ማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል
” December 4 እና 5 2018 እ.ኤ.አ http://www.maledatimes.comዓለም አቀፍ የቡና ኮንፌረንስ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድና ከጉባኤ በኃላ ለዓለም የቡና መገኛ ወደ ሆነዉ ካፋ ዞን እና ብቸኛዉ የብሔራዊ ቡና ሙዚዬም የሚገኝበት ቦንጋ ከተማ እናት ቡና ወደምትገኝበት ዴቻ ወረዳ ማንኪራ ቀበሌ ቡኒ መንድር ጉብኝት እንደሚደረግ November 2 post ማድረጉ ይታወቃል ፡፡ሆኖም ግን ባለስልጣን መ/ቤት 22/02/2011 ዓ.ም ወብ ሳይታቸዉ (website) ላይ የለቀቁትን በመቀየር የአንድን ሕዝብ ታሪክ በተዛባ መልኩ መረጃንአሰራጭተዋል ፡፡ ይህ ደግሞ የአንድ ሕዝብን ታሪክ በተሳሳተ መረጃ ታሪኩናንና ማነቱን የማጥፋትና እንዲሁም የሀገራችንን ሕዝብ በማሳሳት ሕዝብና ሕዝብን ለማጋጨት የተሰራ ግልፅ ደባ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ አሁን ሀገራችን የጀመረችዉን ሠላምንና ድሞክራሲን የማጎልበቱን ሂደት የሚያጨናግፍ እንዲሁም በካፋ ሕዝብ ላይ የታወጀ የታሪክ ስርቆት ነው:: እንዲህ ዓይነቱ የማንነት ዘረፋ በእጅጉ ያስቆጣው የካፋ ህዝብ በ28/2/2011 ከያሉበት በመውጣት በከፍተኛ ሁኔታ ተቃውሟቸውን ማሰማት ከጀመሩ እነሆ 3 ቀን ሆኗቸዋል። መንግስት በጉዳዩ ላይ ትክክለኛውን ምላሽ እስኪሰጥ ድረስ በካፋ ዞን በአጠቃላይ የትራንስፖርትና የንግድ እንቅስቃሴዎች ተቋርጠዋል:: ይሁንና መንግስት በጉዳዩ ላይ እስካሁን ምንም ዓይነት ምላሽ አልሰጠም::የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን ሀገር የማፍረስ ሥራ የተሰማሩትን ተቋማትንና በተቋሙ ዉስጥ በእንደዚህ አይነቱ እኩይ ተግባር ላይ የተሰማሩትን በማጣራት እርምጃ እንዲወሰድባቸዉ ሕዝቡ አጥብቆ በመጠየቅ ላይ ይገኛል፡፡በእንደዚህ አይነተ ተግባር ላይ የተሰማራዉ ተቋም በአሁኑ ጊዜ የጀመርነዉን ለዉጥ የማደፍረስና የሀገራችንን አንድነት ሆነ ብሎ ለማፍረስ ዝግጁ መሆናቸዉን በተግባር አሳይተዋሉ ፡፡ይሁንና የካፋ ህዝብ በጨዋነቱና በአስተዋይነቱ እንዲሁም በአርቆ አሳቢነት ስለሚታወቅ ጉዳዩን የሚመለከተው አካል ማለትም የፌደራል መንግስት በአስቸኳይ ትክክለኛውን ምላሽ በማንነቱ ለማይደራደረው የካፋ ህዝብ እንዲሰጥ ያስፈልጋል ብለዋል::ይህን አስነዋሪና ቆሻሻ ተግባር የፈፀሙት ግለሰቦችም ሆኑ ተቋማት ባስቸኳይ እንዲመረመሩና ባደረጉት ተግባር ትክክለኛ እርምጃ እንዲወስድባቸው በማለት በአፅኖት ጠይቀዋል። ይህ ካልሆነ ግን ትክክለኛውን ፍትህ እስክናገኝ ድረስ ተቃውሟችን ይቀጥላል በማለት አቋማቸውን ገልፀዋል። አያይዘውም እስከዛሬ ድረስ ሲበደልና ሲዘረፍ የነበረው የካፋ ህዝብ ቡናን በተመለከተ ከሚያቀርበው የማነንት ጥያቄ በተጨማሪ እኛ ራሳችንን ማስተዳደር እንችላለን፣ ካሁን በሗላ የደቡብ ክልል የሚባል የአሸንጉልቶች ድርጅት አይወክለንም፣ ራሳችንን ማስተዳደር ስለምንችል የክልል ጥያቄያችን ይመለስልን በማለት አቋማቸውን በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።”BY KUMILACHEW AMBOhttps://www.youtube.com/watch?v=fmK6Jv2FJmI&feature=youtu.be
Average Rating