /   Comments Off on ጅምሩ ጥሩ ነው – ግን እነ በረከትና ካሣ ብቻ አይደሉም!

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 20 Second

ጅምሩ ጥሩ ነው – ግን እነ በረከትና ካሣ ብቻ አይደሉም!

ነፃነት ዘለቀ (netsanetz28@gmail.com)

ብዙ ከዘገዬ በኋላም ቢሆን ብአዴን ነፍስ እያወቀ መምጣቱን በግልጥ እያየን ነው፡፡ ከዘላለም ባርነት የአንድ ቀን ነፃነት እንደሚሻልም እየተገነዘበ እንደሆነ በአንዳንድ ያልተለመዱ መልካም ተግባራቱ እየገለጸ ነው፡፡ ለምሣሌ በድኩማኖቹ ወያኔዎች የማንአለብኝነት ግልጽ ጣልቃ ገብነት ምክንያት በመካከሉ ተሰግስገው በነበሩ የሕወሓት ተወካዮች በነበረከት ስምዖንና ካሣ ታደሰ (ጥንቅሹ) የፊጥኝ ታስሮ ሲሰቃይ መኖሩን ተገንዝቦ እንደተባለው እስከፊታችን መስከረም 2011 ዓ.ም ድረስ እነሱን የማገድ እርምጃ መውሰዱ እየተዘገበ ነው፡፡ እነሱም አግዱን በተመለከተ “የአማራ ሕዝብ አሁን ለደረሰበት አጠቃላይ ዕድገት ከእኛ ውጪ ማንም ቅንጣት አስተዋፅዖ አላደረገም፡፡ እኛ ያመጣንለትን ድል ሊያስነጥቁትና ወደ ደም መፋሰስና ወደ ኋላ ቀር አገዛዝ ሊመልሱት እነ ገዱና ንጉሡ ጥላሁን እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ የአማራ ሕዝብ እኛን ስለሚወድ በየሄድንበት ቦታ ሁሉ በፍቅር እያስተናገደን ባለበት ሁኔታ ስብሰባ እንዳንገባ ሕዝቡ በተለይም ወጣቱ ሳይሆን አድሃሪው  የብኣዴን አመራር ከለከለን፡፡…” የሚል ይዘት ያለው የማስጠንቀቂያ አይሉት የተማጥኖ ወይም የማስፈራሪያ ደብዳቤ ለቀዋል፡፡ “ሞኝ እንዴት ይረታል?” ቢሉት “እምቢ ብሎ” ይሉት አስተኔ ነው የነዚህ ጉዶች ነገር፡፡ ብአዴን እነሱን ካባረረ ዓለም እንደምታልፍ ያህል እያስፈራሩ ይገኛሉ፡፡ እርግጥ ነው “በጌታዋ የተማመነች በግ ላቷን ውጭ ታሳድራለች” እንደሚባለው እነሱም እንደዱሮው መስሏቸው የወያኔን ጡንቻ ተማምነው ሊሆን ይችላል፡፡ ግን ግን ዱሮ ሌላ አሁን ሌላ፤ “ያ ሌላ ፤ ይሄ ሌላ” ብሏል ዘፋኙ፡፡ እነበረከት ተሸወዱ፡፡ በሁልጊዜ አበባየ የሞኝ ዘፈን መቃኘት ለዚህ ዓይነቱ የቀቢፀ ተስፋ አድራጎት ያጋልጣል፡፡

የብአዴን መለወጥና ወደ ሕዝብ ጉያ መግባት እውነት ከሆነ እሰዬው ነው፡፡ ብአዴን ውስጡን ካጸዳና እውነተኛ የአማራና የኢትዮጵያ ተጠሪነቱን ካረጋገጠ የተማሩና በየሙያው ሰፊ ልምድ ያላቸው ብዙ የዚያ ክልል ተወላጆች ከጎኑ እንደሚቆሙ ግልጽ ነው፡፡ ችግሩ የእስካሁኑ ብኣዴን እንደጌቶቹ ወያኔዎች በሙስና የተጨመላለቀና ለወያኔ የሥልጣንና የሀብት ፍርፋሪ ያደረ፣ በዚያ ላይ ለኢትዮጵያና ለአማራው ማሰብ ይቅርና የራሱ አባላትም ከዕውቀትና ከትምህርት በመሸሽ በማይምነትና በአድርባይነት ካባዎች ተጀቡነው ለከርሳቸው ብቻ የሚኖሩ በመሆናቸው ድርጅቱ በእስካሁኑ አካሄዱ የተማሩ ወገኖች ሊጠጉት የማይፈልጉት ማፈሪያ የነበረ መሆኑ ነው፡፡ እንጂ ብአዴን ያለእኩያው የወረዳ ወርዶ ለነዚህ ከአፍ እስካፍንጫቸው እንኳን ማሰብ ለማይችሉ ጥቂት ድኩማን ማደር አልነበረበትም፡፡ እዚህ ላይ ይህ የወያኔ ጥፍጥፍ ንቅናቄ ለአማራ ሕዝብ በሀፍት መሸማቀቂያ እንደነበረ መጠቆም እወዳለሁ፡፡ አሁን ግን “አፉ በሉኝ” ብሎ ጠባዩን ከለወጠና ወደ ሕዝብ ከተጠጋ የማይቀበለው አይኖርም፡፡ ሁላችንም ገብተን የየአቅማችንን አንዳች አወንታዊ ነገር ለማበርከትም አንጓደድም፡፡

እንደ እውነቱ ለውጥ ጥሩ ነው፡፡ መቼም ይለወጥ አንድ ሰው ወይም ድርጅት ሲለወጥ እንደማየት የሚያስደስት የለም፡፡ ለምን ተለወጥክ ብሎም ቅር መሰኘት አግባብ አይደለም፡፡ በምንም ዓይነት ውስጣዊና ውጫዊ ሁኔታ ተገፍቶም ይሁን ወይም ኅሊናው አምኖበትና አስገድዶት አንድ ሰው ከመጥፎነት ወደ መልካምነት ከተለወጠ ያስመሰግነዋል እንጂ በነበረበት ለምን አልረገጠም ተብሎ ሊወቀስ አይገባም፡፡ ሊጤን የሚገባው ዋና ነገር “ለውጡ እውነት ነው ወይ?” የሚለው ነው፡፡ ለውጡ ለማስመሰል የተደረገ እንዳይሆን ማረጋገጥ ይገባል፡፡ ለይምሰል ከሆነ እስስትነት ነው – አንድን አደገኛ ሁኔታ ሸውዶ ለማለፍ የታቀደ፡፡  ከዚህ አንጻር “ብአዴን እያደረገ ያለው የለውጥ ሂደት የሚያኮራና የቀደመ የቆሸሸ ምንነቱን የሚያጥብበት ነው” ብለን አፋችንን ሞልተን እንድንመሰክርለት ብዙ መሥራት ይጠበቅበታል፡፡  በዚያ ላይ የምናውቅለትን የሙስናና የመልካም አስተዳደር ዕጦት በአፋጣኝና ጎን ለጎን እንዲያስተካክል መጣር አለበት፡፡ ብዙ የአማራ አካባቢ ነጋዴዎችና ንጹሓን ዜጎች የሚያለቅሱበት የአሠራር ድክመትና የሙስና ጥልፍልፍ እንዳለ እናውቃለን – ከአምልኮት ሥፍራዎች ውጪ የምንጮህበት ቦታ ጠፍቶን እንጂ፡፡ ለውጥ ሲባል እንግዲህ ይሄን ሁሉ ታሳቢ ያደርጋል፡፡ ዜጎችን በቅንነት ማገልገል፣ ለሥራ ክፍሎችና ለኃላፊነት ቦታዎች ብቁና ሙያዊ ችሎታ ያላቸውን ሰዎች መመደብ፣ ሥራዎች በፍትህና በታለመላቸው የጊዜና የበጀት ሥፍር መሠረት በትክክል መካሄዳቸውን መከታተል፣ መሠረታዊ ታህታይ መዋቅሮችን (መንገድ፣ ህክምና፣ ትምህርት ቤት፣ ፀጥታ፣ ፍትህ፣…) ማሟላታቸውን ማረጋገጥ፣ የዜጎችን ዕንባ ማበስ፣ ፍትህ እንዳይዛባ መቆጣጠር ወዘተ. ይጠበቅበታል፡፡

ብአዴን ስሙንና መለያውን ሁሉ ሊለውጥ እንደሆነም ሰምተናል፡፡ ጥሩ ነው፡፡

ከፍ ሲል እንደገለጽኩት ብአዴን እነበረከትን ከድርጅቱ አግዷል ተብሏል፡፡ ይህም እጅግ መልካም ዜና ነው፡፡ ይሁንና መታገድ ያለባቸው እነዚህ ብቻ አይደሉም፡፡ ድርጅቱን የወያኔ ተላላኪና ቋሚ አሽከር ያደረጉ፣ የአማራውን ሰፊ ሕዝብ ለጥቂቶች መሠሪ አገዛዝ ምቹ እንዲሆን ያደረጉ፣ የአማራን ሀብትና መሬት ለባዕዳን እንዲሸጥ ያደረጉ፣ አማራው በተለይ ላለፉት 27 ዓመታት በትግራይ ነፃ አውጭ ድርጅት በሕወሓት ሥር በባርነት እንዲማቅቅ ያደረጉ እነበረከትና ጥንቅሹ ብቻ ሣይሆኑ ሌሎችም ብዙ አሉና እነሱም በአስቸኳይ ይታገዱ፤ እንዲያውም ለፍርድ ይቅረቡ፡፡ አንድን ሕዝብ ለመከራና ለስደት፣ ለሞትና ለባርነት በማጋለጣቸው “ጥቁር ውሻ ይውለዱ” ተብለው በሕዝብ መረገማቸው የማይቀር መሆኑና ዘር የማይወጣላቸው መሆኑ እንዳለ ሆኖ በሠሩት ሥራ በሕይወት እያሉ ሊጠየቁ ይገባል፡፡ የአማራን ነጭ ጤፍ እንጀራ በልተው፣ የአማራን ውኃ ጠጥተው፣ በአማራ ምድር አድገውና ለቁም ነገር ደርሰው “ዘር ከልጓም ይስባል” እንዲሉ ሆነና ለመጡበት ዘውግ በማዳላት ይህን የዋህና ደግ ሕዝብ ክደዋልና ፈጣሪም በበኩሉ የእጃቸውን እንደሚሰጣቸው የታመነ ነው፡፡ አሁንና ወደፊትም ዘር አይውጣላቸው፡፡ ነፍሳቸውም በአየር ለዘላለም ትቅበዝበዝ፤ ሲሞቱም ዐፅማቸው ዕረፍት ይጣ፡፡ ይህን የዋህ ሕዝብ በቁም እንደቀበሩ እነሱም በታሪክ ለዘላለሙ እየሞቱ ይኑሩ፡፡

