www.maledatimes.com 🚫አስቸኳይ የድረሱልን ጥሪ ከድሬዳዋ🚫አሰሙ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

🚫አስቸኳይ የድረሱልን ጥሪ ከድሬዳዋ🚫አሰሙ!

By   /   September 20, 2018  /   Comments Off on 🚫አስቸኳይ የድረሱልን ጥሪ ከድሬዳዋ🚫አሰሙ!

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 11 Second

የባለፈው ይብቃን እያሉ ነው 

🚫አስቸኳይ የድረሱልን ጥሪ ከድሬዳዋ🚫

 ድሬዳዋ ባሉ ወገኖቻችን ላይ ታላቅ ስጋት ተደቅኗል፣ ሕዝባችን በሩን ዘግቶ የድረሱልኝ ጩኸቱን እያሰማ ነው፣ "በየበሮቻችን ላይ ቀለም እየቀቡ እያለፉ ነው፣ ምን ዓይነት ድግስ እንደደገሱልን ባይታወቅም ብንኖርም ለእግዚአብሔር ብንሞትም ለእግዚአብሔር ብለን ቁርጣችንን አውቀን ተቀምጠናል።"

የዛሬ ወር ገደማ እንዲሁ በጠራራ ፀሐይ ሰዎች በግፍ ሲገደሉ መንግስት በገዳዮች ላይ ምንም ዓይነት ተመጣጣኝ እርምጃ ባለመውሰዱ በሕዝባችን ላይ ዛሬም ውጥረቱ ነግሷል።

ወሎ ቢነካ፣ ጎንደር ቢነካ፣ ጎጃም ቢነካ፣ ሸገር ቢነካ፣ ደቡብ ቢነካ የሚጮህለት አላጣም፣ ድሬዳዋ ግን በሰማይ ከሚኖረው የቅኖች አባት በቀር ያለ ማንም ተመልካች፣ ባለቤት አልባ ከተማ ሆና በጫት እና በሺሻ አዕምሯቸውን በናወዙ ግለሰቦች 40፣ 40፣ 20፣ በሚል የከፋፍለህ ግዛው አደረጃጀት ለረዥም ዘመናት ልዕልናዋንና ክብሯን አጥታ ሰንብታለች።

  ትላንት በቡራዩና በሌሎች ክልሎች በተፈፀመው ግፍ እና በደል ድፍን የኢትዮጵያ ሕዝብ ደም እንባ አንብቷል፣ ሁሉም የተጎዳውን ማኅበረሰብ መልሶ ለማቋቋም የበኩሉን ጥሯል፣ ዛሬስ ያ ግፍ እና በደል በድሬዳዋ እንዳይከሰት ምን ዋስትና አለን? 

 «ቀድሞ ነበር እጂ መጥኖ መደቆስ፣ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ።» እንዲሉ፣ ይህ ስጋት እውን ከመሆኑ በፊት ለወገን ደራሽ ወገን ነውና፣ በመቃብር ስፍራ እንደሚያንዣብቡ ጥን`ባሳ አሞሮች በወገኖቻችን ላይ ሰይፍና ገጀራ ይዘው ሌት ተቀን በከተማይቱ አደባባይ የሚሳለቁትን የቃየል ልጆ ለማስታገስ መንግስት ተገቢውን ጥረት ካላደረገ፣ አገር ተሸብሮ፣ ሕዝብ ካለቀ በኋላ በየመገናኛ ብዙኃንና በየማኅበራዊ ሚዲያ ብቅ እያሉ የሐዘን እንጉርጉሮ ቢሰጡ፣ ልቡ በሐዘን በተሰበረው ወገናችን ፊት ቆመው ሰልፊ ቢነሱስ ምን ጥቅም አለው? 

 ስለሆነም! በማኛውም አጋጣሚ በመንግስት የአመራርነት ስፍራ ያላችሁም ሆነ ተሰሚነት የሚኖራችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በድሬዳዋ ላለው ምስኪን ሕዝባችን ድምፅ ትሆኑት ዘንድ ወገናዊ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።

           ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
                     ©በረከት ገበሬ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on September 20, 2018
  • By:
  • Last Modified: September 20, 2018 @ 10:00 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar