www.maledatimes.com የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የስልጠና ሰነዶችን ሊያሻሽል ነው. (የስልጠና ሰነዶች በኢትዮጵያ ያለውን ለውጥ የማይመጥኑ መሆኑ ነው) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የስልጠና ሰነዶችን ሊያሻሽል ነው. (የስልጠና ሰነዶች በኢትዮጵያ ያለውን ለውጥ የማይመጥኑ መሆኑ ነው)

By   /   September 15, 2018  /   Comments Off on የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የስልጠና ሰነዶችን ሊያሻሽል ነው. (የስልጠና ሰነዶች በኢትዮጵያ ያለውን ለውጥ የማይመጥኑ መሆኑ ነው)

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 48 Second

Maleda Times Media Group

የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የስልጠና ሰነዶችን ሊያሻሽል ነው
አዲስ አበባ ነሀሴ 30/2010 የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የስልጠና ሰነዶች በኢትዮጵያ ያለውን ለውጥ የማይመጥኑ በመሆናቸው ማሻሻያ ሊደረግባቸው እንደሆነ አካዳሚው አስታወቀ።
አካዳሚው ከትግራይ፣ ከአማራ፣ ከኦሮሚያና ከደቡብ ክልል የአመራር አካዳሚ ኃላፊዎች በተገኙበት የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት አድርጓል።
የአካዳሚው ፕሬዚዳንት አቶ ዓለምነው መኮንን እንደገለጹት፤ አካዳሚው ለከፍተኛ፣ መካከለኛና ለጀማሪ አመራሮች ስልጠና የሚሰጥባቸው ሰነዶች ማሻሻያ ይደረግባቸዋል።
”በአካዳሚው የሚሰጠው ስልጠና የአመራሩ የአስተሳሰብ አድማስ ለማስፋትና ቁርጠኝነት ለመፍጠር ሲሆን የስልጠና ሰነዶቹ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለውን ለውጥ የሚመጥን ባለመሆኑ ማሻሻል አስፈልጓል” ብለዋል።
እንዲሁም ከዚህ በፊት በአካዳሚው ስልጠና ካገኙ አመራሮች በተገኘ ግብረ መልስ ሰነዶቹን ለማሻሻል አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች መገኘታቸውን አውስተዋል።
በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ የተፈጠረውን ለውጥ ከዳር የሚያደርስ መሪ መፍጠር እንደሚያስፈልግ የገለጹት አቶ ዓለምነው በሁሉም ዘርፍ የሚፈለገውን አመራር ለመፍጠር የስልጠና ሰነዶቹን ማሻሻል እንደሚጠይቅ ተናግረዋል።
“በጠንካራ አመራር ካልተመራ ለውጡ አቅጣጫውን ሊስት ይችላል” ያሉት ፕሬዚዳንቱ ለተግባራዊነቱ አካዳሚው ጠንካራ አመራሮችን መፍጠር እንደሚጠበቅበት ገልጸዋል።

የስልጠና ሰነዶችን ከማሻሻል በተጨማሪ ሰነዶቹን አውቆና ተረድቶ ስልጠና የሚሰጥ አሰልጣኝ የማዘጋጀት ሥራ እንደሚከናወንም ጠቁመዋል።
በኦሮሚያ ክልል የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ማስረሻ በበኩላቸው የስልጠና ሰነዶች ጥሩ ቢሆኑም በአሁኑ ወቅት የተጀመረው ለውጥና ገዢው ፓርቲ ያስቀመጣቸውን አዳዲስ አቅጣጫዎች ማካተት ያለባቸው በመሆኑ ማሻሻል እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
“አካዳሚው እየተንቀሳቀሰ ያለው እንደ አስተባበሪ እንጂ እንደ ትምህርት ተቋም አይደለም” ያሉት አቶ ሀብታሙ ችግሮችን በዘላቂነት የሚፈታ ሥራ መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
የአማራ ክልል የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አበባው ሲሳይ እንዳሉት፤ በሰነዶቹ ላይ በገዢው ፓርቲ የተለዩ ችግሮችና የተቀመጡ አቅጣጫዎች ሊካተቱ ይገባል።
አቶ ዓለምነው በውይይቱ ወቅት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ አሁን ባለው ሁኔታ ሰነዶቹ ይቀጥሉ፣ በከፊል ይሻሻሉ ወይም ይቀየሩ የሚል ውሳኔ ሳያገኝ ስልጠና እንደማይሰጥ ገልጸዋል።
እንዲሁም ሰነዶቹ የቅርጽና የይዘት ማሻሻያ የሚደረግባቸው መሆኑን ጠቁመው ገዢው ፓርቲ በሚያካሂደው ጉባዔ በርካታ ጥያቄዎች ምላሽ የሚያገኙ ሲሆን ማሻሻያውም ያንን ተከትሎ የሚከናወን እንደሆነም ጠቁመዋል።
በተያዘው በጀት ዓመት ከመደበኛ ስልጠናዎች በተጨማሪ የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብን ለማስፋት የሚረዱ ጉባዔዎችና አውደ ጥናቶች እንደሚካሄዱም ገልጸዋል።
አካዳሚው በስልጠና ሰነዶች የሚደረገውን ማሻሻያ ተከትሎ በበጀት ዓመቱ ከፌዴራል፣ ከክልሎችና ከከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ በርካታ ከፍተኛ፣ መካከለኛና ጀማሪ አመራሮች ስልጠና ለመስጠት ዕቅድ ይዟል።
እንዲሁም በመደበኛ መርሐ ግብር የመማርና ማስተማር ሥራ ለመጀመር ሥርዓተ ትምህርት በመቅረጽ ሁለት ፋካሊቲዎችና አምስት ትምህርት ክፍሎችን በማደራጀት በአራት መስኮች የሁለተኛ ዲግሪና በሦስት መስኮች ደግሞ የሦስተኛ ዲግሪ ለማስተማር አቅዷል።
አካዳሚው በበጀት ዓመቱ 125 የአመራር ተማሪዎችን ተቀብሎ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት ለማስተማር የቅድመ ዝግጅት ሥራ በማከናወን ላይ ይገኛል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on September 15, 2018
  • By:
  • Last Modified: September 15, 2018 @ 4:07 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar