መግደል መሸነፍ ነው በሚለው አነጋገራቸው ህዝብን ሲሰብኩ የነበሩት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ፣በአሁኑ ወቅት በእራሳቸው የዘር ገንድ ባላቸው ዜጎች (ኦሮሞዎች ዝርፊያ፣ግድያ፣አስገደዶ ሴቶችን መድፈር፣ መደብደብ፣ እና ሌሎችንም ጥቃቶች በአዲስ አበባ መዲና እና በመውጫ በሮች ላ መፈፀማቸውን እያዩ ዝምታቸውን መርጠዋል ።
ለጠቅላይ ሚንስትርነት ከታጩም ጊዜ ሆነ ከተመረጡም በኃላ በነበራቸው የአነጋገር ዘይቤ እና ስነ ምግባር ብዙዎችን በሀሳባቸው የማረኩ ቢሆንም ወደ ተግባር ላይ በሚመጣው ሂደት ላይ ግን ምንም አይነት ፈጣን ሂደት አላስመዘገቡም ፣በተለይም በወንጀል የመከላከል እና ህዝብን የማዳን ስራው ዋነኛ በመሆኑ እርሳቸው ቀዳሚነትን ሳይጡት ቀርተዋል ። ቀዳሚ ብለው የሰጡት የሀገር ሰላም እና ደህንነት መስፈን ሳይሆን ከሀገር ውጭ ያሉትን መንግስታት እየዞሩ ማነጋገሩ ለእርሳቸው ልክ እንደ ትልቅ እድል ቆጥረውታል ። ታዲያ ይህ በሚሆንበት ሰአት የኦነግ ተወላጆች ሀዝብን በመጨፍጨፍ ላይ ይገኛሉ ጠቅላይ ሚንስትሩም ዝምታቸው በርትቶአል።
ከቡራዩ ዞን ከአሸዋ ሜዳ፣ ቤሮ… አካባቢ ጥቃት ሸሽተው ኮልፌ አጠና ተራ እስላም መቃብር አጠገብ ፊሊጶስ ት/ቤት የተጠለሉ ዜጎች። እርዳታ ትብብር ይሻሉ። በቦታው ሆኜ በአይኑ ተመልክቶ ማረጋገጡን እና ከፎቶግራፍ ጋር ማታየዙን ሲራክ እስክንድር ይጠቁማል።
ዜጎች በመንግስቶቻቸው እና በጎሳዎቻቸው ከሚኖሩባት መንደር በመፈናቀል ከሶሪያ በላይ ከፍተኛው ቁጥር ከኢትዮጵያ እንደሆነ በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት መዘገባችን ይታወሳል ፣አሁንም ከሚኖሩበት ቀዬ እና መንደር መፍለሱ በሰፊው ተጀምሮአል ።
ማለዳ ታይምስ
Average Rating