ያ አለምህ መኮንን የተባለ ጦልጧላ ውሻም ዝም መባል የለበትም፡፡ ቢያንስ ከድርጅቱ መገለል አለበት፡፡ ከመገለል ባለፈ ግን ጉዳት እንዳይደርስበት የአማራ ታጋዮች ሊጠብቁት ይገባል –  ከመሳደቡ ውጪ ሌላ እንደነ በረከት ያለ ዕኩይ የመላላክ ሥራ ከሌለበት ብዙም ባይጨከንበት ደግ ነው፤ ይህ ጅል ሰው አእምሮውን ተነጥቆ በመሆኑ ያን ክፉ ቃል የተናገረው እንደፍጥርጥሩ እየተጃጃለ ይኑርበት፡፡ ሌሎቹ ግን እባብ ናቸውና የእባብን ዋጋ ያግኙ፡፡ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር አማራ እንዲያልቅ መርዝ በመቀመም የተባበሩ፣ አማራ ከነነፍሱ በገደል ሲወረወረ፣ አማራ ተዘቅዝቆ ሲገረፍ፣ አማራ…. ተቆጥሮ የማይዘለቅ ግፍና በደል ሲደርስበት አንድም አለሁህ ባይ እንዳይኖረው ያደረጉ ሸለምጥማጦች በመሆናቸው እነበረከት የሸንጎ ፍርድ ይገባቸዋል፡፡ እነዚህ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች በዝምታ ከታለፉ ሌሎች ቀበሮዎችንና ተኩላዎችን እንደመፈልፈልና እንደማበረታታትም ይቆጠራል፡፡ ብአዴን በነበረከት ብቻ ሳይወሰን በድርጅቱ መዋቅር ከታች እስከላይ የተሰገሰጉ ወያኔዎችንና ለተንኮል ሥራቸው ስኬት ሲሉ ስምና ብሔራቸውን ሳይቀር እየለወጡ በአማራው ውስጥ ገብተው የሚሰልሉ ሕወሓቶችን መመንጠር ይኖርበታል፡፡ ሞኝነት ይብቃ፡፡ መታረድ ይብቃ፡፡ መኮላሽት ይብቃ፡፡ መሰደድ ይብቃ፡፡ መታሰር ይብቃ፡፡ የመከራው ዘመን ተጠቅልሎ ወደ ታሪክ ግምጃ ቤት ይሰተር፡፡

በተረፈ ከአንድ ድረገፅ ያገኘሁትን ተጋሩ የብአዴን አባላት ቀጥዬ ላስቀምጥና ልሰናበት፡፡

  1. መኮነን ወልደ ገብርዔል— የፌዴሬሽን ም/ቤት አባልና የአማራ ክልል ምክር ቤት ሕግ መወሰኛ ክፍል ሰብሳቢ— ትግሬ
  2. ከበደ ጫኔ — የብአዴን ማዕከላዊ ኮምቴ አባል፤ የንግድ ሚኒስትር የነበረ፤ የኢሕአዴግ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የህዝብ ግንኙነት አማካሪ ሚኒስትርና ባሁኑ ወቅት ደግሞ የፌደራል ጉዳዮችና አርብቶ አደር አካባቢ ልማት ሚኒስትር —ትግሬ
  3. ካሳ ተ/ብርሃን— የብአዴን ማዕከላዊ ኮምቴ አባል፣ የፌደራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስትርና ባሁኑ ጊዜ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር— ትግሬ
  4. ሕላዌ ዮሴፍ— የብአዴን ማዕከላዊ ኮምቴ አባልና በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር — ትግሬ
  5. ገነት ገ/እግዚአብሄር—የአማራ ክልል ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ—ትግሬ
  6. ተሠማ ገ/ሕይወት— የብአዴን አመራር አባልና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድሩ አማካሪ —ትግሬ
  7. ልዑል ዮሐንስ — የብአዴን አመራር አባል፣ «የአማራ ክልል» ባህልና ቱሪዝም ቢሮም ክትትል — ትግሬ
  8. ጸሃዩ መንገሻ — የብአዴን አመራር አባልና የወልዲያ ከተማ ከንቲባ— ትግሬ
  9. ሙሌ ታረቀኝ [አምባሳደር] — የብአዴን ከፍተኛ አመራር አባል፣ የኢሕአዴግ ጽ/ቤት ሕግ ክፍል ሀላፊና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የካቢኔ ጽህፈት ቤት ኃላፊ —ትግሬ
  10. ሐዱሽ ሐለፎም — የብአዴን አመራር አባልና የአብክመ ገ/ኢ/ል/ት/ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ — ትግሬ
  11. ጀኔራል ስዩም ሀጎስ — የምዕራብ እዝ አዛዥ ሆኖ የሰራ፤ መጀመርያ የሕወሓት ታጋይ የነበርና “አማራ ነኝ” ብሎ ኢሕዴንን የተቀላቀለ—ትግሬ
  12. ሃዲስ ሃለፎም — የብአዴን አመራር አባልና የአማራ ክልል የገንዘብ ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር— ትግሬ
  13. የማነ ታደሰ — የብአዴን አመራር አባልና የአማራ ክልል የጸጥታ ዘርፍ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር— ትግሬ
  14. ተክሉ የማነ ብርሃን — በአማራ ክልል በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር — ትግሬ
  15. ካሳሁን አብርሃ — የብአዴን አባልና የጎንደር ኢርፖርት ደሕንነት ኃላፊና የጎንደር ከተማ ወጣቶች ሊግ— ትግሬ
  16. አብርሃም ገብረመድህን — የብአዴን አመራር አባልና የደብረብርሃን ገቢዎች ዳይሬክተር— ትግሬ
  17. አብርሃም ወልደግብርኤል — የብአዴን አመራር አብልና በአማራ ክልል የመንግስት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት— ትግሬ
  18. አቶ በርሄ ገብረማሪያም— የብአዴን የአመራር አባልና የከሚሴ ከተማ ሆስፒታል ዳይሬክተር— ትግሬ
  19. ብርሀኔ ቸኮል — የብአዴን የአመራር አባልና የደብረብርሃን ከተማ ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ— ትግሬ
  20. አብረሀት ዘራይ — የብአዴን የአመራር አባልና የምስራቅ ጎጃም የመምህራንና የትምህርት ተቋማት ዘርፍ አስተባባሪ— ትግሬ
  21. ኪዳነማሪያም ፍስሃ — የብአዴን የአመራር አባልና የጎንደር ከተማ የህብረት ስራ ማህበር ማሰተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ— ትግሬ
  22. ሰለሙን ሙሉጌታ — የብአዴን የአመራር አባልና የጎንደር ከተማ ብአዴን ኃላፊ— ትግሬ
  23. ተሰፋይ ሞገሰ — የብአዴን የአመራር የጎንደር ከተማ ቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ— ትግሬ
  24. ትዕዛዙ አፅብሃ — የብአዴን የአመራር አብልና የጎንደር ከተማ የከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ— ትግሬ
  25. አብዮት ብርሃኑ ገ/መድህን— የብአዴን የአመራር አባልና የጎንደር ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ— ትግሬ
  26. ቻላቸው ዳኛው— የብአዴን የአመራር አባልና የጎንደር ከተማ ፅዳት ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ— ትግሬ
  27. አባዲ አበበ — የብአዴን የአመራር አባልና የጎንደር ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት የሰራ ሂደት አሰተባባሪ — ትግሬ
  28. ጉኡሽ አምባዬ– የብአዴን የአመራር አባልና የይልማና ዴንሳ ወረዳ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል—ትግሬ
  29. ሲሳይ ዘሪሁን – የብአዴን አመራር አባልና የደ/ወሎ ዞን ብአዴን ጽ/ቤት ኃላፊ — ትግሬ
  30. አለም ግዴይ– የብአዴን የአመራር አባል፣ የደሴ/ዙሪያ ወረዳ መሬት አስተዳደር ኃላፊና የደሴና አካባቢው የሕወሓት መረጃ ኃላፊ [2 ደመወዝ የሚከፈለው] — ትግሬ
  31. ዶክተር አሚር አማን ሐጎስ— የብአዴን ስራ አስፈጻሚና የጤና ጥበቃ ሚንስትር — ትግሬ
  32. ልዑል መኮነን የአብክመ/ባቱ/ቢሮ ምክትል ኃላፊ— ትግሬ

ምንጭ https://www.satenaw.com/amharic/wp-content/cache/all/amharic/archives/63084/index.html

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on September 3, 2018
  • By:
  • Last Modified: September 3, 2018 @ 2:42 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar