www.maledatimes.com የሹመት ሳምንታት በአብይ አህመድ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የሹመት ሳምንታት በአብይ አህመድ

By   /   November 5, 2018  /   Comments Off on የሹመት ሳምንታት በአብይ አህመድ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 3 Second

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ጀምረው ካከናወኗቸው በርካታ የለውጥ ርምጃዎች ሴቶችን ወደ ከፍተኛ የአመራር እርከኖች ማሳደጋቸውና በሃገራችን የፓለቲካዊ የስልጣን ክፍፍል ባልተለመደ መልኩ የከፍተኛ የአመራርና የሀላፊነት ቦታዎች በተለይም ደግሞ ከ20 የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ሹመቶች ለሴቶች ግማሹን መስጠታቸው፣ የርዕሰ ብሔርንና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትነትን አሁንም ሴቶችን መሰየማቸው አለም አቀፍ አድናቆትን እያስገኘላቸው ነው። 
ለነዚህ የጠቅላይ ሚስትሩ አብይ ርምጃዎች አንድም በአለማችን እየተለመደና እያደገ የመጣው የሴቶች ፖለቲካዊ ተሳትፎ በአለም አቀፍ ደረጃ እያደገ መምጣት፣ በሴቶች አመራር አለማችን እያስመዘገበች ያለቸው ስኬትና የለጋሽ አገሮችና የአለም አቀፍ ቋማት ግፊቶች እንደ ምክንያትነት መቆጠራቸው እንዳለ ሆኖ፤ የኛ ጠቅላይ ሚንስትር ግን ባለፉት 2 ወራት ሴቶችን ወደ ከፍተኛ የአመራር እርከኖች ማምጣትና ካቢኔያቸውን 50 በመቶ ለሴቶች የመስጠትን ውሳኔ በዛሬው ዕለት የፅህፈት ቤታቸው የፕሬስ ሴክሬታሪያት አድርገው ከሾሟት ቢልለኔ ስዩምና ሌላዋ የሴቶች መብት ተከራካሪ የሰዊት ኃይለሥላሴን ምክር ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረጋቸው መሆኑን ከሚከተለው ፅሁፍ በቀላሉ ማረጋገጥ ይቻላል።
ቢልለኔ እና ሰዊት የዛሬ 5 ወር አካባቢ ” ግልፅ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ” በሚል ርዕስ ጠቅላይ ሚንስትሩ የሴቶችን ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ የካቢኔያቸውን ግማሽ ለሴቶች ከመስጠት አልፎ የሚንስቴር መስሪያ ቤቶቻቸውን እንዴት ማዋቀር እንደሚኖርባቸው ሁለቱ እንስት መክረዋቸው ነበር።
ጠቅላይ ሚንስትሩም አላሳፈሯቸውም ምክራቸውን ተቀብለው ከወራት በኋላ በተግባር አሳይተዋቸዋል። አቶ ዘይኑ ጀማል የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ አቶ እንደሻው ጣሰው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል።

አቶ እንደሻው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በጅማ ዩኒቨርሲቲ፤ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ ከሐገር ውጭ ተከታትለዋል፡፡

Image may contain: 1 person, sitting

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on November 5, 2018
  • By:
  • Last Modified: November 5, 2018 @ 7:30 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar