www.maledatimes.com በአዲስ አበባ ቅቤን ከቫዝሊን ጋር እና ማርን ከመኪና ዘይት ጋር ቀላቅሎ ሲሸጥ የተገኘው ወጣት በቁጥጥር ስር ዋለ። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በአዲስ አበባ ቅቤን ከቫዝሊን ጋር እና ማርን ከመኪና ዘይት ጋር ቀላቅሎ ሲሸጥ የተገኘው ወጣት በቁጥጥር ስር ዋለ።

By   /   September 11, 2018  /   Comments Off on በአዲስ አበባ ቅቤን ከቫዝሊን ጋር እና ማርን ከመኪና ዘይት ጋር ቀላቅሎ ሲሸጥ የተገኘው ወጣት በቁጥጥር ስር ዋለ።

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 1 Second

በአዲስ አበባ ከተማ አንድ ወጣት ቅቤን ከቫዝሊን ቅባትና ከሌሎች በዓድ ፈሳሾች ጋር፣ ማርን ደግሞ ከመኪና ዘይት፣ ከገላ ሳሙናና ከሌሎች በዓድ ፈሳሾች ጋር ቀላቅሎ በማዘጋጀት ለገበያ ሊያወጣ ሲል በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ።

ለፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሰረት በአካባቢው የሚወጣው ጠረን ህብረተሰቡን ኑሮውን ከማወኩም በላይ የእለት ከእለት ህይወቱን መምራት ባለመቻሉ ምክንያት ከአካባቢው የሚወጣውን ጠረን ምን እንደሆነ እንከታተሉላቸው በማመልከታቸው እና ይህ ተጠርጣሪ ግለሰብ በየጊዜው የሚያደርጋቸው ነገሮችም ከአካባቢው ነዋሪዎች ሁኔታ ለየት ያለ በመሆኑ ጥርጣሬው ጠንክሮ ፖሊስ ምርመራ እንዲያደርግበት አስችሎታል።

 ከፖሊስ ምርመራ ለማለዳታይምስ ከቀረበው መረጃ መሰረት ወጣቱ የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን በመጠቀም ከማር፣ቅቤ፣እና ሌሎች ምግብ ነክ ነገርችን በመቀላቀል ለህብረተሰብ ገበያ ላይ ማዋሉን ከማስረጃ ጋር አያይዞ በማቅረብ ክስ ሊመሰርትበት እንደቻለ መረጃው ይጠቁማል ።

ወጣቱ ይጠቀምባቸው የነበሩት ንጥረ ነገሮች የመኪና ዘይት ፣ሳሙና፣ ቫዝሊን ቅባት፣ የፀጉር ፈሳሽ ቅባቶች፣ ሌሎችም የሰውን ልጅ ህይወት በአፋጣኝ ደረጃ የሚጎዱ እና ለሞት የሚያደርሱ ንጥረ ነገሮችን ተጠቅሟል ሲል ምርመራው ይጠቁማል።

ወጣቱ ከፍተኛ ቁጥር ያለውንም ማህበረሰብ ለተለያዩ በሽታዎች ዳርጎታል እስከአሁንም ድረስ በሚያመርታቸው ምርቶች ተጠቀሞ ህይወቱ ያለፈ ሰው ቢኖርም ማንም ሰው ምርመራ እንዲደረግለት አልጠየቀም ይህም በመሆኑ ይህ ወጣት በመጀመሪያ ደረጃ የወንጀል ክስ ሊጠየቅ የገባል ሲል የመርማሪ ፖሊስ መዝገብ ይጠቁማል በምግብ መበከል የሚታመሙ ወገኖች ካሉም ከማናቸውም ከሚጠራጠሯቸው ምግቦች ጋር በማያያዝ ለምርመራ ይረዳ ዘንድ ወደ ፖሊስ በማምራት የምርመራ መዝገብ መስከፈት አለባቸው ተብሏል።

በቅርቡ ፍርድቤት እንደሚቀርብም ይፋ ሆኖአል።

ማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on September 11, 2018
  • By:
  • Last Modified: September 11, 2018 @ 5:28 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar