www.maledatimes.com ባለቤቴ የእራሱን ህይወት አያጠፋም የኢንጂንየር ስመኘው በቀለ ባለቤት (ካናዳ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ባለቤቴ የእራሱን ህይወት አያጠፋም የኢንጂንየር ስመኘው በቀለ ባለቤት (ካናዳ)

By   /   September 7, 2018  /   Comments Off on ባለቤቴ የእራሱን ህይወት አያጠፋም የኢንጂንየር ስመኘው በቀለ ባለቤት (ካናዳ)

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 24 Second

ይልቅ ወሬ ልንገርህ

ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ራሳቸውን ማጥፋታቸውን ፌደራል ፖሊስ ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡
የኢንጂነር ስመኘው በቀለ ባለቤት ወ/ሮ እሙን ማዘንጊያሽ ከሁለት ሳምንታት በፊት
‹ይድረስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ› ትላለች ከካናዳ ቶሮንቶ (በተለይ ለቁም ነገር መጽሔት)
‹ባለቤቴ የራሱን ሕይወት ያጠፋል ለማለት እቸገራለሁ›
የተከበራችሁ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼ፤
ወ/ሮ እሙን ማዘንጊያ እባላለሁ፡፡
የአቶ ስመኘው በቀለ ባለቤትና የልጆቹ፤ የበእምነት ስመኝው፤ አሜን ስመኘውና ጽናት ስመኝው እናት ነኝ፡፡ በአሁኑ ወቅት ነዋሪነቴ፤ በቶሮንቶ ካናዳ ነው፡፡
ዛሬ ከፊታችሁ ተገኝቼ ይህንን መግለጫ የምሰጥበት ምክንያት ከሁላችሁም የተሰወረ አይደለም፡፡ የባለቤቴን፤ የአቶ ስመኘው በቀለን ድንገተኛ ምስጢራዊ ሞት ይመለከታል፡፡
ሀሙስ፤ ሀምሌ 19 ቀን፤ 2010 ዓ.ም. ለኔና ለቤተሰቦቼ፤ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ህዝብ አሳዛኝ ቀን ነበር፡፡ በመገናኛ ብዙሀን የተለቀቀው፤ ባለቤቴ፤ ስመኝው በቀለ፤ ጠዋት በመስቅል አደባባይ፤ ሞቶ ተገኘ፤ የሚለው ዜና፤ ቅስም ሰባሪና አስደንጋጭ ነበር፡፡ ባለቤቴን እስከማውቀው ድረስ፤ ፈሪሀ እግዚአብሄር ያለው፤ ታታሪ፤ አገሩንና ቤተሰቡን የሚወድ፤ በምንም አይነት መልኩ ልጆቹን፤ አገሩንና ቤተሰቡን ጥሎ፤ የራሱን ሕይወት ያጠፋል ብዬ የማላስበው ሰው ነው፡፡ ስለዚህ ባለቤቴ ራሱን አጠፋ ለማለት እቸገራለሁ፡፡
በዚህ በስደት በምኖርበት ካናዳ፤ የባለቤቴን ድንገተኛ ሞት በሰማሁ ግዜ፤ ሀዘኔ መሪር ሆኗል፡፡ የስደትን አስከፊ ገጽታ የተረዳሁበት ክስተትና ዜና ነው፡፡ ስለዚህም ላለፉት 4 ሳምንታት በአደባባይ ወጥቼ፤ ሀዘኔን መግለጽ፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ማመስገን አልቻልኩም፡፡
በባለቤቴ ሞት መሪርና የማይቆርጥ ሀዘን ቢሰማኛም፤ የባለቤቴን ሞት ተከትሎ የኢትዮጵያ ህዝብ ያሳየው ፍቅር፤ ድጋፍና፤ የሀዘን መግለጫ፤ መጽናኛ ሆኖኛል፡፡ ባለቤት ለሀገሩ ካለው ጽኑእ ፍቅር የተነሳ፤ የራሱንና የልጆቹን ህይወት በድሎ ለህዳሴው ግድብ ግንባታም ይሁን ለሌሎች ታላላቅ ግድቦች ግንባታ መስዋእትነት ከፍሏል፡፡ ሞቱን ተከትሎም፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ያሳየው ፍቅር፤ ባለቤቴ እንዳልሞተና፤ በስራው ሕያው ሆኖ እንደሚኖር አሳይቶኛል፡፡
በዚህ አሳዛኝና አስቸጋሪ ወቅት፤ ከጎኔ በመሆን ላጽናናችሁኝ፤ የቶሮንቶና አካባቢው ኢትዮጵያውያንና ኤርትራዊያን፤ እንዲሁም በአገርቤት ልጆቼን የተንከባከባችሁልኝ ወገኖቼ፤ ፈጣሪ ብረድራችሁን ይክፈል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት፤ የባለቤቴን አሟሟት አጣርቶ፤ እውነታውን ለኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
ወደፊት፤ ጊዜና ሁኔታዎች ሲፈቅዱ፤ የማውቀውንና የሚሰማኝን በሰፊው እስገልጽ ድረስ፤ ልክ እንደእስካሁኑ ሁሉ; በአርምሞና በጸሎት; ግዜዬን እንዳሳልፍ እንደምትፈቅዱልኝ አምናለሁ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on September 7, 2018
  • By:
  • Last Modified: September 7, 2018 @ 8:31 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar