www.maledatimes.com ‹‹”ልጄ ከሞተ ጀምሮ በሀዘንና ትካዜ ውስጥ ነኝ፤'”»የኢንጅነር ስመኘው በቀለ አባት!! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

‹‹”ልጄ ከሞተ ጀምሮ በሀዘንና ትካዜ ውስጥ ነኝ፤'”»የኢንጅነር ስመኘው በቀለ አባት!!

By   /   October 8, 2018  /   Comments Off on ‹‹”ልጄ ከሞተ ጀምሮ በሀዘንና ትካዜ ውስጥ ነኝ፤'”»የኢንጅነር ስመኘው በቀለ አባት!!

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 51 Second

የሽባባው ዘመዶች የት ደረሳችሁ በልጃችሁ ስም መነገድ እና በቃል አለመገኘት ምን ያህል ከባድ ነው?

Image may contain: 2 people, outdoor

Image may contain: 1 person

https://t.me/yemelikam/14

ወንድማችን ሀይለማሪያም ቀሬ

ይህን ሼር እንድናረግ በውስጥ መስመር ልኮልናል። 
በምንችለው እንርዳቸው ። ለኢንጅነር ስመኘው በቀለ አባትና ቤተሰብ በመርዳት እንታደጋቸው ።

‹‹ልጄ ከሞተ ጀምሮ በሀዘንና ትካዜ ውስጥ ነኝ፤
የነፃ-ህክምና ድጋፍ ይደረግላቸው የሚል ብጣሽ ወረቀት ይፃፍልኝ::››
‹‹በሚዲያ እንደሚረዱኝ የገለጹ አካላት እስካሁን ምንም አላደረጉልኝም፡፡›› የሟች ኢንጅነር ስመኘው በቀለ አባት- አባ በቀለ አይናለም

ባሕር ዳር፡መስከረም 14/2011 ዓ.ም(አብመድ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ስራ አስኪያጅ የነበሩት የሟች ኢንጅነር ስመኘው አባት አባ በቀለ አይናለም ከጎንደር ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው ሳይና ሳቢያ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ሸንበቂት ቀበሌ ነው የሚኖሩት፡፡
ሸንበቂት አነስተኛ የገጠር ከተማ ናት፡፡ ከተማዋን ከሁለት የሚከፍላት ከጎንደር ወደ ደባርቅ ከተማ የሚወስድ የመኪና መንገድ ይገኛል፡፡ ከዚህ መንገድ በቀኝ በኩል ከአምስት ያልበለጡ ቆርቆሮ በቆርቆሮ የተሰሩ ቤቶች ይገኛሉ፡፡

ከነዚህ ቤቶች በአንዱ ነው የኢንጅነር ስመኘው አባት የ88 ዓመቱ አባ በቀለ አይናለም የሚኖሩት፡፡ ቤቱ የድሮው መንገድ ስራ ድርጅት አውራ ጎዳና የእቃ ማስቀመጫ ነበር፡፡ ግድግዳውም ፣ጣሪያውም በቆርቆሮ የተሰራ ነው፡፡

አይደለም ቤት ውስጥ ገብተው ወጭ ሁኖ ላየው የሟች አባት ከሀዘናቸው በላይ ብርዱና ሙቀቱ እየተፈራረቀ እንደሚያስቸግራቸው ለአንድ አፍታ መገመት አያዳግትም፡፡
ወደ ቤት ውስጥ ለመግባት በሩ አካባቢ እንደደረሱ ኢንጅነር ስመኘውን ከልጅነት እስከ አዋቂነት የእድሜ ደረጃ የሚያሳዩ ፎቶዎች ከቆርቆሮ ግድግዳው ላይ አሉ፡፡ እንደገቡ ሁለት የጠፍር አልጋዎች ይመለከታሉ፡፡ ወደ ቤት እንደገባሁ ከጎን ካለችው ባርጩሜ ላይ ደግሞ ነጭ ጭራ በቀኝ እጃቸው የያዙ፣ በግራ ትክሻቸው የጸሎት ማድረሻ መፅሀፍ ቅዱስ ያነገቱ እና ቢጫ የመነኩሴ ፎጣ የደረቡ ሰው ተቀምጠው አገኘሁ፡፡ እርሳቸው የኢንጅነር አባት አባ በቀለ ናቸው፡፡ በዚህ ቤት ውስጥ ብቻቸውን ነው የሚኖሩት፡፡ ባለቤታቸውን በሞት ከተነጠቁ ቆይተዋል፡፡ አንድ ልጃቸው ኢንጅነር ስመኘው ብቻ ነበር፤እርሱም የማይቀረውን የእናቱን መንገድ ተከትሎ ሄዷል፡፡

