ባለፈው አንድ አመት ውስጥ በጀግኖች መሪዎቻችን ላይ የተሞከረው እና የተመከረው የግዲያ ሚስጥር፦
ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ላይ የተደረገ ሙከራ፦
——————-
#1ኛ. ልክ ለኦቦ ለማ መገርሳ ጠባቂዎች ሁለት ሁለት
ሚሊዮን ብር የነብስ ወከፍ ክፍያ ሰጥቶ ለማስገደል
እንደተሞከረው ሁሉ ለዶ/ር አብይ ጠባቂዎችም ሁለት ሁለት ሚሊዬን እንደሚሠጣቸው ቃል ተገብቶላቸው ለመግደል ተስማምተው ነበር።ዳሩ ግን ጠባቂዎቹ በዶ/ር አብይ ፍቅር የተሸነፉ ስለነበር የተነገራቸውን ሚስጥር ነግረውት ከሃገር ይወጣ ዘንድ ምክር ለገሱት።እሱ ግን ወገኖቼን ትቼ የትም ንቅንቅ አልልም የሚል አቋም ያዘ። ከዚያ ለባለቤቱ ነገረው ባለቤቱም ከሃገር መውጣት አለብን የሚል ድምዳሜ ላይ ደረሰች። ዶ/ር አብይ ግን በውሳኔው ፀንቶ የአብራኩ ክፋዮች ልጆቹ በጣም ስላሳዘኑት እነሱን አሜሪካን ሃገር አድርሶ እሱ ግን የህይወት መስዋትነት ለመክፈል እራሱን አዘጋጅቶ ወደ እናት ሃገሩ ተመለሠ።እንዳትረሱ ለመሞት ወስኖ ወደ
ኢትዮጲያ ተመለሰ።
#2ኛ. ከጠባቂዎቹ አንዱ ሊገድለው ተስማምቶ እሽታንም
ተቀብሎ ነበር። ነገር ግን ገራገሩ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ ለዚህ ጠባቂው ምንም ሳይነግረው የውጭ ትምህርት ጨርሶለት፤ ቨዛም ጭምር ያለቀ ስለነበር ለትምህርት ወደ ውጭ ሄደ።ጠባቂውም ከሄደ በኋላ ታቅዶ የነበረውን ሚስጥረ ግዲያ ለጠቅላያችን ነገረው።
#3ኛ. ከሃረርጌ የኦሮሞ ህዝብ ጋር በሃረር ከተማ ምክክር ላይ በነበረ ግዜ የታጠቁ የመከላከያ አባላት ያለፍቃድ ወደ ስብሰባው ውስጥ ለምግባት ያደረጉት መከራ በጠባቂዎቹ ከሸፈ።
#4ኛ. መሃል አዲስ አበባ፣አብዮት አደባባይ ላይ የተሞከረውን የግዲያ ሙከራ የምታስታውሱት የአደባባይ ማስጥር ነው።
#5ኛ. አዲስ አበባ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ቢሮ ፊትለፊት ያለ ህንፃ ላይ ስናይፐር ወድሮ የጠቅላዩን መውጫ እና መግቢያ ሲጠባበቁ እንደነበር የተደረሰበት ሃቅ ነው።
#6ኛ. የደሞዝ ጥያቄ ነው የሚል ጭንብል አጥልቀው ከነሙሉ ትጥቃቸው ወደ ቤተመንግስት የተመሙትም የመከላከያ አባላት የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ናቸው።
እንግዲህ አስተውሉ ወንድሞቼ ከሞት ጋር ታግሎ እኛን ነፃ ያወጣን መሪ ነው። ሞቶ እኛን ያኖረን መሪ ነው። የዚህን ሃገር ህዝብ ከወለዳቸው ልጆች አስበልጦ እነሱን ሸኝቶ ለመሞት ወስኖ የተመለሰ ታላቅ መሪ ነው። ነፍሱን አሲዞ እንደልባችን አፋችንን እንድንከፍት ያረገና ጀግና መሪ ነው።በህይዎቱ ላይ ወስኖ፤በሞት ውስጥ ታግሎ እኝን ከእስር ያስፈታን ብርቅዬ መሪ ነው። ታዲያ ዛሬ በህይዎቱ ቆምሮ ለኛ ህይወት የሰጠን መሪ ላይ ፊት ማዞርን ምን አመጣው? ከልጆቹ እኛን የመረጠ የክፈለ ዘመኑ ምርጥ መሪ ላይ ሠልፍ መውጣትና መዶለቱንስ ከቶ ምን ወለደው? እና ወገኖቼ ደግመን ደጋግመን ብናሰላስል ተጠቃሚዎቹ እኛ እንጂ ዶ/ር አብይ እንዳልሆነ ብንገነዘብ መልካም ነው።
መልካም ጊዜ
Average Rating