በአዲስ አበባ ለዓመታት ታጥረው የተቀመጡ 400 ቦታዎች ተለዩ ሼክ መሀመድ ሁሴን ከሃያ አመታት በላይ 13 ቦታዎችን አሳጥረው ያለምንም ለውጥ የግል ንብረታቸው አድርገው ቆይተዋል! ሊነጠቁ እና ላልተጠቀሙበት እንዲሁም ሌሎች እንዳይጠቀሙበት ላስተጓጎሉበት የካሳ ክፍያ እንዲሁም የመሬት ታክስ ቀረጥ መከፈል ይገባቸዋል መሬቱም በአፋጣኝ ለሌሎች ባለሀብቶች በአስቸኳይ መሰጠት አለበት።
ለካቢኔው የውሳኔ ሐሳብ ሊቀርብ ነው
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ግንባታ ሳይካሄድባቸው ለዓመታት ታጥረው የተቀመጡ 400 ቦታዎች ለየ፡፡ በምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) የሚመራው ካቢኔ ዕርምጃ ለመውሰድ እንዲያመቸው በቅርቡ የውሳኔ ሐሳብ ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
አዲሱ የከተማው አስተዳደር የከተማውን ቁልፍ ከተረከበ በኋላ በመሬት፣ በቤቶችና በተለያዩ ግንባታዎች ላይ ኦዲት አካሂዷል፡፡
በዚህ መሠረት በማዕከልና በክፍላተ ከተሞች በአጠቃላይ 400 ቦታዎች ታጥረው ለዓመታት የተቀመጡ በመሆናቸው፣ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ በእነዚህ ቦታዎች ላይ መወሰድ ስላለባቸው ዕርምጃዎች ሁለት የውሳኔ ሐሳቦችን አዘጋጅቷል፡፡
የመጀመርያው የውሳኔ ሐሳብ መሬቱን የተረከቡት አልሚዎች ግንባታ ያላካሄዱት በከተማ አስተዳደሩ ችግር በተለይም በፕላን ተቃርኖ ከሆነ፣ መፍትሔው ችግሩን ፈትቶ በድጋሚ መዋዋል ነው፡፡ ነገር ግን ሁለተኛው በቅርቡ ለካቢኔ ይቀርባል ተብሎ የሚጠበቀው የውሳኔ ሐሳብ፣ በራሳቸው ችግር ሳቢያ የወሰዱትን መሬት አጥረው የቆዩትን ባለሀብቶች እንዲነጠቁ የሚጠይቅ መሆኑን ከከተማ አስተዳደሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ምክትል ከንቲባ ታከለ ሥልጣን ከመረከባቸው በፊት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት አጥረው የያዙ ባለሀብቶች ወደ ግንባታ እንዲገቡ የመጨረሻ ዕድል ሰጥቶ ነበር፡፡
በተለይም ሼክ መሐመድ አል አሙዲ አጥረው የያዙዋቸው 13 ቦታዎች እንዲነጠቁ የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ እሳቸው በሳዑዲ ዓረቢያ በእስር ላይ የሚገኙ በመሆናቸውና የአገር ባለውለታ ስለሆኑ፣ በሌሉበት ዕርምጃ መውሰድ አግባብ አይደለም በሚል በይደር ቆይቷል፡፡
በአሁኑ ወቅት እንደ አዲስ በተዘጋጀው የውሳኔ ሐሳብ የሼክ አላሙዲ 13 ቦታዎች መካተታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የከተማ አስተደዳደሩ ያለ ሥራ የተቀመጡ ቦታዎች በአስቸኳይ ወደ ልማት መግባት እንዳለባቸው ስለሚፈልግ፣ የአብዛኛዎቹ ካርታ ይመክናል ተብሎ ይጠበቃል
Average Rating