አባ በቀለ ይናገራሉ ‹‹በቅርቡ ሞት የነጠቀኝን ብቸኛውን ልጄን ስመኘው ብየ ስም ያወጣሁለት ያለ ምክንያት አይደለም፤ከሟች እናቱ ጋር ትዳር በያዝን በአስር ዓመታችን በስንት ስለት ፈጣሪ አንድ ፍሬ ልጅ እንዲሠጠኝ በጠየኩት መሰረት ስለሰጠኝ ነው፡፡ እሱ የስለት ልጅ ነበር›› ይላሉ፡፡

‹‹እርጅና ሲመጣ ጧሪ እንዲሆነኝ፣ ከዚያም አልፎ ለእናት ሀገሩ ኢትዮጵያ ጋሻ፣መከታ እንዲሆን ከሀይማኖታዊ እስከ ዘመናዊ ትምህርት አስተምሬው ነበር፡፡ የተሻለ ትምህርት እንዲያገኝ ደሴ ይኖር ከነበረው ከወንድሜ ቢልልይ አይናለም ሰድጀ ከሰባት እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል እንዲማር አድርጌው ነበር፡፡ምኞቴ ተሳክቶ፣ በነበረበት የኃላፊነት ቦታ ተቀምጦ ሳየው ደስተኛ ነበርኩ፡፡ ስራ ይበዛበት ስለነበር ከስልክ ውጭ በአካል ተገናኝተን የምናውቅባቸው ቀናት ትንሽ ነበሩ፡፡ እናፍቀውም ነበር፡፡እሱ ከሞተ ጀምሮ ቀን ከሌት በሀዘን ውስጥ ነኝ፡፡ የአሟሟቱ ሁኔታም በጣም ያሳስበኛል›› ነበር ያሉኝ፡፡

‹‹በዚህ ላይ ህመሙ ተጫጭኖኛል፡፡ እንደምታየው አይኔን አሞኛል፤የጨጓራ እና የልብ ህመም አለብኝ፡፡ ብቸኛው ልጄ በመጠኑ በገንዘብም በሀሳብም ይረዳኝ ነበር ፡፡ ሞት ነጠቀኝ፡፡ ሀዘኑ የኔ ብቻ እንዳልነበር እና የኢትዮጵያ ህዝብ መሆኑን ሳስብ ትንሽ እፅናናለሁ፡፡አሁን ግን ከፋኝ፡፡ ከቻልክ የነፃ-ህክምና ድጋፍ ይደረግላቸው የሚል ብጣሽ ወረቀት አስፅፍልኝ? ብዙ ሰዎች በሚዲያም፣ በአካልም ‹አይዞዎት እንንከባከብዎታለን!› ብለው ቃል ገብተውልኝ ነበር ፤ግን ማንም ድጋፍ ያደረገልኝ የለም፡፡ የዘመን መለወጫ ቀን የሸንበቂት ወጣቶች አብረውኝ ውለው ደስ ብሎኛል፡፡ ከዛ ወዲህ ግን ማንም የደረሰልኝ የለም›› ነበር ያሉት፡፡
አባ በቀለ አይናለም 1928 ዓ.ም በዳባት ወረዳ ወቅን ከተማ አቅራቢያ ወይብላ ማርያም ተብሎ ከሚጠራው ቦታ ነበር የተወለዱት፡፡ በአውራ ጎዳና የመንገድ ስራ ድርጅት በጥበቃ ተቀጥረው ድርጅቱ በተንቀሳቀሰባቸው አካባቢዎች ሁሉ እየተዘዋወሩ ይሰሩ ነበር፡፡ 
በ1971 ዓ.ም ነበር አሁን ወደ ሚኖሩበት ሸንበቂት ከተማ የመጡት፡፡ ይህችው ቤትም ያኔ ዘብ ይጠብቁባት የነበረች ቤት ናት፡፡ ለ40 ዓመታት ያህልም እየኖሩባት ይገኛሉ፡፡
ከኢንጅነር ስመኘው ሌላ ልጅ አልነበራቸውም ፡፡ በአካባቢውም አንድም የስጋ ዘመድ ያለው ሰው የላቸውም፡፡ ካለፉት 17 ዓመታት ጀምሮ አልፎ አልፎ ምግብ የሚሰጧቸው እና ንፅህናቸውን የሚጠብቁላቸው ጎረቤታቸው ወይዘሮ ሙቀቴ ታደሰ የተባሉ እናት ናቸው፡፡

የአባ በቀለ ጎረቤት ወይዘሮ ሙቀቴ ካሉት የቆርቆሮ በቆርቆሮ ቤቶች በአንዱ ውስጥ ይኖራሉ፡፡ የጉልበት ስራ እየሰሩ ልጆቻቸውን ያስተዳድራሉ፡፡ አልፎ አልፎ ደግሞ የአባ በቀለን ቤት ያፀዳሉ፣ቤት ያፈራውን ምግብ አዘጋጅተው ይመግባሉ፡፡ ባለቤታቸው ከዓመታት በፊት ነው የሞቱት፡፡
ከአባ በቀለ ጋር አብረው በአውራ ጎዳና ድርጅት ውስጥ ይሰሩ የነበሩ እና ወዳጆች እንደነበሩም ነግረውኛል፡፡ የቆየ ወዳጅነታቸውን ለማስቀጠል ጧሪ የሌላቸውን አባ በቀለን ልክ እንደ ቤተሰብ ወደ ቤታቸው እየመጡ ሲንከባከቧቸው ተመልክተናል፡፡ ከዚያ ውጭ ግን ቤቱ ባዶ ነው፡፡

አባ በቀለ በዚህ እድሜያቸው ወጥቶ ለመግባት ከጎናቸው የሚሆን ሰው ያስፈልጋቸዋል፡፡ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ስራ አስኪያጅ የነበሩት የሟች ስመኘው አባት፣አባ በቀለ አይናለም ተስፋቸው ተሟጦ፣ኑሯቸው ተናግቶ፣ደጋፊ እና ጧሪ፣ አይዞህ! ባይ እየፈለጉ ይገኛሉ፡፡
የኢንጅነር ስመኘው በቀለ ህልፈተ ህይወት ከተሰማ በኋላ ወይዘሮ ፍሬዓለም ሽባባው ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተው ነበር፡፡ቃላቸው ስለመተግበሩ ለመጠየቅ ወይዘሮ ፍሬዓለምን ለማግኘት ጥረት አደረግን፤ ነገር ግን ከሀገር ውጭ በመሆናቸው አልተሳካልንም፡፡ ሆኖም የሰቆጣ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ የኔው አምሳል ለአባ በቀለ ቃል የተገባውን ድጋፍ በተመለከተ ወይዘሮ ፍሬዓለም ሽባባውን ወክለው መረጃ ሰጥተውናል፡፡

‹‹የባለሙያዎች ቡድን በቦታው ተሰማርቶ አጥንቷል፡፡ምን አይነት ድጋፍ ነው የሚያስፈልጋቸው? እና በምን መልኩ ነው ድጋፉን የሚያገኙት? የሚለውን ኮሚቴው አጥንቶ አቅርቧል፡፡ ቋሚ ድጋፍ ለመወሰንም ምክክር ተደርጓል፡፡ በጥናቱም መሠረት ወርሀዊ አራት ሺህ ብር ለመስጠት ዛሬ ተወስኗል›› ነው ያሉት፡፡ ከመስከረም ወር ጀምሮ ድጋፉ እንደሚሰጣቸውም አቶ የኔው ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ተናግረዋል፡፡
በሚዲያ ቀርባችሁም ሆነ በአካል ተገኝታችሁ እርሳቸውን ለመርዳት ቃል የገባችሁ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የት አላችሁ? ከአሁኑ ሁኔታቸው የከፋ የምንደርስላቸው ጊዜ ላይኖር ይችላልና ቀድመን ብንደርስላቸውስ?

የባንክ አካውንት ቁጥር 
2030416173549018 
በቀለ አይናለም አየለ 
ሕብረት ባንክ ጎንደር ቅርንጫፍ

ዘጋቢ፡- ኃይሉ ማሞ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on October 8, 2018
  • By:
  • Last Modified: October 8, 2018 @ 5:35 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar