ዶ/ር ዐቢይ ለኢትዮጵያ የጻፈው
‹‹እኔ አንችን ስወድሽ››
—›
ልክ እንደ ምኒልክ – እንደነ ጣይቱ፤
ለአንች ነፃነት – እንደሚቆጡቱ…
እንደ አፄ ካሌብ – ባሕር ተሻግሬ፤
እንደ አባባ ጃንሆይ – ክፉን ተናግሬ፤
እንደ አፄ ዮሐንስ – አንገቴን ሰጥቼ፤
ልክ እንደ መይሳው – ራሴን ሰውቼ፤
እንደነ ገብርዬ – እንደ ጀግናው በላይ፤
ከአንች ክብር በቀር – የራሴን ቤት ላላይ፤
በፍጹም መታመን፤
በጽናት በመቆም – ከሕዝቦችሽ ጋራ፤
ወይ በአንድነት ልንኖር…
ወይም ላ‘ንች ክብር – ሞትን ልንጋራ፤
—›
እኔ አንችን ስወድሽ…
ቃሌን ያደመጠ – ተስፋየንም ያዬ፤
ሼሁ እየሰገደ – ቄሱ እየጸለዬ፤
በሕዝብ እንባና – በሕፃን ለቅሶ፤
የእናቶች ጸሎት – ወደ ጌታ ደርሶ፤
ጥበብ እንዲቸረኝ – የሰማዩ መሪ፤
እየተንበረከክሁ – ለአንችው ፈጣሪ፡፡
—›
እኔ አንችን ስወድሽ…
በሰላም አይደለም – ጸጥታ ባለበት፤
በተንኮል መሐል ነው – ሴራ በበዛበት፡፡
-›
በጥንቃቄ ነው – ያለመዘናጋት፤
በብዙ ሩጫ ነው – ሌት ተቀን በመትጋት፡፡
ክፉ ሚያሴሩብሽ – እንዳሉ ሰምቼ፤
እንቅልፍ እየነሳኝ – ረፍቴን አጥቼ፡፡
-›
ይኸው ጊዜው ከፍቶ – በእጅሽ የበላ፤
ከመሶብሽ ሰርቆ – ጓዳውን የሞላ፤
ማመስገኑ ቢቀር – በቃኝ ማለት ትቶ፤
ጅብ ሆኖ መጣብሽ…
መብላቱ ሲገርመን – ሊያስበላሽ አጫርቶ፡፡
—›
እኔ አንችን ስወድሽ…
የመበቃቀልን – የአጋንንት ሴራ፤
የጎጠኝነትን – የስንፍና ሥራ፤
የምቀኝነት – የተንኮልን ገመድ፤
የመጠፋፋትን – የዝቃጮች ወጥመድ፤
በፍቅር ረትቼ፤
ምህረትን ሰጥቼ፤
ሌባን አስመልሼ፤
ለተበዳይ ክሼ፤
ለተጣሉ እርቅን – ለሌቦች ይቅርታን፤
ለወጣቶች ተስፋን – ለአባቶች ጡረታን፤
ለእናቶች ሳቅን – ለሕፃናት ደስታን…
ለመስጠት ሌት ተቀን – እየለፋሁልሽ፤
በማይሻር ኪዳን – ሰርክ እየማልሁልሽ!!!
—›
እኔ አንችን ስወድሽ…
በበፍጹም እምነት ነው – ፍርሃት አስወግጄ፤
የተንኮል ተራራን – ከሕዝብሽ ጋር ንጄ፤
በአምላክሽ አምኜ – ተስፋሽን አጽንቼ፤
ከቻልሁ ልሞትልሽ – ልክ እንደ አባቶቼ!!!
—›
እንጅ እናታለም…
እንደ የቀን-ጅቦች – ፈጽሞ አልወድሽም፤
ከሕዝበብሽ ነጥዬ…
ከአካልሽ ከፍዬ – ጠላት አልሰጥሽም፡፡
-›
አካልሽን ነክሶ…
መንፈስሽን ረብሾ – ልብሽን ‘ሚያደማ፤
ላ’ንች የጅብ አንጀት – የለኝም እማማ !!!
Hafi Christian
‹‹እኔ አንችን ስወድሽ››
Read Time:1 Minute, 9 Second
- Published: 6 years ago on October 5, 2018
- By: maleda times
- Last Modified: October 5, 2018 @ 4:56 pm
- Filed Under: Ethiopia
Average Rating