ዛሬ ከኦሮሚያ ክልል የመጡት የኦነግ አቀንቃኝ ወጣቶች ከአስኮ በመጀመር የኦነግን ባንዲራ በመስቀል እስከ ፓስተር የመንገዱን አካፋይ ከርቭ ስቶን በኦነግ ባንዲራ ሲቀቡ እና የተሰቀለውን የኢትዮጵያ ባንዲራ እያወረዱ የኦነግን ሲሰቅሉ እንዴት ታደርጋላችሁ ያለው ወጣት እርስ በርሱ ተጋጭቷል መኪኖች ተሰብረዋል ወጣቶች ተጎድተዋል!
ፖሊስ የኦነግ ወጣቶችን እንደ እንቁላል ተንከባክቦ ወደ መጡበት ክልል ሲሸኝ ለምን የኢትዮጵያ ባንዲራ ወረደ ከተማችንን በኦነግ ቀለም አይቀባም ያለውን የአዲስ አበባን ወጣትን ግን እንደ እባብ በአስለቃሽ ጭስና በዱላ ሲቀጠቅጥ ውሏል!
97 በኋላ አዲስ አበባ ፖሊስ ለአዲስ አበባ ወጣት ዱላውን እና አስለቃሽ ጭሱን ጨክኖ ተጠቅሟል!
ፍርሀት አልባ ወጣቱም በወኔና በአልደፈር ባይነት የሀገሩን ባንዲራ ለብሶ ሲጋፈጥ ውሏል
ማምሻውን የተረጋጋ ቢሆንም የአዲስ አበባን ወጣት ወደ አላስፈላጊ ነገር ውስጥ እየከተቱት ያሉትን የዘቀጠ አስተሳሰብ ይዘው የሚመጡትን የኦነግ ወጣት መንግስት አደብ እና ልጓም ሊያበጅለት ይገባል
ዛሬ ከመድኃኔዓለም በፓስተርና አውቶቢስ ተራ የታየው ረብሻ ነገ በመላው አዲስ አበባ ከመዛመቱ በፊት መንግስት በአጭሩ እልባት ይስጥበት!
የአዲስ አበባን ነዋሪ መብት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብቱን ያስከብርለት!
መንግስት ለአንዱ እናት ለሌላው የእንጀራ እናት የሆነው ለምንድነው?
እነ መለስ የነደፉት የአዲስ አበባ ልዩ የጥቅም ጉዳይ ጊዜውን ጠብቆ እየፈነዳ ነው!
ዛሬ በከተማው መጥተው በግድ ከተማዋ ኦነግ ትሁን ያሉ ወጣቶች ነገ በየቤቱ እየገቡ የአዲስ አበባን ነዋሪ ከቤቱ የኛ መሬት ነው እያሉ መንጠቃቸው አይቀርም የኦነግ አስተሳሰብና ዓላማ አሁንም ወደፊትም ለኢትዮጵያ አደገኛ ነው።
የሀገር ባንዲራ አውርደው የፓርቲ ባንዲራ መስቀል የዘቀጠ እና የላሸቀ አስተሳሰብ ማሳያ ነው ይሄ ኦነግና ያደራጃቸውን በጥጋብ የሚደነፉ ወጣቶችን መንግስት ይቆጣጠር አልያ አዲስ አበባ ሰላም እንደማታገኝ የዛሬው ማረጋገጫ ነው!
መንግስት ይሄን ድርጊት በፍትሀዊነት ይመልስ ካለበዚያ በሀይል የአዲስ አበባን ህዝብ አፍኖ ለኦነግ ከለላ የሚሰጥበት አንዳችም ምክንያት የለም!
የዛሬው ግጭት ፎቶዎች ናቸው ይሄ አካባቢ ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል አካባቢ ነው!




-
የአዲስ አበባ መንገዶች ፅዳት ተቆጣጣሪ ክስ በኦነግ ስርአት አልበኞች ላይ ከስ በማቅረብ ቅጣት ማጣል ይገባዋል
Average Rating