www.maledatimes.com ከአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን በመጡ ወጣቶችና ፒያሳ አካባቢ ባሉ ወጣቶች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት አካባቢው ተረብሾ ውሏል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ከአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን በመጡ ወጣቶችና ፒያሳ አካባቢ ባሉ ወጣቶች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት አካባቢው ተረብሾ ውሏል

By   /   September 14, 2018  /   Comments Off on ከአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን በመጡ ወጣቶችና ፒያሳ አካባቢ ባሉ ወጣቶች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት አካባቢው ተረብሾ ውሏል

    Print       Email
0 0
Read Time:46 Second

@ሪፖርተር

ከአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን በመጡ ወጣቶችና ፒያሳ አካባቢ ባሉ ወጣቶች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት አካባቢው ተረብሾ ውሏል፡፡

በተለያዩ አውቶብሶች ፒያሳ መሀል ላይ የተበተኑ ከኦሮሚያ ክልል የመጡ ወጣቶች ገጀራና ሚስማር የተመታበት እንጨት ይዘው እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን፣ የፒያሳ አካባቢ የማኅበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ፖሊስ ጣቢያን ለመዝረፍ እንቅስቃሴ መደረጉንና ፖሊሶችም በጥይት መበተናቸውን፣ ፖሊስ ለሪፖርተር ገልጿል፡፡

የፒያሳ ማኅበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ተረኛ መኰንን ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ 700 የሚሆኑ ወጣቶች ጭነው የመጡት መኪኖች በአካባቢው ወጣቶችና በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ ሪፖርተርም ፖሊስ ጣቢያው ውስጥ ተገኝቶ፣ በአማርኛ መግባባት የማይችሉ ጉዳት የደረሰባቸው ወጣቶች የሕክምና ዕርዳታ ሲጠብቁ ለማስተዋል ችሏል፡፡

በዳግማዊ በአፄ ምንልክ አደባባይ ሐውልትና አካባቢም በመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ ጥበቃ እየተደረገለት የነበረ ሲሆን፣ የፌዴራል አድማ በታኝ ፖሊስም ወደ አመሻሹ አካባቢ ዓርማ የሌለው ሰንደቅ ዓላማ ይዘው ወደ ጎዳና የወጡ የአዲስ አበባ ወጣቶችን ሲበትን ተስተውሏል፡፡

በፒያሳ የሚገኙ ባንኮችና የንግድ መደብሮች ሙሉ በሙሉ ከመዘጋታቸውም በተጨማሪ፣ የትራንስፖርት አገልግሎትም በመቋረጡ ብዙዎች ሲቸገሩ ታይተዋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on September 14, 2018
  • By:
  • Last Modified: September 14, 2018 @ 11:07 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar