www.maledatimes.com ሕወሓት 11 የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን መረጠ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ሕወሓት 11 የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን መረጠ

By   /   October 1, 2018  /   Comments Off on ሕወሓት 11 የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን መረጠ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 20 Second

  1. ሕወሓት 11 የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን መረጠ

ሕወሓት 11 የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን መረጠ

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) እያካሄደ ባለው 13ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ 11 የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን መረጠ፡፡

የድርጅቱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በመሆን የተመረጡት ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር)፣ ወ/ሮ ፈትለ ወርቅ ገብረ እግዚአብሔር፣ አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ (አባይ ነብሶ)፣ አቶ ዓለም ገብረ ዋህድ፣ አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር)፣ አክሊሉ ኃይለ ሚካኤል (ዶ/ር)፣ አቶ በየነ ምክሩና አዲስ ዓለም ባሌማ (ዶ/ር) ናቸው፡፡ ጉባዔው ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) እና ወ/ሮ ፈትለ ወርቅ ገብረ እግዚአብሔር የድርጅቱ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል፡፡

በተያያዘ ዜና፣ ድርጅቱ ዛሬ መስከረም 21 ቀን 2011 ዓ.ም. ጠዋት 55 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን መርጧል፡፡

ሕወሓት በጉባዔው 65 ዕጩዎችን ለማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት አቅርቦ የነበረ ሲሆን፣ በተደረገው የድምፅ አሰጣጥ 55 አባላትን ለማዕከላዊ ኮሚቴ መርጧል፡፡

በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ከተመረጡት መካከል የድርጅቱ ሊቀመንበርና ትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር)፣ የቀድሞው የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ፣ የኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፈትለ ወርቅ ገብረ እግዚአብሔር፣ በፓርላማ የመንግሥት ተጠሪ አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር)፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ የትግራይ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ረዳኢ ሐለፎም፣ የቀድሞ የብሔራዊ ደኅንነትና መረጃ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋ ይገኙበታል፡፡

የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች የሆኑት ኦሕዴድና ብአዴን ስማቸውን ወደ ኦዴግና አዴግ ቢቀይሩም፣ ሕወሓት ስሙን እንደማይቀይርና የፓርቲውም ፕሮግራም አብዮታዊ ዴሞክራሲ ሆኖ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

ካሁን ቀደም የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት 45 የነበሩ ሲሆን፣ ጉባዔያቸውን ያደረጉት ኦዴግ፣ አዴግና ሕወሓት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ቁጥር ወደ 55 አሳድገዋል፡፡

ሕወሓት በጉባዔው 12 አንጋፋ የድርጅቱ አባላትን በክብር ማሰናበቱን አስታውቋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on October 1, 2018
  • By:
  • Last Modified: October 1, 2018 @ 3:28 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar